ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።
125 በይሖዋ የሚታመኑ፣+
ፈጽሞ ሳይናወጥ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖረው
እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።+
2 ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ፣+
ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም
በሕዝቡ ዙሪያ ይሆናል።+
3 ጻድቃን ትክክል ያልሆነ ነገር መሥራት እንዳይጀምሩ፣+
የክፋት በትር ለጻድቃን በተሰጠ ምድር ላይ አይኖርም።+
4 ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩ ሰዎች፣
ለልበ ቅኖች+ መልካም ነገር አድርግ።+
5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው ዞር የሚሉትን፣
ይሖዋ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።+
በእስራኤል ሰላም ይስፈን።