-
ዘሌዋውያን 7:33-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ስቡን የሚያቀርበው የአሮን ልጅ የእንስሳውን ቀኝ እግር እንደ ድርሻው አድርጎ ይወስዳል።+ 34 እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ ሆኖ የቀረበውን እግር እወስዳለሁ፤ ለእስራኤላውያንም ዘላቂ ሥርዓት እንዲሆን ለካህኑ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ እሰጣቸዋለሁ።+
35 “‘ካህናት ሆነው ይሖዋን ለማገልገል በሚቀርቡበት ቀን፣ ለይሖዋ በእሳት ከቀረቡት መባዎች ላይ ለካህናቱ ይኸውም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሚመደብላቸው ድርሻ ይህ ነው።+
-
-
ዘዳግም 18:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይሰጣቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ።+
-