የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 36
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤርምያስ ባሮክን በቃሉ አስጻፈው (1-7)

      • ባሮክ ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብሎ አነበበ (8-19)

      • ኢዮዓቄም ጥቅልሉን አቃጠለው (20-26)

      • መልእክቱ በአዲስ ጥቅልል ላይ በድጋሚ ተጻፈ (27-32)

ኤርምያስ 36:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:36፤ ኤር 25:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 17

ኤርምያስ 36:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የመጽሐፍ ጥቅልል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:1, 2፤ 25:3
  • +ኤር 1:5፤ 25:9
  • +ኤር 4:16፤ 32:30

ኤርምያስ 36:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 55:7፤ ሕዝ 33:11፤ ሚክ 7:18

ኤርምያስ 36:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በመጽሐፍ ጥቅልሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 32:12፤ 45:2-5
  • +ኤር 45:1

ኤርምያስ 36:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 17

ኤርምያስ 36:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከመጽሐፉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:1, 2

ኤርምያስ 36:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:36
  • +2ዜና 20:2, 3፤ አስ 4:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 17

ኤርምያስ 36:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጸሐፊ።”

  • *

    ወይም “የመመገቢያ ክፍል።”

  • *

    ወይም “ከመጽሐፉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:10
  • +2ነገ 22:8፤ 2ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24፤ 39:13, 14፤ ሕዝ 8:11
  • +ኤር 36:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 16-17

ኤርምያስ 36:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከመጽሐፉ።”

ኤርምያስ 36:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:20
  • +2ነገ 22:14፤ ኤር 26:22
  • +ኤር 36:25

ኤርምያስ 36:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከመጽሐፉ።”

ኤርምያስ 36:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመጽሐፉ።”

ኤርምያስ 36:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:26

ኤርምያስ 36:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:14

ኤርምያስ 36:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከኅዳር አጋማሽ እስከ ታኅሣሥ አጋማሽ ያለውን ጊዜ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ15ን ተመልከት።

ኤርምያስ 36:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:8
  • +ኤር 36:12
  • +ኤር 36:10

ኤርምያስ 36:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:19

ኤርምያስ 36:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:2

ኤርምያስ 36:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:23

ኤርምያስ 36:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:8, 9

ኤርምያስ 36:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:6, 8, 15፤ 2ዜና 36:9, 10፤ ኤር 22:24, 30
  • +ኤር 22:18, 19

ኤርምያስ 36:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዘሩንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15፤ ኤር 19:15
  • +2ዜና 36:15, 16

ኤርምያስ 36:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መጽሐፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:2, 4
  • +ኤር 36:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2017፣ ገጽ 2

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 16

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 36:12ነገ 23:36፤ ኤር 25:1
ኤር. 36:2ኤር 1:1, 2፤ 25:3
ኤር. 36:2ኤር 1:5፤ 25:9
ኤር. 36:2ኤር 4:16፤ 32:30
ኤር. 36:3ኢሳ 55:7፤ ሕዝ 33:11፤ ሚክ 7:18
ኤር. 36:4ኤር 32:12፤ 45:2-5
ኤር. 36:4ኤር 45:1
ኤር. 36:8ኤር 7:1, 2
ኤር. 36:92ነገ 23:36
ኤር. 36:92ዜና 20:2, 3፤ አስ 4:15, 16
ኤር. 36:10ኤር 26:10
ኤር. 36:102ነገ 22:8፤ 2ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24፤ 39:13, 14፤ ሕዝ 8:11
ኤር. 36:10ኤር 36:25
ኤር. 36:12ኤር 36:20
ኤር. 36:122ነገ 22:14፤ ኤር 26:22
ኤር. 36:12ኤር 36:25
ኤር. 36:19ኤር 36:26
ኤር. 36:21ኤር 36:14
ኤር. 36:252ነገ 24:8
ኤር. 36:25ኤር 36:12
ኤር. 36:25ኤር 36:10
ኤር. 36:26ኤር 1:19
ኤር. 36:27ኤር 36:2
ኤር. 36:28ኤር 36:23
ኤር. 36:29ኤር 25:8, 9
ኤር. 36:302ነገ 24:6, 8, 15፤ 2ዜና 36:9, 10፤ ኤር 22:24, 30
ኤር. 36:30ኤር 22:18, 19
ኤር. 36:31ዘዳ 28:15፤ ኤር 19:15
ኤር. 36:312ዜና 36:15, 16
ኤር. 36:32ኤር 36:2, 4
ኤር. 36:32ኤር 36:23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 36:1-32

ኤርምያስ

36 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 2 “አንድ ጥቅልል* ውሰድና በኢዮስያስ ዘመን ለአንተ መናገር ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ+ በእስራኤል፣ በይሁዳና በብሔራት ሁሉ+ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የነገርኩህን ቃል በሙሉ ጻፍበት።+ 3 ምናልባት የይሁዳ ቤት ሰዎች በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”+

4 ከዚያም ኤርምያስ የነሪያህን ልጅ ባሮክን+ ጠራው፤ ይሖዋ የነገረውንም ቃል ሁሉ በቃሉ አስጻፈው፤ ባሮክም በጥቅልሉ* ላይ ጻፈው።+ 5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ታግጃለሁ፤ ወደ ይሖዋ ቤትም መግባት አልችልም። 6 ስለዚህ ገብተህ እኔ ያስጻፍኩህን የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብለህ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ። በጾም ቀን በይሖዋ ቤት የተሰበሰቡ ሰዎች እየሰሙ አንብበው፤ በዚህ መንገድ፣ ከየከተሞቻቸው ለመጡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ታነብላቸዋለህ። 7 ምናልባት ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡት ልመና ወደ ይሖዋ ሊደርስና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ሊመለሱ ይችላሉ፤ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣና መዓት ታላቅ ነውና።”

8 በመሆኑም የነሪያህ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ በይሖዋ ቤት የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ ጮክ ብሎ አነበበ።+

9 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአምስተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም ያለው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሕዝብ ሁሉ በይሖዋ ፊት ጾም አወጀ።+ 10 ከዚያም ባሮክ በይሖዋ ቤት በላይኛው ግቢ ይኸውም በይሖዋ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ+ አጠገብ ባለው፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በሳፋን+ ልጅ በገማርያህ+ ክፍል* ሕዝቡ ሁሉ እየሰማ የኤርምያስን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ አነበበ።

11 የሳፋን ልጅ፣ የገማርያህ ልጅ ሚካያህ ከጥቅልሉ* ላይ የተነበበውን የይሖዋን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ 12 ወደ ንጉሡ ቤት፣* ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። መኳንንቱ* ሁሉ ይኸውም ጸሐፊው ኤሊሻማ፣+ የሸማያህ ልጅ ደላያህ፣ የአክቦር+ ልጅ ኤልናታን፣+ የሳፋን ልጅ ገማርያህ፣ የሃናንያህ ልጅ ሴዴቅያስና ሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር። 13 ሚካያህ፣ ባሮክ ሕዝቡ እየሰማ ከጥቅልሉ* ላይ ሲያነብ ያዳመጠውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።

14 በዚህ ጊዜ መኳንንቱ ሁሉ የኩሺ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ የሆነውን የሁዲን “ሕዝቡ እየሰማህ ያነበብከውን ጥቅልል ይዘህ ና” ብሎ እንዲነግረው ወደ ባሮክ ላኩት። የነሪያህ ልጅ ባሮክም ጥቅልሉን ይዞ ወደ እነሱ ሄደ። 15 እነሱም “እባክህ ተቀመጥና ጥቅልሉን ጮክ ብለህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው።

16 እነሱም ቃሉን ሁሉ እንደሰሙ በፍርሃት ተውጠው እርስ በርስ ተያዩ፤ ከዚያም ባሮክን “ይህን ቃል ሁሉ ለንጉሡ ልንነግረው ይገባል” አሉት። 17 ደግሞም ባሮክን “ይህን ሁሉ ቃል የጻፍከው እንዴት እንደሆነ እስቲ ንገረን። በቃሉ ነው ያስጻፈህ?” ብለው ጠየቁት። 18 ባሮክም “ይህን ሁሉ በቃሉ አስጻፈኝ፤ እኔም በጥቅልሉ* ላይ በቀለም ጻፍኩት” ብሎ መለሰላቸው። 19 መኳንንቱ ባሮክን “ሂድ፣ አንተና ኤርምያስ ተደበቁ፤ ያላችሁበትንም ማንም ሰው አይወቅ” አሉት።+

20 ከዚያም ንጉሡ ወደሚገኝበት ግቢ ሄዱ፤ ጥቅልሉንም በጸሐፊው በኤሊሻማ ክፍል አስቀመጡት፤ የሰሙትንም ነገር ሁሉ ለንጉሡ ነገሩት።

21 ንጉሡም ጥቅልሉን እንዲያመጣ የሁዲን+ ላከው፤ እሱም ጥቅልሉን ከጸሐፊው ከኤሊሻማ ክፍል ይዞት መጣ። የሁዲም ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ ቆመው የነበሩት መኳንንት ሁሉ እየሰሙ ያነበው ጀመር። 22 ንጉሡ በዘጠነኛው ወር* የክረምቱን ወቅት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም በምድጃ የሚነድ እሳት ነበር። 23 የሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ካነበበ በኋላ ንጉሡ የተነበበውን ክፍል በጸሐፊ ቢላ እየቀደደ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይወረውረው ነበር፤ ጥቅልሉ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ድረስ እንዲሁ አደረገ። 24 ይህን ሁሉ ቃል ሲሰሙ የነበሩት ንጉሡም ሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ ምንም ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። 25 ኤልናታን፣+ ደላያህና+ ገማርያህ+ ንጉሡ ጥቅልሉን እንዳያቃጥለው ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም። 26 በተጨማሪም ንጉሡ ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን እንዲይዟቸው የንጉሡን ልጅ የራህምኤልን፣ የአዝርዔልን ልጅ ሰራያህንና የአብድዔልን ልጅ ሸሌምያህን አዘዘ፤ ይሖዋ ግን ሰውሯቸው ነበር።+

27 ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየሰማ የጻፈውን ቃል የያዘውን ጥቅልል+ ካቃጠለው በኋላ የይሖዋ ቃል እንደገና እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 28 “ሌላ ጥቅልል ውሰድና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ጥቅልል+ ላይ የነበረውን ያንኑ ቃል ሁሉ ጻፍበት። 29 የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል፤ ደግሞም ‘“የባቢሎን ንጉሥ ያላንዳች ጥርጥር መጥቶ ይህችን ምድር ያወድማል፤ ሰውንና እንስሳንም ከምድሪቱ ላይ ያጠፋል” ብለህ በጥቅልሉ ላይ የጻፍከው ለምንድን ነው?’ ብለሃል።+ 30 ስለዚህ ይሖዋ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም ላይ እንዲህ ይላል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይኖረውም፤+ ሬሳውም የቀን ሐሩርና የሌሊት ቁር ይፈራረቅበታል።+ 31 እሱን፣ ልጆቹንና* አገልጋዮቹን ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤ ደግሞም በእነሱ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና በይሁዳ ሰዎች ላይ አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤+ እነሱ ግን አልሰሙም።’”’”+

32 ከዚያም ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወስዶ ለነሪያህ ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤+ እሱም ኤርምያስ በቃል እያስጻፈው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በእሳት ባቃጠለው ጥቅልል*+ ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፈበት። ደግሞም ከዚያ ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ