የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለንጉሥ አካዝ የተላከ መልእክት (1-9)

        • ሸአርያሹብ (3)

      • አማኑኤልን በተመለከተ የተሰጠ ምልክት (10-17)

      • ከዳተኛ መሆን የሚያስከትለው መዘዝ (18-25)

ኢሳይያስ 7:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እነሱ ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:1, 2
  • +2ነገ 15:37፤ 2ዜና 28:6
  • +2ነገ 16:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 101-102

ኢሳይያስ 7:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 102

ኢሳይያስ 7:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ቀሪዎች ብቻ ይመለሳሉ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:18
  • +2ነገ 18:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 102-104

ኢሳይያስ 7:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:30፤ ኢሳ 8:6, 7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2006፣ ገጽ 9

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 102-104

ኢሳይያስ 7:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2013፣ ገጽ 16

ኢሳይያስ 7:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እናሸብረው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

  • *

    ወይም “ግንቦቹንም እንንደል።” ቃል በቃል “እንሰንጥቀውም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2013፣ ገጽ 16

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 104-105

ኢሳይያስ 7:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 105

ኢሳይያስ 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:6፤ ሆሴዕ 1:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2006፣ ገጽ 9

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 105

ኢሳይያስ 7:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:23, 24
  • +2ነገ 15:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 105-106

ኢሳይያስ 7:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 105-106

ኢሳይያስ 7:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 6:36, 37፤ ኢሳ 37:30፤ 38:7, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 105-106

ኢሳይያስ 7:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 106

ኢሳይያስ 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 107

ኢሳይያስ 7:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ልጃገረዷ።”

  • *

    “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 9:6፤ ዮሐ 1:14፤ 1ጢሞ 3:16
  • +ማቴ 1:23፤ ሉቃስ 1:30-35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 146, 153

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2013፣ ገጽ 16-17

    8/15/2011፣ ገጽ 10

    10/1/2008፣ ገጽ 4-5

    12/15/2003፣ ገጽ 5

    11/15/1994፣ ገጽ 29

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 107-108

ኢሳይያስ 7:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 107

ኢሳይያስ 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:29፤ 16:8, 9፤ ኢሳ 8:3, 4፤ 17:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 107

ኢሳይያስ 7:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:20
  • +2ነገ 18:13, 14፤ 2ዜና 28:19, 20፤ ኢሳ 36:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 108-109

ኢሳይያስ 7:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 109-110

ኢሳይያስ 7:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዞች።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 109-110

ኢሳይያስ 7:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የኤፍራጥስን ወንዝ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 110

ኢሳይያስ 7:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 110

ኢሳይያስ 7:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 110

ኢሳይያስ 7:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 110

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 7:12ነገ 16:1, 2
ኢሳ. 7:12ነገ 15:37፤ 2ዜና 28:6
ኢሳ. 7:12ነገ 16:5
ኢሳ. 7:3ኢሳ 8:18
ኢሳ. 7:32ነገ 18:17
ኢሳ. 7:42ነገ 15:30፤ ኢሳ 8:6, 7
ኢሳ. 7:62ነገ 16:5
ኢሳ. 7:82ነገ 17:6፤ ሆሴዕ 1:6
ኢሳ. 7:91ነገ 16:23, 24
ኢሳ. 7:92ነገ 15:27
ኢሳ. 7:11መሳ 6:36, 37፤ ኢሳ 37:30፤ 38:7, 8
ኢሳ. 7:132ዜና 36:15, 16
ኢሳ. 7:14ኢሳ 9:6፤ ዮሐ 1:14፤ 1ጢሞ 3:16
ኢሳ. 7:14ማቴ 1:23፤ ሉቃስ 1:30-35
ኢሳ. 7:162ነገ 15:29፤ 16:8, 9፤ ኢሳ 8:3, 4፤ 17:1
ኢሳ. 7:171ነገ 12:20
ኢሳ. 7:172ነገ 18:13, 14፤ 2ዜና 28:19, 20፤ ኢሳ 36:1
ኢሳ. 7:202ነገ 16:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 7:1-25

ኢሳይያስ

7 በዖዝያ+ ልጅ፣ በኢዮዓታም ልጅ በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን፣ የሶርያው ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ+ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ እሱ ግን ድል ሊያደርጋት አልቻለም።*+ 2 የዳዊት ቤት፣ “ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ግንባር ፈጥራለች” የሚል ወሬ ደረሰው።

በዚህ ጊዜ የአካዝም ሆነ የሕዝቡ ልብ በነፋስ እንደሚናወጥ የዱር ዛፍ መናወጥ ጀመረ።

3 ከዚያም ይሖዋ ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ አንተና ልጅህ ሸአርያሹብ*+ ከአካዝ ጋር ለመገናኘት ወደ አጣቢው እርሻ በሚወስደው መንገድ አጠገብ ወዳለው ወደ ላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ ጫፍ ውጡ።+ 4 እንዲህም በለው፦ ‘አይዞህ፣ ተረጋጋ። በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱ ሁለት የግንድ ጉማጆች ማለትም በሶርያ ንጉሥ በረጺንና በረማልያህ+ ልጅ ኃይለኛ ቁጣ የተነሳ አትፍራ፤ ልብህም አይደንግጥ። 5 ሶርያ ከኤፍሬምና ከረማልያህ ልጅ ጋር እንዲህ ብላ አሲራብሃለች፦ 6 “በይሁዳ ላይ እንዝመትና እንበታትነው፤* በቁጥጥራችንም ሥር እናውለው፤* የታብኤልንም ልጅ እናንግሥበት።”+

7 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ይህ ሴራ አይሳካም፤

ደግሞም አይፈጸምም።

 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፣

የደማስቆ ራስ ደግሞ ረጺን ነውና።

ኤፍሬም በ65 ዓመት ውስጥ

ብትንትኑ ወጥቶ ሕዝብ መሆኑ ይቀራል።+

 9 የኤፍሬም ራስ ሰማርያ+ ነው፤

የሰማርያም ራስ የረማልያህ ልጅ ነው።+

ጠንካራ እምነት ከሌላችሁ

ጸንታችሁ መቆም አትችሉም።”’”

10 ከዚያም ይሖዋ አካዝን እንዲህ አለው፦ 11 “አምላክህ ይሖዋ ምልክት እንዲያሳይህ ጠይቅ፤+ ምልክቱም እንደ መቃብር* ጥልቅ የሆነ ወይም እንደ ሰማይ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።” 12 አካዝ ግን “አልጠይቅም፤ ይሖዋንም አልፈትንም” አለ።

13 ከዚያም ኢሳይያስ እንዲህ አለ፦ “የዳዊት ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ። የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላክንም ትዕግሥት ልትፈታተኑ ትፈልጋላችሁ?+ 14 በመሆኑም ይሖዋ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፦ እነሆ፣ ወጣቷ* ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤+ አማኑኤል* ብላም ትጠራዋለች።+ 15 ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ በሚችልበት ጊዜ ቅቤና ማር ይበላል። 16 ልጁ ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት በጣም የምትፈራቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ጨርሶ የተተወ ይሆናል።+ 17 ይሖዋ፣ ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት+ ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የአሦርን ንጉሥ ያመጣልና።+

18 “በዚያ ቀን ይሖዋ በግብፅ፣ ርቀው በሚገኙት የአባይ ጅረቶች ያሉትን ዝንቦች፣ በአሦርም ምድር ያሉትን ንቦች በፉጨት ይጠራል፤ 19 ሁሉም መጥተው ጥልቅ በሆኑ ሸለቆዎች፣* በየዓለቱ ንቃቃት፣ በቁጥቋጦዎች ሁሉና ውኃ ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።

20 “በዚያም ቀን ይሖዋ በወንዙ* አካባቢ ከሚገኘው ቦታ በተከራየው ምላጭ ይኸውም በአሦር ንጉሥ+ አማካኝነት ራሱንና የእግሩን ፀጉር ይላጨዋል፤ ጢሙንም ሙልጭ አድርጎ ያስወግደዋል።

21 “በዚያም ቀን አንድ ሰው ከመንጋው መካከል አንዲት ጊደርና ሁለት በጎች በሕይወት ያተርፋል። 22 በብዛት ከሚገኘው ወተት የተነሳም ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱ መካከል የቀረው ሰው ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።

23 “በዚያ ቀን 1,000 የብር ሰቅል የሚያወጣ 1,000 የወይን ተክል ይገኝበት የነበረው ቦታ ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ይወርሰዋል። 24 ምድሪቱ በቁጥቋጦና በአረም ስለምትሸፈን ሰዎች ወደዚያ የሚሄዱት ቀስትና ደጋን ይዘው ነው። 25 በአንድ ወቅት በመቆፈሪያ ተመንጥረውና ከአረም ጸድተው የነበሩ ተራሮች ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ስለሚወርሳቸው ወደዚያ መሄድ ትፈራለህ፤ እነዚህ ቦታዎች በሬዎች የሚሰማሩባቸውና በጎች የሚፈነጩባቸው ይሆናሉ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ