የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ይስሐቅ ያዕቆብን ወደ ጳዳንአራም ላከው (1-9)

      • ያዕቆብ በቤቴል ያለመው ሕልም (10-22)

        • አምላክ የሰጠውን ተስፋ በድጋሚ ለያዕቆብ አረጋገጠለት (13-15)

ዘፍጥረት 28:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 24:34, 37፤ ዘፀ 34:15, 16፤ 1ነገ 11:1-3፤ 2ቆሮ 6:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1995፣ ገጽ 13

ዘፍጥረት 28:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:16

ዘፍጥረት 28:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 17:5፤ 46:15, 19፤ 1ዜና 2:1, 2

ዘፍጥረት 28:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:7፤ 15:13፤ 17:1, 8፤ ዕብ 11:9
  • +ዘፍ 12:2, 3

ዘፍጥረት 28:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 24:29
  • +ዘፍ 25:20

ዘፍጥረት 28:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:1፤ 2ቆሮ 6:14

ዘፍጥረት 28:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 27:43

ዘፍጥረት 28:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 27:46

ዘፍጥረት 28:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 36:2, 3

ዘፍጥረት 28:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:31፤ 27:43

ዘፍጥረት 28:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:18, 19

ዘፍጥረት 28:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መሰላል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 1:51፤ ዕብ 1:7, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2004፣ ገጽ 28

    10/15/2003፣ ገጽ 28-29

ዘፍጥረት 28:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 26:24, 25
  • +ዘፍ 12:7፤ 28:4፤ መዝ 105:9-11

ዘፍጥረት 28:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 13:14, 16፤ 1ነገ 4:20
  • +ዘፍ 18:18፤ 22:15, 18

ዘፍጥረት 28:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:6
  • +ዘፍ 31:3፤ ዘኁ 23:19፤ ኢያሱ 23:14፤ ዕብ 6:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2013፣ ገጽ 21

ዘፍጥረት 28:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 47:2
  • +ዘፍ 35:1

ዘፍጥረት 28:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:13

ዘፍጥረት 28:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የአምላክ ቤት” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:6፤ ኢያሱ 16:1, 2

ዘፍጥረት 28:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 170

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 28:1ዘፍ 24:34, 37፤ ዘፀ 34:15, 16፤ 1ነገ 11:1-3፤ 2ቆሮ 6:14
ዘፍ. 28:2ዘፍ 29:16
ዘፍ. 28:3ዘፍ 17:5፤ 46:15, 19፤ 1ዜና 2:1, 2
ዘፍ. 28:4ዘፍ 12:7፤ 15:13፤ 17:1, 8፤ ዕብ 11:9
ዘፍ. 28:4ዘፍ 12:2, 3
ዘፍ. 28:5ዘፍ 24:29
ዘፍ. 28:5ዘፍ 25:20
ዘፍ. 28:6ዘፍ 28:1፤ 2ቆሮ 6:14
ዘፍ. 28:7ዘፍ 27:43
ዘፍ. 28:8ዘፍ 27:46
ዘፍ. 28:9ዘፍ 36:2, 3
ዘፍ. 28:10ዘፍ 11:31፤ 27:43
ዘፍ. 28:11ዘፍ 28:18, 19
ዘፍ. 28:12ዮሐ 1:51፤ ዕብ 1:7, 14
ዘፍ. 28:13ዘፍ 26:24, 25
ዘፍ. 28:13ዘፍ 12:7፤ 28:4፤ መዝ 105:9-11
ዘፍ. 28:14ዘፍ 13:14, 16፤ 1ነገ 4:20
ዘፍ. 28:14ዘፍ 18:18፤ 22:15, 18
ዘፍ. 28:15ዘፍ 35:6
ዘፍ. 28:15ዘፍ 31:3፤ ዘኁ 23:19፤ ኢያሱ 23:14፤ ዕብ 6:18
ዘፍ. 28:17መዝ 47:2
ዘፍ. 28:17ዘፍ 35:1
ዘፍ. 28:18ዘፍ 31:13
ዘፍ. 28:19ዘፍ 35:6፤ ኢያሱ 16:1, 2
ዘፍ. 28:22ዘፍ 35:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 28:1-22

ዘፍጥረት

28 በመሆኑም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ ባረከውና እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ።+ 2 በጳዳንአራም ወደሚገኘው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድና ከእናትህ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች+ መካከል አንዷን አግባ። 3 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ይባርክሃል፤ ፍሬያማም ያደርግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል፤ አንተም በእርግጥ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤ ትሆናለህ።+ 4 አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን፣+ አንተም እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ የምትኖርበትን ምድር እንድትወርስ የአብርሃምን በረከት+ ለአንተና ከአንተ ጋር ላለው ዘርህ ይሰጣል።”

5 ስለሆነም ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ እሱም የያዕቆብና የኤሳው እናት የርብቃ ወንድም+ እንዲሁም የአራማዊው የባቱኤል ልጅ ወደሆነው ወደ ላባ+ ለመሄድ ወደ ጳዳንአራም ጉዞ ጀመረ።

6 ኤሳው፣ ይስሐቅ ያዕቆብን እንደባረከውና ሚስት እንዲያገባ ወደ ጳዳንአራም እንደላከው እንዲሁም በባረከው ጊዜ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ”+ ብሎ እንዳዘዘውና 7 ያዕቆብም አባቱንና እናቱን በመታዘዝ ወደ ጳዳንአራም እንደሄደ አወቀ።+ 8 በዚህ ጊዜ ኤሳው የከነአን ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤+ 9 ስለዚህ ኤሳው ወደ እስማኤል ሄደ፤ ካሉትም ሚስቶች በተጨማሪ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን የነባዮትን እህት ማሃላትን አገባ።+

10 ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነስቶ ወደ ካራን አቀና።+ 11 ከዚያም ወደ አንድ ስፍራ ደረሰ፤ ፀሐይ ጠልቃ ስለነበረም እዚያ ለማደር አሰበ። በመሆኑም በአካባቢው ካሉት ድንጋዮች አንዱን አንስቶ በመንተራስ እዚያው ተኛ።+ 12 እሱም ሕልም አለመ፤ በሕልሙም በምድር ላይ የተተከለ ደረጃ* አየ፤ የደረጃውም ጫፍ እስከ ሰማያት ይደርስ ነበር፤ በላዩም ላይ የአምላክ መላእክት ይወጡና ይወርዱ ነበር።+ 13 ከደረጃውም በላይ ይሖዋ ነበር፤ እሱም እንዲህ አለ፦

“እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክና የይስሐቅ አምላክ ይሖዋ ነኝ።+ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።+ 14 ዘርህም በእርግጥ እንደ ምድር አፈር ብዙ ይሆናል፤+ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ትስፋፋለህ። የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካኝነት በእርግጥ ይባረካሉ።*+ 15 እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ።+ የገባሁልህን ቃል እስክፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”+

16 ከዚያም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ነቅቶ “በእርግጥም በዚህ ስፍራ ይሖዋ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅኩም ነበር” አለ። 17 እሱም በፍርሃት ተዋጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህ የአምላክ ቤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፤+ ይህ የሰማያት በር ነው።”+ 18 በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት።+ 19 ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል* አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ+ ነበር።

20 ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፦ “አምላክ ከእኔ ባይለይና በመንገዴ ቢጠብቀኝ እንዲሁም የምበላው ምግብና የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ፣ 21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብመለስ ይሖዋ አምላኬ መሆኑን አስመሠከረ ማለት ነው። 22 እንደ ዓምድ ያቆምኩት ይህ ድንጋይም የአምላክ ቤት ይሆናል፤+ አምላክ ሆይ፣ እኔም ከምትሰጠኝ ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለአንተ እሰጣለሁ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ