የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ስለሰመጠው የጢሮስ መርከብ የተነገረ ሙሾ (1-36)

ሕዝቅኤል 27:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:17

ሕዝቅኤል 27:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:9፤ ሕዝ 28:2, 12

ሕዝቅኤል 27:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዘዳ 3:8, 9 ላይ የተጠቀሰውን “የሄርሞን ተራራ” ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:8, 9፤ 1ዜና 5:23

ሕዝቅኤል 27:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 4

ሕዝቅኤል 27:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 4

ሕዝቅኤል 27:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:15, 18
  • +1ነገ 9:27

ሕዝቅኤል 27:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሽማግሌዎቹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:2, 5
  • +ሕዝ 27:27

ሕዝቅኤል 27:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:6፤ ኤር 46:9

ሕዝቅኤል 27:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 4፤ ዮናስ 1:3
  • +2ዜና 9:21
  • +ኤር 10:9

ሕዝቅኤል 27:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 66:19
  • +ዘፍ 10:2
  • +ኢዩ 3:6

ሕዝቅኤል 27:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 3፤ ሕዝ 38:6

ሕዝቅኤል 27:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በጣም ተፈላጊ የሆነ ጥቁር እንጨት። እንግሊዝኛ፣ ኢቦኒ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:7
  • +1ነገ 10:22

ሕዝቅኤል 27:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 11:12, 33
  • +ዘፍ 43:11
  • +ኤር 8:22
  • +1ነገ 5:9፤ ዕዝራ 3:7፤ ሥራ 12:20

ሕዝቅኤል 27:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀላ ያለ ግራጫ ሱፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 7:8

ሕዝቅኤል 27:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከቀረፋ ዛፍ ጋር የሚዛመድ ዛፍ ነው።

ሕዝቅኤል 27:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የተሸመነ የኮርቻ ልብስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 25:3

ሕዝቅኤል 27:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 17:11፤ ኢሳ 60:7
  • +ዘፍ 25:13

ሕዝቅኤል 27:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:7
  • +1ነገ 10:1, 2፤ ኢሳ 60:6

ሕዝቅኤል 27:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:31
  • +2ነገ 19:12፤ አሞጽ 1:5
  • +ዘፍ 25:3፤ ኢዮብ 6:19
  • +ዘፍ 10:22

ሕዝቅኤል 27:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ክብር ተላብሰሽ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:22፤ ኢሳ 23:14

ሕዝቅኤል 27:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ጉባኤ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:8, 9
  • +ሕዝ 27:10, 11
  • +ሕዝ 26:14

ሕዝቅኤል 27:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:1፤ ሕዝ 26:17

ሕዝቅኤል 27:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከነፍሳቸው ምሬት የተነሳ።”

ሕዝቅኤል 27:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:5

ሕዝቅኤል 27:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:14, 16
  • +ዘካ 9:3

ሕዝቅኤል 27:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:19
  • +ሕዝ 27:27

ሕዝቅኤል 27:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:15
  • +ሕዝ 28:17

ሕዝቅኤል 27:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:10

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 27:2ሕዝ 26:17
ሕዝ. 27:3ኢሳ 23:9፤ ሕዝ 28:2, 12
ሕዝ. 27:5ዘዳ 3:8, 9፤ 1ዜና 5:23
ሕዝ. 27:6ዘፍ 10:2, 4
ሕዝ. 27:7ዘፍ 10:2, 4
ሕዝ. 27:8ዘፍ 10:15, 18
ሕዝ. 27:81ነገ 9:27
ሕዝ. 27:9ኢያሱ 13:2, 5
ሕዝ. 27:9ሕዝ 27:27
ሕዝ. 27:10ዘፍ 10:6፤ ኤር 46:9
ሕዝ. 27:12ዘፍ 10:2, 4፤ ዮናስ 1:3
ሕዝ. 27:122ዜና 9:21
ሕዝ. 27:12ኤር 10:9
ሕዝ. 27:13ኢሳ 66:19
ሕዝ. 27:13ዘፍ 10:2
ሕዝ. 27:13ኢዩ 3:6
ሕዝ. 27:14ዘፍ 10:2, 3፤ ሕዝ 38:6
ሕዝ. 27:15ዘፍ 10:7
ሕዝ. 27:151ነገ 10:22
ሕዝ. 27:17መሳ 11:12, 33
ሕዝ. 27:17ዘፍ 43:11
ሕዝ. 27:17ኤር 8:22
ሕዝ. 27:171ነገ 5:9፤ ዕዝራ 3:7፤ ሥራ 12:20
ሕዝ. 27:18ኢሳ 7:8
ሕዝ. 27:20ዘፍ 25:3
ሕዝ. 27:212ዜና 17:11፤ ኢሳ 60:7
ሕዝ. 27:21ዘፍ 25:13
ሕዝ. 27:22ዘፍ 10:7
ሕዝ. 27:221ነገ 10:1, 2፤ ኢሳ 60:6
ሕዝ. 27:23ዘፍ 11:31
ሕዝ. 27:232ነገ 19:12፤ አሞጽ 1:5
ሕዝ. 27:23ዘፍ 25:3፤ ኢዮብ 6:19
ሕዝ. 27:23ዘፍ 10:22
ሕዝ. 27:251ነገ 10:22፤ ኢሳ 23:14
ሕዝ. 27:27ሕዝ 27:8, 9
ሕዝ. 27:27ሕዝ 27:10, 11
ሕዝ. 27:27ሕዝ 26:14
ሕዝ. 27:30ኢሳ 23:1፤ ሕዝ 26:17
ሕዝ. 27:32ሕዝ 26:5
ሕዝ. 27:33ሕዝ 27:14, 16
ሕዝ. 27:33ዘካ 9:3
ሕዝ. 27:34ሕዝ 26:19
ሕዝ. 27:34ሕዝ 27:27
ሕዝ. 27:35ሕዝ 26:15
ሕዝ. 27:35ሕዝ 28:17
ሕዝ. 27:36መዝ 37:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 27:1-36

ሕዝቅኤል

27 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጢሮስ ላይ ሙሾ አውርድ፤*+ 3 ጢሮስንም እንዲህ በላት፦

‘አንቺ በባሕሩ መግቢያዎች ላይ የምትኖሪና

በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር የንግድ ልውውጥ የምታደርጊ፣

ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ጢሮስ ሆይ፣ አንቺ ራስሽ ‘ፍጹም ውብ ነኝ’ ብለሻል።+

 4 ግዛትሽ በባሕሩ መካከል ነው፤

የገነቡሽ ሰዎችም ውበትሽን ፍጹም አድርገውታል።

 5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሰኒር*+ በመጣ የጥድ እንጨት ሠሩ፤

ለአንቺም የመርከብ ምሰሶ ለመሥራት ከሊባኖስ፣ አርዘ ሊባኖስ አመጡ።

 6 በባሳን የባሉጥ ዛፎች መቅዘፊያዎችሽን ሠሩ፤

የፊተኛውን ክፍልሽንም ከኪቲም+ ደሴቶች በመጣ በዝሆን ጥርስ በተለበጠ የጥድ እንጨት ሠሩ።

 7 ከግብፅ የመጣው የተለያየ ቀለም ያለው በፍታ የመርከብ ሸራሽን ለመሥራት አገልግሏል፤

የላይኛው መድረክ መሸፈኛዎችሽም ከኤሊሻ+ ደሴቶች በመጣ ሰማያዊ ክርና ሐምራዊ ሱፍ የተሠሩ ናቸው።

 8 ቀዛፊዎችሽ የሲዶና እና የአርዋድ+ ነዋሪዎች ነበሩ።

ጢሮስ ሆይ፣ የገዛ ራስሽ ባለሙያዎች መርከበኞችሽ ነበሩ።+

 9 ልምድ ያካበቱት* የጌባል+ ባለሙያዎች ስንጥቆችሽን ይደፍናሉ።+

በባሕር ላይ የሚጓዙ መርከቦችና ባሕረኞቻቸው ሁሉ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመገበያየት ወደ አንቺ ይመጡ ነበር።

10 የፋርስ፣ የሉድና የፑጥ+ ሰዎች ተዋጊዎች ሆነው በጦር ሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግሉ ነበር።

ጋሻቸውንና የራስ ቁራቸውን በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ደግሞም ግርማ ሞገስ አጎናጸፉሽ።

11 በሠራዊትሽ ውስጥ ያሉት የአርዋድ ሰዎች በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ቆመው ነበር፤

ጀግኖችም በማማዎችሽ ላይ ነበሩ።

ክብ የሆኑ ጋሻዎቻቸውን በቅጥሮችሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤

ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።

12 “‘“ከተትረፈረፈው ውድ ሀብትሽ የተነሳ ተርሴስ+ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር።+ ሸቀጣ ሸቀጦችሽን በብር፣ በብረት፣ በቆርቆሮና በእርሳስ ይለውጡ ነበር።+ 13 ያዋን፣ ቱባልና+ መሼቅ+ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በባሪያዎችና በመዳብ ዕቃዎች ይለውጡ ነበር።+ 14 የቶጋርማ+ ሰዎች ደግሞ ሸቀጦችሽን በጭነት ፈረሶች፣ በጦር ፈረሶችና በበቅሎዎች ይለውጡ ነበር። 15 የዴዳን+ ሰዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ በብዙ ደሴቶች ላይ ነጋዴዎች ቀጠርሽ፤ የዝሆን ጥርስና+ ዞጲ* በግብር መልክ ያመጡልሽ ነበር። 16 ከምታመርቻቸው ዕቃዎች ብዛት የተነሳ ኤዶም ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር። ሸቀጦችሽን በበሉር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ የተለያዩ ቀለማት ባላቸው ጥልፎች፣ ጥራት ባለው ልብስ፣ በዛጎልና በሩቢ ይለውጡ ነበር።

17 “‘“ይሁዳና የእስራኤል ምድር ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሚኒት+ ስንዴ፣ ምርጥ በሆኑ ምግቦች፣ በማር፣+ በዘይትና በበለሳን+ ይለውጡ ነበር።+

18 “‘“ደማስቆ+ ከተትረፈረፈው ምርትሽና ከሀብትሽ የተነሳ ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር፤ የሄልቦን የወይን ጠጅና የዛሃር ሱፍ* ጨርቅ ትሸጥልሽ ነበር። 19 በዑዛል አቅራቢያ የሚገኙት ዌዳንና ያዋን ሸቀጦችሽን በሚተጣጠፍ ብረት፣ በብርጉድና* በጠጅ ሣር ይለውጡ ነበር። 20 ዴዳን፣+ በከብት ላይ ለመቀመጥ የሚያገለግል ግላስ* በማቅረብ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር። 21 የጠቦቶች፣ የአውራ በጎችና የፍየሎች+ ነጋዴ የሆኑ ዓረቦችንና የቄዳር+ አለቆችን ሁሉ ቀጠርሽ። 22 የሳባና የራአማ+ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሁሉም ዓይነት ምርጥ የሆኑ ሽቶዎች፣ የከበሩ ድንጋዮችና በወርቅ ይለውጡ ነበር።+ 23 ካራን፣+ ካኔህና ኤደን+ እንዲሁም የሳባ፣+ የአሹርና+ የኪልማድ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር። 24 በገበያ ቦታሽ ያማሩ ልብሶችን፣ በሰማያዊ ጨርቅና የተለያዩ ቀለማት ባለው ጥልፍ የተሠራን ካባ እንዲሁም ብዙ ዓይነት ቀለም ያላቸውን ምንጣፎች ይነግዱ የነበረ ሲሆን ሁሉም በገመድ በጥብቅ የታሰሩ ነበሩ።

25 የተርሴስ መርከቦች+ ሸቀጦችሽን ያጓጉዙልሽ ነበር፤

በመሆኑም በባሕሩ መካከል በሀብት ተሞልተሽና ጭነት በዝቶልሽ* ነበር።

26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ባሕር አምጥተውሻል፤

የምሥራቁ ነፋስ በተንጣለለው ባሕር መካከል ሰባብሮሻል።

27 ውድቀት በሚደርስብሽ ቀን ሀብትሽ፣ ሸቀጦችሽ፣ የምትነግጃቸው ዕቃዎች፣ ባሕረኞችሽ፣ መርከበኞችሽ፣

ስንጥቆችሽን የሚደፍኑልሽ ሰዎች፣ ነጋዴዎችሽና+ ተዋጊዎችሽ ሁሉ+

ይኸውም በአንቺ ውስጥ ያለው ሕዝብ* ሁሉ

በተንጣለለው ባሕር መካከል ይሰምጣል።+

28 መርከበኞችሽ ሲጮኹ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል።

29 ቀዛፊዎቹ፣ ባሕረኞቹና መርከበኞቹ ሁሉ

ከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ መሬት ላይም ይቆማሉ።

30 በአንቺ የተነሳ በራሳቸው ላይ አቧራ እየነሰነሱና በአመድ ላይ እየተንከባለሉ

ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ምርር ብለውም ያለቅሳሉ።+

31 በአንቺ የተነሳ ራሳቸውን ይላጫሉ፣ ማቅ ይለብሳሉ

እንዲሁም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው * ያለቅሳሉ።

32 ለአንቺም በሚያለቅሱበት ጊዜ ሙሾ ያወርዳሉ፤ የሐዘን እንጉርጉሮም ያንጎራጉራሉ፦

‘በባሕር መካከል ጸጥ እንዳለችው እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?+

33 ሸቀጥሽ ከተንጣለለው ባሕር በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል።+

የተትረፈረፈው ሀብትሽና ሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽጓል።+

34 አሁን ግን በተንጣለለው ባሕር ላይ ተሰባብረሽ ጥልቁ ውኃ ውስጥ ሰምጠሻል፤+

ሸቀጥሽና ሕዝብሽ ሁሉ አብረውሽ ሰምጠዋል።+

35 የደሴቶቹም ነዋሪዎች ሁሉ በመገረም አተኩረው ይመለከቱሻል፤+

ነገሥታታቸውም በታላቅ ፍርሃት ይርዳሉ፤+ ፊታቸውም ይለዋወጣል።

36 በብሔራት መካከል ያሉ ነጋዴዎች በአንቺ ላይ ከደረሰው ነገር የተነሳ ያፏጫሉ።

ፍጻሜሽ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤

ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆኛለሽ።’”’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ