የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • ለጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ሊከተሉት የሚገባው ሕግ (1-20)

        • ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ መሆን (5-9)

ዘዳግም 20:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:22፤ 31:6፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31

ዘዳግም 20:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 31:6

ዘዳግም 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:14፤ ኢያሱ 23:10

ዘዳግም 20:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 24:5

ዘዳግም 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 7:3
  • +ዘኁ 13:33፤ 14:1-3፤ 32:9፤ ዘዳ 1:28

ዘዳግም 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:19

ዘዳግም 20:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:44, 46፤ ኢያሱ 9:22, 27

ዘዳግም 20:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 14:13
  • +ኢያሱ 22:8

ዘዳግም 20:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 6:17፤ 10:28፤ 11:11

ዘዳግም 20:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:1

ዘዳግም 20:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:15፤ ዘዳ 7:4፤ ኢያሱ 23:12, 13፤ ኢሳ 2:6፤ 1ቆሮ 5:6፤ 15:33

ዘዳግም 20:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 135

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 20:1ዘዳ 3:22፤ 31:6፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31
ዘዳ. 20:2ዘኁ 31:6
ዘዳ. 20:4ዘፀ 14:14፤ ኢያሱ 23:10
ዘዳ. 20:7ዘዳ 24:5
ዘዳ. 20:8መሳ 7:3
ዘዳ. 20:8ዘኁ 13:33፤ 14:1-3፤ 32:9፤ ዘዳ 1:28
ዘዳ. 20:10ኢያሱ 11:19
ዘዳ. 20:11ዘሌ 25:44, 46፤ ኢያሱ 9:22, 27
ዘዳ. 20:142ዜና 14:13
ዘዳ. 20:14ኢያሱ 22:8
ዘዳ. 20:16ኢያሱ 6:17፤ 10:28፤ 11:11
ዘዳ. 20:17ዘዳ 7:1
ዘዳ. 20:18ዘፀ 34:15፤ ዘዳ 7:4፤ ኢያሱ 23:12, 13፤ ኢሳ 2:6፤ 1ቆሮ 5:6፤ 15:33
ዘዳ. 20:19ነህ 9:25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 20:1-20

ዘዳግም

20 “ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ለመግጠም ብትሄድና ፈረሶቻቸው፣ ሠረገሎቻቸውና ሠራዊታቸው ከአንተ ይልቅ እጅግ ብዙ መሆናቸውን ብታይ አትፍራቸው፤ ምክንያቱም ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው።+ 2 ወደ ውጊያው ለመግባት በምትቀርቡበትም ጊዜ ካህኑ መጥቶ ሕዝቡን ማነጋገር አለበት።+ 3 እንዲህም ይበላቸው፦ ‘እስራኤላውያን ሆይ፣ ስሙ፤ እንግዲህ ዛሬ ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ነው። ልባችሁ አይራድ። በእነሱ ምክንያት አትፍሩ፣ አትሸበሩ ወይም አትንቀጥቀጡ፤ 4 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’+

5 “አለቆቹም ሕዝቡን እንዲህ ይበሉ፦ ‘ከመካከላችሁ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለ? ወደ ቤቱ ይመለስ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ቤቱን ሌላ ሰው ሊያስመርቀው ይችላል። 6 ወይን ተክሎ ገና ከዚያ ያልበላ አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊበላው ይችላል። 7 አንዲት ሴት አጭቶ ገና ያላገባት ሰው አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።+ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊያገባት ይችላል።’ 8 በተጨማሪም አለቆቹ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ይናገሩ፦ ‘ከመካከላችሁ የፈራና ልቡ የራደ አለ?+ ልክ እንደ ራሱ ልብ የወንድሞቹንም ልብ እንዳያቀልጥ+ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።’ 9 አለቆቹም ለሕዝቡ ተናግረው ሲጨርሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሠራዊቱን አለቆች ይሹሙ።

10 “አንዲትን ከተማ ለመውጋት ወደ እሷ ስትቀርብ ለከተማዋ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ።+ 11 ከተማዋ የሰላም ጥሪህን ከተቀበለችና በሯን ከከፈተችልህ ነዋሪዎቿ ሁሉ የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሕዝቦች ይሆኑልሃል፤ አንተንም ያገለግሉሃል።+ 12 ይሁን እንጂ የሰላም ጥሪህን ካልተቀበለችና ከአንተ ጋር ውጊያ ለመግጠም ከተነሳች ከተማዋን ክበባት፤ 13 አምላክህ ይሖዋ ከተማዋን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም በውስጧ የሚኖሩትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው። 14 ሆኖም ሴቶቹን፣ ትናንሽ ልጆቹን፣ እንስሳቱንና በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ነገር ሁሉ ማርከህ ለራስህ መውሰድ ትችላለህ፤+ አምላክህ ይሖዋ በእጅህ አሳልፎ የሰጠህን ከጠላቶችህ ያገኘኸውን ምርኮም ትበላለህ።+

15 “በአቅራቢያህ በሚገኙ በእነዚህ ብሔራት ከተሞች ላይ ሳይሆን ከአንተ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይህንኑ ነው። 16 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።+ 17 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤+ 18 ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው።+

19 “አንዲትን ከተማ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ብትከባትና ለብዙ ቀናት ብትወጋት ዛፎቿን በመጥረቢያ አትጨፍጭፍ። ፍሬያቸውን ልትበላ ትችላለህ፤ ሆኖም አትቁረጣቸው።+ ደግሞስ ሰው ይመስል የሜዳን ዛፍ ከበህ ማጥፋት አለብህ? 20 ለምግብነት እንደማይሆን የምታውቀውን ዛፍ ብቻ ማጥፋት ትችላለህ። ዛፉንም ቆርጠህ ከአንተ ጋር ውጊያ የገጠመችው ከተማ እስክትወድቅ ድረስ ዙሪያዋን ልታጥርበት ትችላለህ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ