-
ዘኁልቁ 28:3-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “እንዲህም በላቸው፦ ‘ለይሖዋ የምታቀርቡት በእሳት የሚቃጠል መባ ይህ ነው፦ በየቀኑ፣ አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ዘወትር አቅርቡ።+ 4 አንደኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ፣ ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* አቅርቡ፤+ 5 ከእነዚህም ጋር ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ 6 ይህም በሲና ተራራ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው፤ 7 ከዚህም ጋር የመጠጥ መባውን ይኸውም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን አቅርቡ።+ የሚያሰክረውን መጠጥ ለይሖዋ እንደሚቀርብ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ በቅዱሱ ስፍራ አፍሱት። 8 ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* አቅርቡት። ከእሱም ጋር ማለዳ ላይ የሚቀርበውን ዓይነት የእህል መባና ከእሱ ጋር አብሮ የሚቀርበውን ዓይነት የመጠጥ መባ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።+
-