መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት የሚዜም ማህሌት። የአሳፍ+ መዝሙር።
2 አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስን
በትክክል እፈርዳለሁ።
3 ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣
ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ)
4 ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤
ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን* ከፍ ከፍ አታድርጉ።
6 ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብ
ወይም ከደቡብ አይመጣምና።
አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።+
8 በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤+
የወይን ጠጁ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው።
እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤
በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”+
9 እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤
ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።