የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • በየሰባት ዓመቱ ዕዳ ይሰረዛል (1-6)

      • ድሆችን መርዳት (7-11)

      • በየሰባት ዓመቱ ባሮች ነፃ ይወጣሉ (12-18)

        • የባሪያን ጆሮ በወስፌ መብሳት (16, 17)

      • የእንስሳትን በኩር መቀደስ (19-23)

ዘዳግም 15:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:2

ዘዳግም 15:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2-3

ዘዳግም 15:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:43፤ ዘዳ 14:21፤ 23:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2-3

ዘዳግም 15:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:8

ዘዳግም 15:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 1:7, 8፤ ኢሳ 1:19

ዘዳግም 15:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመያዣ ታበድራለህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:12
  • +ዘዳ 28:13፤ 1ነገ 4:24, 25

ዘዳግም 15:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 21:13፤ ያዕ 2:15, 16፤ 1ዮሐ 3:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2010፣ ገጽ 8

ዘዳግም 15:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመያዣ አበድረው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:35፤ ምሳሌ 19:17፤ ማቴ 5:42፤ ሉቃስ 6:34, 35፤ ገላ 2:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2010፣ ገጽ 8

ዘዳግም 15:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:1
  • +ዘፀ 22:22, 23፤ ዘዳ 24:14, 15፤ ምሳሌ 21:13

ዘዳግም 15:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:35፤ 2ቆሮ 9:7፤ 1ጢሞ 6:18፤ ዕብ 13:16
  • +ዘዳ 24:19፤ መዝ 41:1

ዘዳግም 15:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:11
  • +ምሳሌ 3:27፤ ማቴ 5:42፤ ሉቃስ 12:33

ዘዳግም 15:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:39

ዘዳግም 15:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2014፣ ገጽ 19-20

ዘዳግም 15:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:5, 6

ዘዳግም 15:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በበሬህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:2፤ 22:30፤ ዘኁ 3:13፤ 18:15, 17

ዘዳግም 15:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:5, 6፤ 14:23፤ 16:11

ዘዳግም 15:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:20፤ ዘዳ 17:1፤ ሚል 1:8፤ ዕብ 9:14

ዘዳግም 15:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በደጆችህ።”

  • *

    ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:15፤ 14:4, 5

ዘዳግም 15:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 7:26፤ ሥራ 15:20, 29
  • +ዘሌ 17:10, 13፤ ዘዳ 12:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2000፣ ገጽ 30-31

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 15:1ዘሌ 25:2
ዘዳ. 15:2ዘዳ 31:10
ዘዳ. 15:3ዘፀ 12:43፤ ዘዳ 14:21፤ 23:20
ዘዳ. 15:4ዘዳ 28:8
ዘዳ. 15:5ኢያሱ 1:7, 8፤ ኢሳ 1:19
ዘዳ. 15:6ዘዳ 28:12
ዘዳ. 15:6ዘዳ 28:13፤ 1ነገ 4:24, 25
ዘዳ. 15:7ምሳሌ 21:13፤ ያዕ 2:15, 16፤ 1ዮሐ 3:17
ዘዳ. 15:8ዘሌ 25:35፤ ምሳሌ 19:17፤ ማቴ 5:42፤ ሉቃስ 6:34, 35፤ ገላ 2:10
ዘዳ. 15:9ዘዳ 15:1
ዘዳ. 15:9ዘፀ 22:22, 23፤ ዘዳ 24:14, 15፤ ምሳሌ 21:13
ዘዳ. 15:10ሥራ 20:35፤ 2ቆሮ 9:7፤ 1ጢሞ 6:18፤ ዕብ 13:16
ዘዳ. 15:10ዘዳ 24:19፤ መዝ 41:1
ዘዳ. 15:11ማቴ 26:11
ዘዳ. 15:11ምሳሌ 3:27፤ ማቴ 5:42፤ ሉቃስ 12:33
ዘዳ. 15:12ዘፀ 21:2፤ ዘሌ 25:39
ዘዳ. 15:16ዘፀ 21:5, 6
ዘዳ. 15:19ዘፀ 13:2፤ 22:30፤ ዘኁ 3:13፤ 18:15, 17
ዘዳ. 15:20ዘዳ 12:5, 6፤ 14:23፤ 16:11
ዘዳ. 15:21ዘሌ 22:20፤ ዘዳ 17:1፤ ሚል 1:8፤ ዕብ 9:14
ዘዳ. 15:22ዘዳ 12:15፤ 14:4, 5
ዘዳ. 15:23ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 7:26፤ ሥራ 15:20, 29
ዘዳ. 15:23ዘሌ 17:10, 13፤ ዘዳ 12:16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 15:1-23

ዘዳግም

15 “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ የሌሎችን ዕዳ መሰረዝ ይኖርብሃል።+ 2 ዕዳ የሚሰረዘው በሚከተለው መንገድ ነው፦ እያንዳንዱ አበዳሪ ባልንጀራው ያለበትን ዕዳ ይሰርዝለታል። ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ክፍያ መጠየቅ የለበትም፤ ምክንያቱም ለይሖዋ ሲባል ዕዳ እንዲሰረዝ ይታወጃል።+ 3 ከባዕድ አገር ሰው ክፍያ መጠየቅ ትችላለህ፤+ ወንድምህ ለአንተ መመለስ ያለበትን ማንኛውንም ነገር ግን ተውለት። 4 ይሁንና አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ ይሖዋ ስለሚባርክህ+ ከእናንተ መካከል ማንም ድሃ አይሆንም፤ 5 ይህ የሚሆነው ግን የአምላክህን የይሖዋን ቃል በትኩረት የምትሰማና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በጥንቃቄ የምትፈጽም ከሆነ ነው።+ 6 አምላክህ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ይባርክሃልና፤ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ* እንጂ አትበደርም፤+ ብዙ ብሔራትን ትገዛለህ እንጂ አንተን አይገዙህም።+

7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* 9 ‘ዕዳ የሚሰረዝበት ሰባተኛው ዓመት ቀርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ በልብህ አድሮ ለድሃው ወንድምህ ከመለገስ ወደኋላ እንዳትልና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር ተጠንቀቅ።+ እሱ በአንተ ላይ ቅር ተሰኝቶ ወደ ይሖዋ ቢጮኽ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ 10 በልግስና ስጠው፤+ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው።+ 11 መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና።+ ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።+

12 “ከወንድሞችህ አንዱ ይኸውም አንድ ዕብራዊ ወይም አንዲት ዕብራዊ፣ ለአንተ ቢሸጥና ስድስት ዓመት ቢያገለግልህ በሰባተኛው ዓመት ነፃ አውጣው።+ 13 ነፃ የምታወጣው ከሆነ ባዶ እጁን አትስደደው። 14 ከመንጋህና ከአውድማህ እንዲሁም ከዘይትና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው። አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን ስጠው። 15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።

16 “ሆኖም ይህ ሰው ከአንተ ጋር በነበረበት ጊዜ ደስተኛ ስለነበር አንተንና ቤተሰብህን በመውደድ ‘ፈጽሞ ከአንተ አልለይም!’ ቢልህ+ 17 ጆሮውን በር ላይ አስደግፈህ በወስፌ ብሳው፤ እሱም ዕድሜ ልኩን የአንተ ባሪያ ይሆናል። ሴት ባሪያህንም በተመለከተ እንደዚሁ አድርግ። 18 ባሪያህን ነፃ አድርጎ ማሰናበት ሊከብድህ አይገባም፤ ምክንያቱም እሱ በስድስት ዓመት ውስጥ የሰጠህ አገልግሎት በቅጥር ሠራተኛ ደሞዝ ቢሰላ እጥፍ ዋጋ ያስወጣህ ነበር፤ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ በምትሠራው ነገር ሁሉ ባርኮሃል።

19 “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው።+ በከብትህ* በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት። 20 አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በየዓመቱ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ብሉት።+ 21 ይሁንና እንስሳው እንከን ካለበት ይኸውም አንካሳ ወይም ዕውር ከሆነ አሊያም ሌላ ዓይነት ከባድ ጉድለት ካለበት ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርበው።+ 22 በከተሞችህ* ውስጥ ብላው፤ እንደ ሜዳ ፍየል ወይም እንደ ርኤም* ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል።+ 23 ሆኖም ደሙን አትብላ፤+ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ