ኤርምያስ
48 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ሞዓብ+ እንዲህ ይላል፦
“ወዮ፣ ነቦ+ ጠፍታለችና!
ቂርያታይም+ ኀፍረት ተከናንባለች፤ ደግሞም ተይዛለች።
አስተማማኝ የሆነው መጠጊያ ተዋርዷል፤ ፈራርሷልም።+
2 ከእንግዲህ ሞዓብን አያወድሷትም።
ለውድቀት ትዳረግ ዘንድ፣
‘ኑ ብሔር መሆኗ እንዲያከትም እንደምስሳት’ ብለው በሃሽቦን+ ይዶልቱባታል።
አንቺም ማድመን ሆይ፣ ዝም በይ፤
ከኋላሽ ሰይፍ ይከተልሻልና።
3 ከሆሮናይም+ የጩኸት ድምፅ
እንዲሁም የጥፋትና የታላቅ ውድቀት ድምፅ ይሰማል።
4 ሞዓብ ጠፍታለች።
ልጆቿ ይጮኻሉ።
5 ወደ ሉሂት በሚወስደው አቀበት እያለቀሱ ይወጣሉ።
በደረሰው ጥፋት የተነሳ፣ ከሆሮናይም ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ሲወርዱም የጭንቅ ጩኸት ይሰማሉ።+
6 ሽሹ፤ ሕይወታችሁን አትርፉ!*
በምድረ በዳ እንዳለ የጥድ ዛፍ ሁኑ።
7 ምክንያቱም አንቺ በሥራሽና ውድ በሆነ ሀብትሽ ትታመኛለሽ፤
ደግሞም ትያዣለሽ።
ከሞሽ+ ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር
በአንድነት በግዞት ይወሰዳል።
8 አጥፊው በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ይመጣል፤
አንድም ከተማ አያመልጥም።+
10 ይሖዋ የሰጠውን ተልእኮ በግድየለሽነት የሚያከናውን የተረገመ ነው!
ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚመልስ ሰው የተረገመ ነው!
11 ሞዓባውያን ከልጅነታቸው ጀምሮ
በአምቡላው ላይ እንደረጋ ወይን ጠጅ ተረጋግተው ተቀምጠዋል።
ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም፤
በግዞትም ተወስደው አያውቁም።
በዚህም ምክንያት ቃናቸው እንዳለ ነው፤
መዓዛቸውም አልተለወጠም።
12 “‘ስለዚህ፣ እነሆ እነሱን እንዲገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘እነሱም ይገለብጧቸዋል፤ ዕቃዎቻቸውንም ባዶ ያስቀራሉ፤ ትላልቅ እንስራዎቻቸውንም ይሰባብራሉ። 13 የእስራኤል ቤት ይተማመንበት በነበረው በቤቴል እንዳፈረ ሁሉ ሞዓባውያንም በከሞሽ ያፍራሉ።+
14 “እኛ ለውጊያ የተዘጋጀን ኃያላን ተዋጊዎች ነን” በማለት እንዴት በድፍረት ትናገራላችሁ?’+
ምርጥ የሆኑት ወጣቶቻቸውም ታርደዋል።’+
16 በሞዓባውያን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ቀርቧል፤
ውድቀታቸውም በፍጥነት እየቀረበ ነው።+
17 በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ፣
ስማቸውን የሚያውቁ ሁሉ አብረዋቸው ያዝናሉ።
‘ኃያሉ በትር፣ የውበትም ዘንግ እንዴት ተሰበረ!’ በሏቸው።
19 አንቺ በአሮዔር+ የምትኖሪ፣ መንገዱ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ።
የሚሸሸውን ወንድና የምታመልጠውን ሴት ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።
20 ሞዓብ ኀፍረት ተከናነበች፤ በሽብርም ተውጣለች።
ዋይ ዋይ በሉ፤ እንዲሁም ጩኹ።
ሞዓብ መጥፋቷን በአርኖን+ አውጁ።
21 “ፍርድ ወደ ደልዳላው መሬት* መጥቷል፤+ በሆሎን፣ በያሃጽና+ በመፋአት፣+ 22 በዲቦን፣+ በነቦና+ በቤትዲብላታይም፣ 23 በቂርያታይም፣+ በቤትጋሙልና በቤትምዖን፣+ 24 በቀሪዮትና+ በቦስራ እንዲሁም በሩቅና በቅርብ ባሉ የሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል።
25 ‘የሞዓብ ብርታት* ተቆርጧል፤
ክንዱም ተሰብሯል’ ይላል ይሖዋ።
ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤
መሳለቂያም ሆኗል።
27 እስራኤል የአንተ መሳለቂያ ሆኖ አልነበረም?+
ራስህን የምትነቀንቀውና እሱን የምትቃወመው
እስራኤል ከሌቦች ጋር ተገኝቶ ነው?
28 እናንተ የሞዓብ ነዋሪዎች፣ ከከተሞቹ ወጥታችሁ በቋጥኝ ላይ ኑሩ፤
በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ ርግብም ሁኑ።’”
29 “ስለ ሞዓብ ኩራት ሰምተናል፤ እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው፤
ስለ እብሪቱ፣ ስለ ኩራቱ፣ ስለ ትዕቢቱና ስለ ልቡ ማበጥ ሰምተናል።”+
30 “‘ቁጣውን አውቃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤
‘ሆኖም ጉራው ከንቱ ይሆናል።
አንዳች ነገር አያደርጉም።
የተንዠረገጉት ቅርንጫፎችሽ ባሕሩን ተሻግረዋል።
እስከ ባሕሩ፣ እስከ ያዜርም ደርሰዋል።
33 ከፍራፍሬ እርሻውና ከሞዓብ ምድር
ሐሴትና ደስታ ጠፍቷል።+
ከወይን መጭመቂያዎቹ የወይን ጠጅ መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጌአለሁ።
በእልልታ ወይን የሚረግጥ ሰው አይኖርም።
ጩኸቱ ለየት ያለ ጩኸት ይሆናል።’”+
34 “‘በሃሽቦን+ የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ኤልዓሌ+ ድረስ ይሰማል።
የኒምሪም ውኃዎች እንኳ ይደርቃሉ።+
35 ከፍ ባለ የማምለኪያ ቦታ ላይ መባ የሚያቀርበውንና
ለአምላኩ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው
ከሞዓብ አጠፋለሁ’ ይላል ይሖዋ።
ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና።
37 ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+
ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
38 “‘በሞዓብ ጣሪያዎች ሁሉና
በአደባባዮቿ ሁሉ ላይ
ከዋይታ ሌላ የሚሰማ ነገር የለም።
ሞዓብን እንደተጣለ እንስራ
ሰባብሬአታለሁና’ ይላል ይሖዋ።
39 ‘እጅግ ተሸብራለች! ዋይ ዋይ በሉ!
ሞዓብ ኀፍረት ተከናንቦ ጀርባውን አዙሯል!
ሞዓብ መሳለቂያ ሆኗል፤
በዙሪያው ያሉት ሁሉ ከእሱ የተነሳ ይደነግጣሉ።’”
40 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
41 ከተሞቹ ይወረራሉ፤
ምሽጎቿም ይያዛሉ።
በዚያ ቀን የሞዓብ ተዋጊዎች ልብ
ምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።’”
43 የሞዓብ ነዋሪ ሆይ፣
ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል’ ይላል ይሖዋ።
44 ‘ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓዱ ውስጥ ይወድቃል፤
ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።’
‘የሚቀጡበትን ዓመት በሞዓብ ላይ አመጣለሁና’ ይላል ይሖዋ።
45 ‘የሚሸሹት ሰዎች ኃይላቸው ተሟጦ በሃሽቦን ጥላ ሥር ይቆማሉ።
ከሃሽቦን እሳት፣
ከሲሖን መካከልም ነበልባል ይወጣልና።+
የሞዓብን ግንባርና
የሁከት ልጆችን ራስ ቅል ይበላል።’+
46 ‘ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ!
የከሞሽ+ ሰዎች ጠፍተዋል።
ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፤
ሴቶች ልጆችህም በግዞት ተወስደዋል።+
47 በዘመኑ መጨረሻ ግን፣ ከሞዓብ የተማረኩትን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።
‘በሞዓብ ላይ የተላለፈው የፍርድ መልእክት እዚህ ላይ ይደመደማል።’”+