መዝሙር
መዝሙር። የዳዊት ማህሌት።
108 አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።
በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።+
2 ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣+ ተነሱ።
እኔም በማለዳ እነሳለሁ።
3 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤
በብሔራትም መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
4 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+
ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው።
5 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+
6 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑ
በቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠኝ።+
7 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦
9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+
በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+
በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+
10 ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+
11 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?
አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+