የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ቃየንና አቤል (1-16)

      • የቃየን ዘሮች (17-24)

      • ሴትና ልጁ ሄኖስ (25, 26)

ዘፍጥረት 4:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወለድኩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:28
  • +1ዮሐ 3:10-12፤ ይሁዳ 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2013፣ ገጽ 13

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 10-11

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 151

ዘፍጥረት 4:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 23:35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2013፣ ገጽ 13-14

    1/15/2002፣ ገጽ 22

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 11-12

ዘፍጥረት 4:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 16

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2002፣ ገጽ 21

    2/1/1999፣ ገጽ 21

    6/15/1996፣ ገጽ 4-5

ዘፍጥረት 4:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:12
  • +ዕብ 11:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 17-19

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2015፣ ገጽ 20

    1/1/2013፣ ገጽ 14-15

    1/15/2002፣ ገጽ 21

    8/15/2000፣ ገጽ 13-14

    2/1/1999፣ ገጽ 21

    6/15/1996፣ ገጽ 4

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 14

ዘፍጥረት 4:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 16-17

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2013፣ ገጽ 15

    1/15/2002፣ ገጽ 22

    2/1/1999፣ ገጽ 21

    6/15/1996፣ ገጽ 4-5

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 14-16

ዘፍጥረት 4:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/1999፣ ገጽ 21, 23

    1/15/1999፣ ገጽ 21

    6/15/1994፣ ገጽ 14

ዘፍጥረት 4:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሐሴት ታደርግ አልነበረም?”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2014፣ ገጽ 28

    1/15/2002፣ ገጽ 22

    2/1/1999፣ ገጽ 21-23

    1/15/1999፣ ገጽ 21

    6/15/1996፣ ገጽ 4-5

    6/15/1994፣ ገጽ 14

    2/1/1994፣ ገጽ 31

    ንቁ!፣

    10/2011፣ ገጽ 24

ዘፍጥረት 4:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 23:35፤ 1ዮሐ 3:10-12፤ ይሁዳ 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2013፣ ገጽ 15

    9/15/2002፣ ገጽ 28

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 16

ዘፍጥረት 4:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2002፣ ገጽ 22

ዘፍጥረት 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 12:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 6

    በአምላክ ፍቅር ኑሩ፣ ገጽ 90

    ከአምላክ ፍቅር፣ ገጽ 75

    ራእይ፣ ገጽ 101

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2004፣ ገጽ 14

    11/15/1995፣ ገጽ 10

ዘፍጥረት 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:5

ዘፍጥረት 4:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ኃይሏን።”

ዘፍጥረት 4:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከምድር ገጽ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 127

ዘፍጥረት 4:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አበጀለት።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2004፣ ገጽ 29

    1/15/2002፣ ገጽ 22-23

    2/1/1999፣ ገጽ 21-22

ዘፍጥረት 4:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በኖድ ምድር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:8

ዘፍጥረት 4:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 5:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 127

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 10

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2010፣ ገጽ 25

    1/1/2004፣ ገጽ 29

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 90-91

    ማመራመር፣ ገጽ 252-253, 301

ዘፍጥረት 4:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዋሽንት።”

ዘፍጥረት 4:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/2002፣ ገጽ 6

ዘፍጥረት 4:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2020፣ ገጽ 4

ዘፍጥረት 4:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2020፣ ገጽ 4

ዘፍጥረት 4:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የተሾመ፤ የተቀመጠ፤ የተመደበ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:8፤ ማቴ 23:35፤ ዕብ 11:4
  • +ዘፍ 5:3፤ 1ዜና 1:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2009፣ ገጽ 13

ዘፍጥረት 4:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰዎች የይሖዋን ስም ማቃለል ጀመሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 5:6፤ ሉቃስ 3:23, 38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 19

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 1 2017፣ ገጽ 10

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2005፣ ገጽ 15-16

    9/15/2001፣ ገጽ 29

    1/15/1997፣ ገጽ 30

    11/15/1993፣ ገጽ 12-13

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 4:1ዘፍ 1:28
ዘፍ. 4:11ዮሐ 3:10-12፤ ይሁዳ 11
ዘፍ. 4:2ማቴ 23:35
ዘፍ. 4:4ዘፀ 13:12
ዘፍ. 4:4ዕብ 11:4
ዘፍ. 4:8ማቴ 23:35፤ 1ዮሐ 3:10-12፤ ይሁዳ 11
ዘፍ. 4:10ዕብ 12:24
ዘፍ. 4:11ዘፍ 9:5
ዘፍ. 4:16ዘፍ 2:8
ዘፍ. 4:17ዘፍ 5:4
ዘፍ. 4:24ዘፍ 4:15
ዘፍ. 4:25ዘፍ 4:8፤ ማቴ 23:35፤ ዕብ 11:4
ዘፍ. 4:25ዘፍ 5:3፤ 1ዜና 1:1
ዘፍ. 4:26ዘፍ 5:6፤ ሉቃስ 3:23, 38
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 4:1-26

ዘፍጥረት

4 አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች።+ ቃየንንም+ በወለደች ጊዜ “በይሖዋ እርዳታ ወንድ ልጅ አፈራሁ”* አለች። 2 በኋላም ወንድሙን አቤልን+ ወለደች።

አቤል የበግ እረኛ ሆነ፤ ቃየን ግን አራሽ ሆነ። 3 ከጊዜ በኋላም ቃየን የተወሰኑ የምድር ፍሬዎችን ለይሖዋ መባ አድርጎ አቀረበ። 4 አቤል ግን ከመንጋው በኩራት+ መካከል የተወሰኑትን ከነስባቸው አቀረበ። ይሖዋ አቤልንና ያቀረበውን መባ+ በጥሩ ፊት ሲመለከት 5 ቃየንንና ያቀረበውን መባ ግን በጥሩ ፊት አልተመለከተም። በመሆኑም ቃየን በጣም ተናደደ፤ እጅግ አዘነ። 6 ከዚያም ይሖዋ ቃየንን እንዲህ አለው፦ “ለምን ተናደድክ? ለምንስ አዘንክ? 7 መልካም ወደ ማድረግ ብታዘነብል ኖሮ ሞገስ አታገኝም ነበር?* መልካም ወደ ማድረግ ካላዘነበልክ ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባ ነው፤ ሊቆጣጠርህም ይፈልጋል፤ ታዲያ አንተ ትቆጣጠረው ይሆን?”

8 ከዚያ በኋላ ቃየን ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳው ላይ ሳሉም ቃየን ወንድሙን አቤልን ደብድቦ ገደለው።+ 9 በኋላም ይሖዋ ቃየንን “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው፤ እሱም “እኔ አላውቅም። እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ። 10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው።+ 11 እንግዲህ የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል+ አፏን ከከፈተችው ምድር እንድትሰደድ ተረግመሃል። 12 ምድርን በምታርስበትም ጊዜ ምርቷን* አትሰጥህም። በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ ትሆናለህ።” 13 በዚህ ጊዜ ቃየን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “ለሠራሁት ጥፋት የምቀበለው ቅጣት ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። 14 ይኸው በዚህ ቀን ከምድሪቱ* ልታባርረኝ ነው፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ እንዲሁም በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ እሆናለሁ፤ እንግዲህ በቃ፣ ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛል።” 15 ስለሆነም ይሖዋ “እንግዲያው ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው።

በመሆኑም ያገኘው ማንም እንዳይገድለው ይሖዋ ለቃየን ምልክት አደረገለት።* 16 ከዚያም ቃየን ከይሖዋ ፊት ርቆ ሄደ፤ ከኤደን በስተ ምሥራቅ+ በሚገኘው በግዞት ምድር* መኖር ጀመረ።

17 ከዚህ በኋላ ቃየን ከሚስቱ+ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች፤ ሄኖክንም ወለደች። ከዚያም ቃየን ከተማ መገንባት ጀመረ፤ ከተማዋንም በልጁ በሄኖክ ስም ሰየማት። 18 ከጊዜ በኋላም ሄኖክ ኢራድን ወለደ። ኢራድም መሁያኤልን ወለደ፤ መሁያኤልም መቱሻኤልን ወለደ፤ መቱሻኤል ደግሞ ላሜህን ወለደ።

19 ላሜህም ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የመጀመሪያዋ ስም አዳ ሲሆን የሁለተኛዋ ስም ደግሞ ጺላ ነበር። 20 አዳ ያባልን ወለደች። ያባል በድንኳን የሚኖሩና ከብት የሚያረቡ ሰዎች አባት ነበር። 21 የወንድሙ ስም ዩባል ነበር። እሱም የበገና ደርዳሪዎችና የእምቢልታ* ነፊዎች አባት ነበር። 22 ጺላ ደግሞ ቱባልቃይንን ወለደች፤ እሱም መዳብና ብረት እየቀጠቀጠ የተለያዩ መሣሪያዎችን ይሠራ ነበር። የቱባልቃይን እህት ናዕማ ትባል ነበር። 23 ከዚያም ላሜህ ለሚስቶቹ ለአዳና ለጺላ የሚከተለውን ተቀኘ፦

“እናንተ የላሜህ ሚስቶች፣ ቃሌን ስሙ፤

የምላችሁንም አዳምጡ፦

አንድ ሰው ስላቆሰለኝ፣

አዎ፣ አንድ ወጣት ስለመታኝ ገደልኩት።

24 ቃየንን የሚገድል 7 እጥፍ የበቀል ቅጣት+ የሚደርስበት ከሆነ

ላሜህን የገደለማ 77 ጊዜ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል።”

25 አዳም ከሚስቱ ጋር በድጋሚ የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም “ቃየን አቤልን ስለገደለው+ በእሱ ፋንታ አምላክ ሌላ ዘር ተክቶልኛል” በማለት ሴት*+ አለችው። 26 ሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሄኖስ+ አለው። በዚያን ዘመን ሰዎች የይሖዋን ስም መጥራት ጀመሩ።*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ