የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 42
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቡ ኤርምያስን እንዲጸልይላቸው ለመኑት (1-6)

      • ይሖዋ “ወደ ግብፅ አትሂዱ” አላቸው (7-22)

ኤርምያስ 42:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    2ነገ 25:23 ላይ ያአዛንያህ፣ ኤር 43:2 ላይ ደግሞ አዛርያስ ተብሎ ተጠርቷል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 40:13, 14

ኤርምያስ 42:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:62

ኤርምያስ 42:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 41:16

ኤርምያስ 42:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አዝናለሁና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:36፤ ኤር 18:7, 8፤ ሚክ 7:18

ኤርምያስ 42:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 41:17, 18

ኤርምያስ 42:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:6

ኤርምያስ 42:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 43:4, 7

ኤርምያስ 42:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለተወሰነ ጊዜ በዚያ ለመኖር።”

ኤርምያስ 42:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:45፤ ኤር 44:12-14, 27, 28

ኤርምያስ 42:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በበሽታ።”

ኤርምያስ 42:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:8-10፤ 2ዜና 34:24, 25፤ 36:16, 17፤ ሰቆ 2:4
  • +ኤር 29:18

ኤርምያስ 42:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 42:1, 2

ኤርምያስ 42:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 24:19፤ ነህ 9:26፤ ዘካ 7:11

ኤርምያስ 42:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 43:10, 11

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 42:1ኤር 40:13, 14
ኤር. 42:2ዘዳ 28:62
ኤር. 42:8ኤር 41:16
ኤር. 42:10ዘዳ 32:36፤ ኤር 18:7, 8፤ ሚክ 7:18
ኤር. 42:11ኤር 41:17, 18
ኤር. 42:12ዘፀ 34:6
ኤር. 42:14ኤር 43:4, 7
ኤር. 42:16ዘዳ 28:45፤ ኤር 44:12-14, 27, 28
ኤር. 42:182ነገ 25:8-10፤ 2ዜና 34:24, 25፤ 36:16, 17፤ ሰቆ 2:4
ኤር. 42:18ኤር 29:18
ኤር. 42:20ኤር 42:1, 2
ኤር. 42:212ዜና 24:19፤ ነህ 9:26፤ ዘካ 7:11
ኤር. 42:22ኤር 43:10, 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 42:1-22

ኤርምያስ

42 ከዚያም የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣+ የሆሻያህ ልጅ የዛንያህ* እና ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው 2 ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ሞገስ ለማግኘት የምናቀርበውን ልመና እባክህ ስማ፤ ስለ እኛና ስለ እነዚህ ቀሪዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይ፤ ይኸው እንደምታየው ከብዙዎች መካከል የቀረነው ጥቂቶች ብቻ ነን።+ 3 አምላክህ ይሖዋ በየት መሄድ እንደሚገባንና ምን ማድረግ እንዳለብን ይንገረን።”

4 ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እሺ፣ ሰምቻችኋለሁ፤ በጠየቃችሁኝ መሠረት ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ፤ ይሖዋ የሚመልስላችሁንም ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ። አንድም ቃል አላስቀርባችሁም።”

5 እነሱም ለኤርምያስ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “አምላክህ ይሖዋ በአንተ በኩል እንዳዘዘን ባናደርግ፣ ይሖዋ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምሥክር ይሁን። 6 የአምላካችንን የይሖዋን ቃል በመታዘዝ መልካም እንዲሆንልን፣ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ ወደ እሱ የምንልክህ አምላካችን ይሖዋ የሚለውን ሁሉ እንፈጽማለን።”

7 ከአሥር ቀን በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 8 ስለዚህ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን፣ ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ ጠራ።+ 9 እንዲህም አላቸው፦ “ሞገስ ለማግኘት ያሰማችሁትን ልመና በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ 10 ‘በእርግጥ በዚህች ምድር ላይ የምትኖሩ ከሆነ፣ እገነባችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ባመጣሁት ጥፋት እጸጸታለሁና።*+ 11 ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ የተነሳ አትሸበሩ።’+

“‘ከእሱ የተነሳ አትፍሩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘አድናችሁና ከእጁ እታደጋችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና። 12 ምሕረት አደርግላችኋለሁ፤+ እሱም ምሕረት ያደርግላችኋል፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም ይመልሳችኋል።

13 “‘እናንተ ግን “አይሆንም፤ በዚህች ምድር ላይ አንኖርም!” ብትሉና የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ባትታዘዙ፣ 14 ደግሞም “አይሆንም፤ ጦርነት ወደማናይበት፣ የቀንደ መለከት ድምፅ ወደማንሰማበት ወይም ምግብ አጥተን ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤+ በዚያም እንኖራለን” ብትሉ፣ 15 እናንተ የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ግብፅ ለመግባት ቆርጣችሁ ከተነሳችሁና በዚያ ለመኖር* ከሄዳችሁ፣ 16 የፈራችሁት ሰይፍ ራሱ በግብፅ ምድር ያገኛችኋል፤ የፈራችሁትም ረሃብ ወደ ግብፅ ተከትሏችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።+ 17 በዚያ ለመኖር ሲሉ ወደ ግብፅ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታሉ። በእነሱ ላይ ከማመጣው ጥፋት ከመካከላቸው የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይኖርም።”’

18 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ወደ ግብፅ ከሄዳችሁ፣ ቁጣዬና ንዴቴ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ እንደወረደ ሁሉ+ በእናንተም ላይ ቁጣዬ ይወርዳል፤ እናንተም ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ፤ መቀጣጫም ትሆናላችሁ፤+ ይህን ቦታም ዳግመኛ አታዩትም።’

19 “የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ ተናግሯል። ወደ ግብፅ አትሂዱ። ዛሬ እንዳስጠነቀቅኳችሁ በእርግጥ እወቁ፤ 20 በደላችሁም ሕይወታችሁን* እንደሚያሳጣችሁ እወቁ። እንዲህ ስትሉ ወደ ይሖዋ አምላካችሁ ልካችሁኝ ነበርና፦ ‘ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ስለ እኛ ጸልይ፤ አምላካችን ይሖዋም የሚለውን ነገር ሁሉ ንገረን፤ እኛም የተባልነውን እናደርጋለን።’+ 21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን የአምላካችሁን የይሖዋን ቃልም ሆነ ወደ እናንተ ልኮኝ የነገርኳችሁን ሁሉ አትታዘዙም።+ 22 ስለዚህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ቦታ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ