16 ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን+ የአርኖንን ሸለቆ መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤ 17 እንዲሁም ከኪኔሬት አንስቶ በአረባ እስከሚገኘው ባሕር ይኸውም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ያለውን አረባን፣ ዮርዳኖስንና ወሰኑን ሰጠኋቸው።+