የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢዮዓቄም ዓመፀ፤ በኋላም ሞተ (1-7)

      • ዮአኪን በይሁዳ ላይ ነገሠ (8, 9)

      • ለመጀመሪያ ጊዜ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰዱ (10-17)

      • ሴዴቅያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ እንዲሁም ዓመፀ (18-20)

2 ነገሥት 24:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:1፤ 46:2፤ ዳን 1:1፤ 3:1፤ 4:33

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የዳንኤል ትንቢት፣ ገጽ 31-32

2 ነገሥት 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕን 1:6
  • +ዘሌ 26:27, 28፤ ዘዳ 28:15፤ 2ነገ 23:27

2 ነገሥት 24:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 4:26
  • +2ነገ 21:11፤ 23:26

2 ነገሥት 24:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:16፤ ኤር 2:34፤ 19:4
  • +ኤር 15:1፤ ሰቆ 3:42

2 ነገሥት 24:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:8

2 ነገሥት 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 22:18, 19፤ 36:30

2 ነገሥት 24:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 5
  • +ዘፍ 15:18፤ 1ነገ 4:21
  • +ኤር 46:2

2 ነገሥት 24:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 24:1፤ 37:1
  • +2ዜና 36:8

2 ነገሥት 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 1:1

2 ነገሥት 24:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    11/2007፣ ገጽ 16

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 6

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 48

2 ነገሥት 24:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 29:1, 2
  • +2ዜና 36:9, 10፤ ኤር 24:1፤ ሕዝ 17:12
  • +ኤር 52:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 48

2 ነገሥት 24:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 20:13, 17
  • +1ነገ 7:48-50፤ ዕዝራ 1:7፤ ዳን 5:2

2 ነገሥት 24:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ምሽግ የሚገነቡ ሰዎችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 1:3, 6
  • +ኤር 24:1
  • +2ነገ 25:12

2 ነገሥት 24:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:27፤ 1ዜና 3:17
  • +ኤር 22:24, 25

2 ነገሥት 24:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ምሽግ የሚገነቡ ሰዎችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

2 ነገሥት 24:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 3:15
  • +2ዜና 36:10-12፤ ኤር 37:1፤ 52:1

2 ነገሥት 24:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:31

2 ነገሥት 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:36, 37፤ ኤር 24:8፤ 37:1, 2፤ 38:5, 6፤ ሕዝ 21:25

2 ነገሥት 24:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:27
  • +2ዜና 36:11, 13፤ ኤር 27:12፤ 38:17፤ ሕዝ 17:12-15

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 24:1ኤር 25:1፤ 46:2፤ ዳን 1:1፤ 3:1፤ 4:33
2 ነገ. 24:2ዕን 1:6
2 ነገ. 24:2ዘሌ 26:27, 28፤ ዘዳ 28:15፤ 2ነገ 23:27
2 ነገ. 24:3ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 4:26
2 ነገ. 24:32ነገ 21:11፤ 23:26
2 ነገ. 24:42ነገ 21:16፤ ኤር 2:34፤ 19:4
2 ነገ. 24:4ኤር 15:1፤ ሰቆ 3:42
2 ነገ. 24:52ዜና 36:8
2 ነገ. 24:6ኤር 22:18, 19፤ 36:30
2 ነገ. 24:7ዘኁ 34:2, 5
2 ነገ. 24:7ዘፍ 15:18፤ 1ነገ 4:21
2 ነገ. 24:7ኤር 46:2
2 ነገ. 24:8ኤር 24:1፤ 37:1
2 ነገ. 24:82ዜና 36:8
2 ነገ. 24:10ዳን 1:1
2 ነገ. 24:12ኤር 29:1, 2
2 ነገ. 24:122ዜና 36:9, 10፤ ኤር 24:1፤ ሕዝ 17:12
2 ነገ. 24:12ኤር 52:28
2 ነገ. 24:132ነገ 20:13, 17
2 ነገ. 24:131ነገ 7:48-50፤ ዕዝራ 1:7፤ ዳን 5:2
2 ነገ. 24:14ዳን 1:3, 6
2 ነገ. 24:14ኤር 24:1
2 ነገ. 24:142ነገ 25:12
2 ነገ. 24:152ነገ 25:27፤ 1ዜና 3:17
2 ነገ. 24:15ኤር 22:24, 25
2 ነገ. 24:171ዜና 3:15
2 ነገ. 24:172ዜና 36:10-12፤ ኤር 37:1፤ 52:1
2 ነገ. 24:182ነገ 23:31
2 ነገ. 24:192ነገ 23:36, 37፤ ኤር 24:8፤ 37:1, 2፤ 38:5, 6፤ ሕዝ 21:25
2 ነገ. 24:202ነገ 23:27
2 ነገ. 24:202ዜና 36:11, 13፤ ኤር 27:12፤ 38:17፤ ሕዝ 17:12-15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 24:1-20

ሁለተኛ ነገሥት

24 በኢዮዓቄም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮዓቄምም ለሦስት ዓመት የእሱ አገልጋይ ሆነ። ሆኖም ሐሳቡን ለውጦ ዓመፀበት። 2 ከዚያም ይሖዋ የከለዳውያንን፣+ የሶርያውያንን፣ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ወራሪ ቡድኖች ይልክበት ጀመር። ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት+ ይሁዳን እንዲያጠፉ እነዚህን ቡድኖች ይልክባቸው ነበር። 3 ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤+ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤+ 4 ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤+ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።+

5 የቀረው የኢዮዓቄም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ 6 በመጨረሻም ኢዮዓቄም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ዮአኪን ነገሠ።

7 የባቢሎን ንጉሥ ከግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ አንስቶ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ የሚገኘውን የግብፅን ንጉሥ+ ምድር ሁሉ ወስዶ ስለነበር የግብፅ ንጉሥ ዳግመኛ ከምድሩ ለመውጣት አልደፈረም።

8 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ።+ እናቱ ነሁሽታ ትባል ነበር፤ እሷም የኢየሩሳሌም ሰው የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች። 9 አባቱ እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። 10 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነጾር አገልጋዮች በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ከተማዋም ተከበበች።+ 11 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹ ከተማዋን ከበው ሳሉ ወደ ከተማዋ መጣ።

12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ 13 ከዚያም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።+ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ የሠራቸውን የወርቅ ዕቃዎች በሙሉ ሰባበራቸው።+ ይህ የሆነው ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው። 14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+ 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ። 16 ደግሞም የባቢሎን ንጉሥ ኃያላን የሆኑና ለጦርነት የሠለጠኑ ወንዶችን በሙሉ ይኸውም 7,000 ተዋጊዎችን እንዲሁም 1,000 የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን* ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ። 17 ከዚያም የዮአኪንን አጎት ማታንያህን+ በእሱ ምትክ አነገሠው፤ ስሙንም ቀይሮ ሴዴቅያስ+ አለው።

18 ሴዴቅያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እናቱ ሀሙጣል ትባል ነበር፤+ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። 19 ኢዮዓቄም እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 20 እነዚህ ነገሮች በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የተፈጸሙት ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ነው፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዓመፀ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ