የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሦስተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-11)

      • አራተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (12-25)

ዘኁልቁ 24:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በይሖዋ ዓይን መልካም እንደሆነ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 23:3, 15, 23

ዘኁልቁ 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 2:2፤ 23:9
  • +1ሳሙ 19:20

ዘኁልቁ 24:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 23:7, 18

ዘኁልቁ 24:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 24:16

ዘኁልቁ 24:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 1:52፤ 2:2

ዘኁልቁ 24:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዞች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 22:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2014፣ ገጽ 10

ዘኁልቁ 24:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:7
  • +ዘፍ 49:10፤ መዝ 2:6፤ ዮሐ 1:49
  • +ዘኁ 24:20
  • +1ዜና 14:2፤ ዳን 2:44፤ ራእይ 11:15

ዘኁልቁ 24:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:27፤ ዘዳ 9:5

ዘኁልቁ 24:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:1-3፤ 27:29

ዘኁልቁ 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 22:10, 11፤ 23:11፤ ነህ 13:1, 2

ዘኁልቁ 24:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 22:16, 17

ዘኁልቁ 24:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከልቤ አመንጭቼ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 22:18, 38

ዘኁልቁ 24:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቀኖቹ መጨረሻ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2022፣ ገጽ 6

ዘኁልቁ 24:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 23:7
  • +ዘኁ 24:3, 4

ዘኁልቁ 24:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰሪሳራ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 22:16
  • +መዝ 110:2፤ ዕብ 1:8
  • +2ሳሙ 7:16, 17፤ ኢሳ 9:7
  • +2ሳሙ 8:2፤ 1ዜና 18:2፤ መዝ 108:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ራእይ፣ ገጽ 53, 318

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2005፣ ገጽ 17

ዘኁልቁ 24:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 27:37፤ 2ሳሙ 8:14፤ አሞጽ 9:11, 12
  • +ዘፍ 36:8፤ ኢያሱ 24:4
  • +1ዜና 4:42, 43፤ ሕዝ 25:14

ዘኁልቁ 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:10፤ መዝ 2:9፤ 72:11፤ ራእይ 6:2፤ 19:15

ዘኁልቁ 24:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:8, 14
  • +ዘዳ 25:19፤ 1ሳሙ 15:3፤ 1ዜና 4:43

ዘኁልቁ 24:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18, 19፤ መሳ 1:16

ዘኁልቁ 24:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 4፤ ሕዝ 27:6
  • +ናሆም 3:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2007፣ ገጽ 18-19

ዘኁልቁ 24:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 31:7, 8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘኁ. 24:1ዘኁ 23:3, 15, 23
ዘኁ. 24:2ዘኁ 2:2፤ 23:9
ዘኁ. 24:21ሳሙ 19:20
ዘኁ. 24:3ዘኁ 23:7, 18
ዘኁ. 24:4ዘኁ 24:16
ዘኁ. 24:5ዘኁ 1:52፤ 2:2
ዘኁ. 24:6ዘኁ 22:11
ዘኁ. 24:7ዘዳ 8:7
ዘኁ. 24:7ዘፍ 49:10፤ መዝ 2:6፤ ዮሐ 1:49
ዘኁ. 24:7ዘኁ 24:20
ዘኁ. 24:71ዜና 14:2፤ ዳን 2:44፤ ራእይ 11:15
ዘኁ. 24:8ዘፀ 23:27፤ ዘዳ 9:5
ዘኁ. 24:9ዘፍ 12:1-3፤ 27:29
ዘኁ. 24:10ዘኁ 22:10, 11፤ 23:11፤ ነህ 13:1, 2
ዘኁ. 24:11ዘኁ 22:16, 17
ዘኁ. 24:13ዘኁ 22:18, 38
ዘኁ. 24:15ዘኁ 23:7
ዘኁ. 24:15ዘኁ 24:3, 4
ዘኁ. 24:17ራእይ 22:16
ዘኁ. 24:17መዝ 110:2፤ ዕብ 1:8
ዘኁ. 24:172ሳሙ 7:16, 17፤ ኢሳ 9:7
ዘኁ. 24:172ሳሙ 8:2፤ 1ዜና 18:2፤ መዝ 108:9
ዘኁ. 24:18ዘፍ 27:37፤ 2ሳሙ 8:14፤ አሞጽ 9:11, 12
ዘኁ. 24:18ዘፍ 36:8፤ ኢያሱ 24:4
ዘኁ. 24:181ዜና 4:42, 43፤ ሕዝ 25:14
ዘኁ. 24:19ዘፍ 49:10፤ መዝ 2:9፤ 72:11፤ ራእይ 6:2፤ 19:15
ዘኁ. 24:20ዘፀ 17:8, 14
ዘኁ. 24:20ዘዳ 25:19፤ 1ሳሙ 15:3፤ 1ዜና 4:43
ዘኁ. 24:21ዘፍ 15:18, 19፤ መሳ 1:16
ዘኁ. 24:24ዘፍ 10:2, 4፤ ሕዝ 27:6
ዘኁ. 24:24ናሆም 3:18
ዘኁ. 24:25ዘኁ 31:7, 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘኁልቁ 24:1-25

ዘኁልቁ

24 በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ* ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤+ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና። 2 በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤+ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ።+ 3 በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+

“የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣

ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣

 4 የአምላክን ቃል የሰማው፣

ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየው

ዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦+

 5 ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣

እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው!+

 6 እንደ ሸለቆዎች፣*

በወንዝም ዳር እንዳሉ የአትክልት ስፍራዎች በረጅሙ ተዘርግተዋል።+

ይሖዋ እንደተከላቸው እሬቶች፣

በውኃም ዳር እንዳሉ አርዘ ሊባኖሶች ሆነዋል።

 7 ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤

ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል።+

ንጉሡም+ ከአጋግ+ የላቀ ይሆናል፤

መንግሥቱም ከፍ ከፍ ይላል።+

 8 አምላክ ከግብፅ አወጣው፤

ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው።

የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤+

አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል።

 9 አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤

እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤

የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።”+

10 በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤+ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። 11 በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤+ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።”

12 በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? 13 ‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ* መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’+ 14 እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት* ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።” 15 ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+

“የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣

ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣+

16 የአምላክን ቃል የሰማው፣

የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤

ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለ

ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦

17 አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤

እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም።

ኮከብ+ ከያዕቆብ ይወጣል፤

በትረ መንግሥትም+ ከእስራኤል ይነሳል።+

የሞዓብን ግንባር፣*

የሁከት ልጆችንም ሁሉ ራስ ቅል ይፈረካክሳል።+

18 እስራኤል ጀግንነቱን ሲያሳይ

ኤዶም ርስቱ ይሆናል፤+

ሴይርም+ የጠላቶቹ ርስት ይሆናል።+

19 ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤+

የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።”

20 አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦

“አማሌቅ ከብሔራት መካከል የመጀመሪያ ነበር፤+

ሆኖም በመጨረሻ ይጠፋል።”+

21 ቄናውያንንም+ ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦

“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው።

22 ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል።

አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?”

23 እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦

“አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን?

24 ከኪቲም+ የባሕር ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤

አሦርንም ያጠቃሉ፤+

ደግሞም ኤቤርን ያሠቃያሉ።

ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።”

25 ከዚያም በለዓም+ ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ