የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለሱ ቃል ተገባላቸው (1-13)

      • ‘በጻድቁ ቀንበጥ’ ሥር ያለስጋት መኖር (14-16)

      • ከዳዊትና ከካህናቱ ጋር የተገባ ቃል ኪዳን (17-26)

        • የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳን (20)

ኤርምያስ 33:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 3:25፤ ኤር 32:2፤ 37:21፤ 38:28

ኤርምያስ 33:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው፣ ርዕስ 55

ኤርምያስ 33:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:52፤ ኤር 32:24

ኤርምያስ 33:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:26፤ ኤር 30:17
  • +ኢሳ 54:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/1996፣ ገጽ 8-9, 18

ኤርምያስ 33:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:3፤ ኤር 30:3
  • +ኤር 24:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/1996፣ ገጽ 9

ኤርምያስ 33:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:2፤ ዘካ 13:1
  • +መዝ 85:2፤ ኢሳ 43:25፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2017፣ ገጽ 1

ኤርምያስ 33:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 62:3, 7
  • +ነህ 6:15, 16፤ ሚክ 7:17

ኤርምያስ 33:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:12
  • +ዘካ 9:17
  • +2ዜና 5:13፤ ዕዝራ 3:11፤ መዝ 106:1፤ ኢሳ 12:4፤ ሚክ 7:18
  • +ዘሌ 7:12፤ መዝ 107:22

ኤርምያስ 33:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 65:10፤ ኤር 32:43

ኤርምያስ 33:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:26
  • +ኤር 32:44

ኤርምያስ 33:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 29:10

ኤርምያስ 33:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወራሽ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:2፤ ዘካ 6:12፤ ራእይ 22:16
  • +ኢሳ 11:1, 4፤ ኤር 23:5፤ ዕብ 1:9

ኤርምያስ 33:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:17
  • +ሕዝ 28:26
  • +ኤር 23:6

ኤርምያስ 33:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:16, 17፤ 1ነገ 2:4፤ መዝ 89:20, 29፤ ኢሳ 9:7፤ ሉቃስ 1:32, 33

ኤርምያስ 33:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:16፤ ኢሳ 54:10፤ ኤር 31:35-37

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2019፣ ገጽ 26

    “የሰላሙ መስፍን“፣ ገጽ 98-99

ኤርምያስ 33:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:16, 17፤ 23:5፤ መዝ 89:34, 35፤ 132:11፤ ኢሳ 55:3
  • +ኢሳ 9:6፤ ሉቃስ 1:32, 33
  • +ዘዳ 21:5

ኤርምያስ 33:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 11

ኤርምያስ 33:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደንብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:16
  • +መዝ 104:19፤ ኤር 31:35, 36

ኤርምያስ 33:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዘሮች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 2:1, 70
  • +ኢሳ 14:1፤ ኤር 31:20

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 33:1ነህ 3:25፤ ኤር 32:2፤ 37:21፤ 38:28
ኤር. 33:3ኢሳ 48:6
ኤር. 33:4ዘዳ 28:52፤ ኤር 32:24
ኤር. 33:6ኢሳ 30:26፤ ኤር 30:17
ኤር. 33:6ኢሳ 54:13
ኤር. 33:7ዘዳ 30:3፤ ኤር 30:3
ኤር. 33:7ኤር 24:6
ኤር. 33:8ኢሳ 40:2፤ ዘካ 13:1
ኤር. 33:8መዝ 85:2፤ ኢሳ 43:25፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:18
ኤር. 33:9ኢሳ 62:3, 7
ኤር. 33:9ነህ 6:15, 16፤ ሚክ 7:17
ኤር. 33:11ኤር 31:12
ኤር. 33:11ዘካ 9:17
ኤር. 33:112ዜና 5:13፤ ዕዝራ 3:11፤ መዝ 106:1፤ ኢሳ 12:4፤ ሚክ 7:18
ኤር. 33:11ዘሌ 7:12፤ መዝ 107:22
ኤር. 33:12ኢሳ 65:10፤ ኤር 32:43
ኤር. 33:13ኤር 17:26
ኤር. 33:13ኤር 32:44
ኤር. 33:14ኤር 29:10
ኤር. 33:15ኢሳ 53:2፤ ዘካ 6:12፤ ራእይ 22:16
ኤር. 33:15ኢሳ 11:1, 4፤ ኤር 23:5፤ ዕብ 1:9
ኤር. 33:16ኢሳ 45:17
ኤር. 33:16ሕዝ 28:26
ኤር. 33:16ኤር 23:6
ኤር. 33:172ሳሙ 7:16, 17፤ 1ነገ 2:4፤ መዝ 89:20, 29፤ ኢሳ 9:7፤ ሉቃስ 1:32, 33
ኤር. 33:20ዘፍ 1:16፤ ኢሳ 54:10፤ ኤር 31:35-37
ኤር. 33:212ሳሙ 7:16, 17፤ 23:5፤ መዝ 89:34, 35፤ 132:11፤ ኢሳ 55:3
ኤር. 33:21ኢሳ 9:6፤ ሉቃስ 1:32, 33
ኤር. 33:21ዘዳ 21:5
ኤር. 33:25ዘፍ 1:16
ኤር. 33:25መዝ 104:19፤ ኤር 31:35, 36
ኤር. 33:26ዕዝራ 2:1, 70
ኤር. 33:26ኢሳ 14:1፤ ኤር 31:20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 33:1-26

ኤርምያስ

33 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ሳለ የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 2 “ምድርን የሠራት ይሖዋ፣ አዎ፣ ያበጃትና አጽንቶ የመሠረታት ይሖዋ እንዲህ ይላል፤ ስሙ ይሖዋ ነው፤ 3 ‘ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተ የማታውቀውን ታላቅና ለመረዳት አዳጋች የሆነ ነገር ወዲያውኑ እነግርሃለሁ።’”+

4 “እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ በዙሪያዋ በተደለደለው የአፈር ቁልልና በሰይፍ የተነሳ ስለፈረሱት የዚህች ከተማ ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንዲህ እላለሁ፤+ 5 ደግሞም ከከለዳውያን ጋር ሊዋጉ የሚመጡትን ሰዎች እንዲሁም ከክፋታቸው የተነሳ ፊቴን ከዚህች ከተማ እንድሰውር ባደረጉኝና በታላቅ ቁጣዬ በመታኋቸው ሰዎች ሬሳ የሚሞሉትን ቦታዎች በተመለከተ እንዲህ እላለሁ፦ 6 ‘እነሆ፣ ከተማዋ እንድታገግም አደርጋለሁ፤ ጤናም እሰጣታለሁ፤+ እኔም እፈውሳቸዋለሁ እንዲሁም የተትረፈረፈ ሰላምና እውነት እሰጣቸዋለሁ።+ 7 ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤+ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ።+ 8 እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤+ በእኔ ላይ የሠሩትን ኃጢአትና በደል ሁሉ ይቅር እላለሁ።+ 9 እሷም የማደርግላቸውን መልካም ነገር በሙሉ በሚሰሙ የምድር ብሔራት ሁሉ ፊት የሐሴት ስም፣ ውዳሴና ውበት ትሆንልኛለች።+ በማደርግላት መልካም ነገር ሁሉና በምሰጣት ሰላም ሁሉ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’”+

10 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ 11 አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣+ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!”+ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’

“‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይዘው ይመጣሉ’+ ይላል ይሖዋ።”

12 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰው ወይም ከብት በሌለበት በዚህ ጠፍ መሬት እንዲሁም በከተሞቹ ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የግጦሽ መሬት ዳግመኛ ያገኛሉ።’+

13 “‘በተራራማው ምድር በሚገኙ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ በሚገኙ ከተሞች፣ በደቡብ ባሉ ከተሞች፣ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎችና+ በይሁዳ ከተሞች፣+ እረኞች በጎቻቸውን የሚቆጥሩበት ጊዜ ዳግመኛ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”

14 “‘እነሆ፣ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።+ 15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+ 16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+

17 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከዳዊት ዘር፣ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤+ 18 ከሌዋውያን ካህናትም መካከል ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ፣ የእህል መባዎችን ለማቃጠልና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በፊቴ የሚቆም ሰው ጨርሶ አይታጣም።’”

19 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 20 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ፣ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ የምትችሉ ከሆነ፣+ 21 ያን ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ ሊፈርስ ይችላል፤+ ያን ጊዜ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ አይኖረውም፤+ አገልጋዮቼ ከሆኑት ከሌዋውያን ካህናት+ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ይፈርሳል። 22 የሰማያት ሠራዊት ሊቆጠር፣ የባሕርም አሸዋ ሊሰፈር እንደማይችል ሁሉ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና አገልጋዮቼን ሌዋውያንን እንዲሁ አበዛቸዋለሁ።’”

23 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 24 “እነዚህ ሰዎች፣ ‘ይሖዋ የመረጣቸውን ሁለቱን ወገኖች ይተዋቸዋል’ እንደሚሉ አላስተዋልክም? የገዛ ሕዝቤንም ይንቃሉ፤ እነሱን እንደ ብሔር አድርገው መመልከት አቁመዋል።

25 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማቋቋሜ+ እንዲሁም የሰማይንና የምድርን ሕግ* መደንገጌ የተረጋገጠ እንደሆነ ሁሉ፣+ 26 በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ልጆች* ላይ የሚነግሡ ገዢዎች ከዘሩ እንዳይታጡ የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር ፈጽሞ አልጥልም። ተማርከው የተወሰዱባቸውን መልሼ እሰበስባለሁና፤+ ርኅራኄም አሳያቸዋለሁ።’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ