-
ዘሌዋውያን 23:27-31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። 29 በዚህ ቀን ራሱን የማያጎሳቁል* ማንኛውም ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።+ 30 በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ የሚሠራን ሰው* ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 31 ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው።
-