አሞጽ
ችግረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ግፍ የምትፈጽሙና+ ድሆችን የምትጨቁኑ ሴቶች፣
ባሎቻችሁንም* ‘የምንጠጣው ነገር አምጡልን!’
የምትሉ የባሳን ላሞች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ።
2 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በቅድስናው ምሏል፤
‘“እነሆ፣ እናንተን በሜንጦ፣
ከእናንተ የቀሩትንም በመንጠቆ የሚያነሳበት ቀን እየመጣባችሁ ነው።
3 እያንዳንዳችሁ ከፊታችሁ በምታገኟቸው፣ በቅጥሩ ላይ ባሉት ክፍተቶች በኩል ትወጣላችሁ፤
ወደ ሃርሞንም ትጣላላችሁ” ይላል ይሖዋ።’
5 እርሾ ያለበትን ዳቦ የሚቃጠል የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤+
በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትንም መባ በአዋጅ አስነግሩ!
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
7 ‘በተጨማሪም መከር ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኳችሁ፤+
በአንዱ ከተማ ዝናብ እንዲዘንብ ሳደርግ በሌላው ከተማ ግን እንዳይዘንብ አደረግኩ።
አንዱ እርሻ ዝናብ ያገኛል፤
ዝናብ ያላገኘው ሌላው እርሻ ግን ይደርቃል።
8 በሁለት ወይም በሦስት ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ውኃ ለመጠጣት ወደ አንዲት ከተማ እያዘገሙ ሄዱ፤+
ይሁንና ጥማቸውን ማርካት አልቻሉም፤
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
9 ‘በሚያቃጥል ሙቀትና በዋግ መታኋችሁ።+
የአትክልት ስፍራዎቻችሁንና የወይን እርሻዎቻችሁን አበዛችሁ፤
ይሁንና የበለስ ዛፎቻችሁንና የወይራ ዛፎቻችሁን አንበጣ ይበላቸዋል፤+
ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
10 ‘በግብፅ ላይ የደረሰውን ዓይነት ቸነፈር ሰደድኩባችሁ።+
ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልኩ፤+ ፈረሶቻችሁንም ማረክሁ።+
የሰፈሮቻችሁ ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግኩ፤+
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ።
11 ‘ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጥኳቸው ሁሉ
ምድራችሁን ገለበጥኩ።+
እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ጉማጅ ነበራችሁ፤
ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
12 ስለዚህ እስራኤል ሆይ፣ እንዲሁ አደርግብሃለሁ።
እስራኤል ሆይ፣ ይህን ነገር ስለማደርግብህ
አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።