ኤርምያስ
14 ድርቅን አስመልክቶ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+
2 ይሁዳ ታለቅሳለች፤+ በሮቿም ወላልቀዋል።
በሐዘን ተውጠው መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤
ከኢየሩሳሌምም ጩኸት ይሰማል።
3 ጌቶቻቸውም አገልጋዮቻቸውን* ውኃ እንዲፈልጉ ላኳቸው።
እነሱም ወደ ውኃ ጉድጓዶቹ* ሄዱ፤ ውኃ ግን አላገኙም።
ባዶ ዕቃ ይዘው ተመለሱ።
በኀፍረት ተዋጡ፤ ተስፋም ቆረጡ፤
ራሳቸውንም ተከናነቡ።
5 በሜዳ ያለች እንስት ርኤም* እንኳ
ምንም ሣር ባለመኖሩ እንደወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።
6 የዱር አህዮች በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ይቆማሉ።
እንደ ቀበሮ አየር አጥሯቸው ያለከልካሉ፤
ምንም ዓይነት ተክል ባለመኖሩ ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።+
7 ይሖዋ ሆይ፣ የገዛ ራሳችን በደል በእኛ ላይ የሚመሠክርብን ቢሆንም
ለስምህ ስትል እርምጃ ውሰድ።+
የክህደት ሥራችን በዝቷልና፤+
ኃጢአት የሠራነውም በአንተ ላይ ነው።
8 አንተ የእስራኤል ተስፋ፣ በጭንቀትም ጊዜ አዳኙ+ የሆንክ ሆይ፣
በምድሪቱ እንደ እንግዳ፣
ሌሊቱን ለማሳለፍ ሲል ብቻ ጎራ እንዳለ መንገደኛ የሆንከው ለምንድን ነው?
9 ክው ብሎ እንደቀረ ሰው፣
ማዳን እንደማይችል ኃያል ሰው የሆንከው ለምንድን ነው?
እባክህ አትተወን።
10 ይሖዋ ይህን ሕዝብ አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “መቅበዝበዝ ይወዳሉ፤+ እግራቸውን አልሰበሰቡም።+ ስለዚህ ይሖዋ በእነሱ ደስ አይሰኝም።+ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።”+
11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ሕዝብ መልካም ሁኔታ እንዲገጥመው አትጸልይ።+ 12 በሚጾሙበት ጊዜ የሚያቀርቡትን ልመና አልሰማም፤+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የእህል መባዎች በሚያቀርቡበት ጊዜም በእነሱ ደስ አልሰኝም፤+ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* አጠፋቸዋለሁና።”+
13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”+
14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+ 15 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ሳልካቸው በስሜ የሚተነብዩትና በዚህች ምድር ላይ ሰይፍም ሆነ ረሃብ አይከሰትም የሚሉት እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ።+ 16 የሚተነብዩለትም ሕዝብ ከረሃቡና ከሰይፉ የተነሳ አስከሬኑ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ይጣላል፤ እነሱን፣ አዎ እነሱን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይኖርም፤+ የሚገባቸውን ጥፋት በላያቸው ላይ አመጣለሁና።’+
17 “ይህን ቃል ንገራቸው፦
‘ዓይኖቼ ሌት ተቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ፤+
ድንግሊቱ የሕዝቤ ሴት ልጅ እጅግ አስከፊ በሆነ ቁስል ሙሉ በሙሉ ደቃለችና፤
ደግሞም ተሰብራለች።+
18 ወደ መስክ ብወጣ፣
እነሆ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ!+
ወደ ከተማም ብገባ፣
በረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎችን አያለሁ!+
ነቢዩና ካህኑ በማያውቁት አገር ተቅበዝብዘዋልና።’”+
19 ይሁዳን ጨርሶ ትተኸዋል? ወይስ ጽዮንን ተጸይፈሃታል?*+
ታዲያ ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ የመታኸን ለምንድን ነው?+
ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤
የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+
21 ስለ ስምህ ስትል አትናቀን፤+
ክብር የተላበሰውን ዙፋንህን አታቃልል።
ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስታውስ፤ አታፍርሰውም።+
22 ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?
ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ?
አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም?+
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክ
አንተን ተስፋ እናደርጋለን።