-
1 ነገሥት 6:31-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 ለውስጠኛው ክፍል መግቢያ የሚሆኑ በሮችን፣ በጎንና በጎን የሚቆሙ ዓምዶችንና መቃኖችን አንድ አምስተኛ* አድርጎ ከጥድ እንጨት ሠራ። 32 ሁለቱ በሮች ከጥድ እንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ በበሮቹም ላይ የኪሩቦችን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጣቸው፤ ደግሞም ወርቁን በኪሩቦቹና በዘንባባ ዛፎቹ ላይ ጠፈጠፈው። 33 ለቤተ መቅደሱ* መግቢያ የሚሆኑትንና የአንድ አራተኛው* ክፍል የሆኑትን የጥድ እንጨት መቃኖች የሠራው በዚሁ መንገድ ነበር። 34 እሱም ከጥድ እንጨት ሁለት በሮች ሠራ። ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት አንዱ በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ፣ ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት ሌላኛውም በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ ተገጥሞ ነበር።+ 35 እሱም ኪሩቦችን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸ፤ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።
-