7 በመሆኑም በንፍታሌም ተራራማ አካባቢ በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን፣+ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ሴኬምንና+ በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ ማለትም ኬብሮንን ለዚህ ዓላማ ቀደሱ። 8 ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ባለው የዮርዳኖስ ክልል ደግሞ ከሮቤል ነገድ ርስት በአምባው ላይ በሚገኘው ምድረ በዳ ላይ ያለችውን ቤጼርን፣+ ከጋድ ነገድ ርስት በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ ርስት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ መረጡ።+