1 ሳሙኤል 16:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከጊዜ በኋላ ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሳኦል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን አልፈለግኩም፤+ ታዲያ አንተ ለእሱ የምታዝነው እስከ መቼ ነው?+ በል ቀንድህን ዘይት ሙላና+ ሂድ። የቤተልሔም ሰው ወደሆነው ወደ እሴይ+ እልክሃለሁ፤ ምክንያቱም ከወንዶች ልጆቹ መካከል ንጉሥ የሚሆንልኝ ሰው መርጫለሁ።”+ 1 ሳሙኤል 16:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እነሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤልያብን+ ሲያየው “መቼም ይሖዋ የሚቀባው ሰው ይህ መሆን አለበት” አለ። 1 ሳሙኤል 17:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ታላቅ ወንድሙ ኤልያብም+ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሲሰማ በእሱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ የወረድከው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እነዚያን ጥቂት በጎች ምድረ በዳ ላይ ለማን ተውካቸው?+ እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፉ ሐሳብ መች አጣሁት፤ ወደዚህ የመጣኸው ለሌላ ሳይሆን ውጊያውን ለማየት ነው።”
16 ከጊዜ በኋላ ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሳኦል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን አልፈለግኩም፤+ ታዲያ አንተ ለእሱ የምታዝነው እስከ መቼ ነው?+ በል ቀንድህን ዘይት ሙላና+ ሂድ። የቤተልሔም ሰው ወደሆነው ወደ እሴይ+ እልክሃለሁ፤ ምክንያቱም ከወንዶች ልጆቹ መካከል ንጉሥ የሚሆንልኝ ሰው መርጫለሁ።”+
28 ታላቅ ወንድሙ ኤልያብም+ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሲሰማ በእሱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ የወረድከው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እነዚያን ጥቂት በጎች ምድረ በዳ ላይ ለማን ተውካቸው?+ እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፉ ሐሳብ መች አጣሁት፤ ወደዚህ የመጣኸው ለሌላ ሳይሆን ውጊያውን ለማየት ነው።”