ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።
70 አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤
ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
2 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ
ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ
አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
3 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ
አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4 አንተን የሚፈልጉ ግን
በአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+
የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣
ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ።
5 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤+
አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ።+
አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+
ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ።+