93 ይሖዋ ነገሠ!+
ግርማ ተጎናጽፏል፤
ይሖዋ ብርታት ለብሷል፤
እንደ ቀበቶ ታጥቆታል።
ምድር በጽኑ ተመሥርታለች፤
ልትናወጥ አትችልም።
2 ዙፋንህ ከብዙ ዘመናት በፊት ጸንቶ የተመሠረተ ነው፤+
አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።+
3 ይሖዋ ሆይ፣ ወንዞቹ ጎረፉ፤
ወንዞቹ ጎረፉ፤ አስገመገሙም፤
ወንዞቹ ይጎርፋሉ፤ ደግሞም በኃይል ይላተማሉ።
4 ከብዙ ውኃዎች ድምፅ፣
ኃይለኛ ከሆነው የባሕር ማዕበልም በላይ፣+
ይሖዋ ከፍ ባለ ቦታ ግርማ ተጎናጽፏል።+
5 ማሳሰቢያዎችህ እጅግ አስተማማኝ ናቸው።+
ይሖዋ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለሙ በቅድስና ያጌጠ ነው።+