የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መሳፍንት የመጽሐፉ ይዘት

      • መሳፍንቱ ቶላና ያኢር (1-5)

      • እስራኤላውያን ዓመፁ፤ በኋላም ንስሐ ገቡ (6-16)

      • አሞናውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ (17, 18)

መሳፍንት 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:16

መሳፍንት 10:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:14

መሳፍንት 10:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሶርያን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:19፤ 4:1፤ 6:1፤ ነህ 9:28
  • +መሳ 3:7፤ መዝ 106:36-38
  • +ዘኁ 25:1, 2
  • +1ነገ 11:5፤ 2ነገ 23:13
  • +መሳ 16:23፤ 1ሳሙ 5:4፤ 2ነገ 1:2

መሳፍንት 10:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 48፤ 31:17፤ መሳ 2:14፤ 4:2

መሳፍንት 10:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2007፣ ገጽ 8

መሳፍንት 10:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:13፤ 3:7፤ 1ሳሙ 12:9, 10
  • +ዘዳ 4:30

መሳፍንት 10:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:30
  • +ዘኁ 21:23-25
  • +መሳ 3:31

መሳፍንት 10:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:12
  • +2ዜና 15:2፤ ሚክ 3:4

መሳፍንት 10:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 18:27
  • +ኤር 2:28

መሳፍንት 10:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱ ልትታገሥ አልቻለችም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:26
  • +2ዜና 7:14፤ 33:13, 15፤ መዝ 106:44፤ ኢሳ 63:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 254

መሳፍንት 10:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:36, 38፤ መሳ 3:13

መሳፍንት 10:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 11:1

ተዛማጅ ሐሳብ

መሳ. 10:1መሳ 2:16
መሳ. 10:4ዘዳ 3:14
መሳ. 10:6መሳ 2:19፤ 4:1፤ 6:1፤ ነህ 9:28
መሳ. 10:6መሳ 3:7፤ መዝ 106:36-38
መሳ. 10:6ዘኁ 25:1, 2
መሳ. 10:61ነገ 11:5፤ 2ነገ 23:13
መሳ. 10:6መሳ 16:23፤ 1ሳሙ 5:4፤ 2ነገ 1:2
መሳ. 10:7ዘዳ 28:15, 48፤ 31:17፤ መሳ 2:14፤ 4:2
መሳ. 10:10መሳ 2:13፤ 3:7፤ 1ሳሙ 12:9, 10
መሳ. 10:10ዘዳ 4:30
መሳ. 10:11ዘፀ 14:30
መሳ. 10:11ዘኁ 21:23-25
መሳ. 10:11መሳ 3:31
መሳ. 10:13መሳ 2:12
መሳ. 10:132ዜና 15:2፤ ሚክ 3:4
መሳ. 10:141ነገ 18:27
መሳ. 10:14ኤር 2:28
መሳ. 10:16ዘዳ 7:26
መሳ. 10:162ዜና 7:14፤ 33:13, 15፤ መዝ 106:44፤ ኢሳ 63:9
መሳ. 10:17ዘፍ 19:36, 38፤ መሳ 3:13
መሳ. 10:18መሳ 11:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መሳፍንት 10:1-18

መሳፍንት

10 ከአቢሜሌክ በኋላ የዶዶ ልጅ፣ የፑሃ ልጅ የይሳኮር ሰው የሆነው ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሳ።+ እሱም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች በምትገኘው በሻሚር ይኖር ነበር። 2 በእስራኤልም ውስጥ ለ23 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። ከዚያም ሞተ፤ በሻሚርም ተቀበረ።

3 ከእሱም በኋላ ጊልያዳዊው ያኢር ተነሳ፤ በእስራኤልም ውስጥ ለ22 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። 4 ያኢር በ30 አህዮች የሚጋልቡ 30 ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ ሃዎትያኢር+ ተብለው የሚጠሩ 30 ከተሞች ነበሯቸው፤ ከተሞቹም የሚገኙት በጊልያድ ምድር ነው። 5 ከዚያም ያኢር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።

6 እስራኤላውያንም በይሖዋ ፊት እንደገና መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ባአልን፣+ የአስታሮትን ምስሎች፣ የአራምን* አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣+ የአሞናውያንን አማልክትና+ የፍልስጤማውያንን አማልክት+ ማገልገል ጀመሩ። ይሖዋን ተዉት፤ እሱንም አላገለገሉም። 7 የይሖዋም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ እነሱንም ለፍልስጤማውያንና ለአሞናውያን ሸጣቸው።+ 8 ስለሆነም በዚያ ዓመት እስራኤላውያንን አደቀቋቸው፤ ክፉኛም ጨቆኗቸው፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በጊልያድ በሚገኘው በአሞራውያን ምድር የነበሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ለ18 ዓመት ጨቆኗቸው። 9 በተጨማሪም አሞናውያን ይሁዳን፣ ቢንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ይሻገሩ ነበር፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨንቀው ነበር። 10 ከዚያም እስራኤላውያን “አንተን አምላካችንን ትተን ባአልን በማገልገላችን+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናል” በማለት ይሖዋ እንዲረዳቸው ጮኹ።+

11 ሆኖም ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “ግብፃውያን፣+ አሞራውያን፣+ አሞናውያን፣ ፍልስጤማውያን፣+ 12 ሲዶናውያን፣ አማሌቃውያንና ምድያማውያን በጨቆኗችሁ ጊዜ አላዳንኳችሁም? ወደ እኔ ስትጮኹ ከእጃቸው ታደግኳችሁ። 13 እናንተ ግን እኔን ትታችሁ ሌሎች አማልክትን አገለገላችሁ።+ ዳግመኛ የማላድናችሁም በዚህ የተነሳ ነው።+ 14 ወደመረጣችኋቸው አማልክት ሂዱና እንዲረዷችሁ ጠይቋቸው።+ በጭንቀታችሁ ጊዜ እነሱ ያድኗችሁ።”+ 15 እስራኤላውያን ግን ይሖዋን “ኃጢአት ሠርተናል። መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግብን። እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። 16 እነሱም ከመካከላቸው ባዕዳን አማልክትን አስወግደው ይሖዋን አገለገሉ፤+ በመሆኑም በእስራኤል ላይ እየደረሰ የነበረውን መከራ ሊታገሥ አልቻለም።* +

17 ከጊዜ በኋላም አሞናውያን+ ተሰባስበው በጊልያድ ሰፈሩ። በመሆኑም እስራኤላውያን ተሰባስበው በምጽጳ ሰፈሩ። 18 የጊልያድ ሕዝብና መኳንንት እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ከአሞናውያን ጋር የሚደረገውን ውጊያ ግንባር ቀደም ሆኖ የሚመራው ማን ነው?+ ይህ ሰው በጊልያድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሁን።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ