ዘሌዋውያን 19:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በስሜ በሐሰት አትማሉ፤+ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። መሳፍንት 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የእስራኤል ሰዎች በምጽጳ+ ተሰብስበው “ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ከቢንያም ወገን ለሆነ ሰው መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።+