3 ይሖዋ ከከነአን ጋር በተደረገው ጦርነት ያልተካፈሉትን እስራኤላውያን ሁሉ እንዲፈትኗቸው+ ሲል በምድሪቱ ላይ እንዲኖሩ የፈቀደላቸው ብሔራት እነዚህ ናቸው 2 (ይህን ያደረገው ከዚህ በፊት ተዋግተው የማያውቁት በኋላ ላይ የመጡት የእስራኤላውያን ትውልዶች የውጊያ ልምድ እንዲያገኙ ነው)፦ 3 አምስቱ የፍልስጤም+ ገዢዎች፣ ከነአናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያን+ እንዲሁም ከበዓልሄርሞን ተራራ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት + ድረስ በሚዘልቀው የሊባኖስ+ ተራራ የሚኖሩት ሂዋውያን።+