የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቡ ብዙኃኑ የሚከተለውን መንገድ ተከተለ (1-7)

      • የይሖዋን ቃል ንቀው ምን ዓይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል? (8-17)

      • ኤርምያስ በይሁዳ ላይ በደረሰው ውድቀት የተነሳ አዘነ (18-22)

        • “በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?” (22)

ኤርምያስ 8:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:19፤ 2ነገ 17:16፤ 21:1, 3፤ ኤር 19:13፤ ሕዝ 8:16፤ ሶፎ 1:4, 5
  • +ኤር 16:4

ኤርምያስ 8:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:3

ኤርምያስ 8:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:1

ኤርምያስ 8:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።

  • *

    ወይም “የተወሰነ ጊዜዋን።”

  • *

    “ቁርዬ” ልትሆንም ትችላለች።

  • *

    ወይም “የሚፈልሱበትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2023፣ ገጽ 17

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 6 2016፣ ገጽ 8-9

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2002፣ ገጽ 32

ኤርምያስ 8:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

  • *

    ወይም “የውሸት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:1

ኤርምያስ 8:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 29:14

ኤርምያስ 8:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:30፤ ሶፎ 1:13
  • +ኢሳ 56:11፤ ሕዝ 33:31፤ ሚክ 3:11
  • +ኤር 5:31፤ 6:12-15፤ 27:9፤ ሰቆ 2:14፤ ሕዝ 22:28

ኤርምያስ 8:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንደነገሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 23:16, 17፤ ሕዝ 13:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣

    3/2017፣ ገጽ 1

ኤርምያስ 8:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 3:3
  • +ኤር 23:12

ኤርምያስ 8:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:5
  • +ኤር 9:15፤ 23:15፤ ሰቆ 3:19

ኤርምያስ 8:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:10፤ 14:19

ኤርምያስ 8:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:19, 20፤ 14:17

ኤርምያስ 8:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጊልያድ ሕመም ማስታገሻ ቅባት የለም?”

  • *

    ወይም “ሐኪም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 37:25
  • +ኤር 30:12, 13
  • +ኤር 30:17፤ 33:4, 6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2010፣ ገጽ 21-22

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 8:2ዘዳ 4:19፤ 2ነገ 17:16፤ 21:1, 3፤ ኤር 19:13፤ ሕዝ 8:16፤ ሶፎ 1:4, 5
ኤር. 8:2ኤር 16:4
ኤር. 8:5ኤር 5:3
ኤር. 8:6ኤር 5:1
ኤር. 8:7ኢሳ 1:3
ኤር. 8:8ኢሳ 8:1
ኤር. 8:9ኢሳ 29:14
ኤር. 8:10ዘዳ 28:30፤ ሶፎ 1:13
ኤር. 8:10ኢሳ 56:11፤ ሕዝ 33:31፤ ሚክ 3:11
ኤር. 8:10ኤር 5:31፤ 6:12-15፤ 27:9፤ ሰቆ 2:14፤ ሕዝ 22:28
ኤር. 8:11ኤር 23:16, 17፤ ሕዝ 13:10
ኤር. 8:12ኤር 3:3
ኤር. 8:12ኤር 23:12
ኤር. 8:14ኤር 4:5
ኤር. 8:14ኤር 9:15፤ 23:15፤ ሰቆ 3:19
ኤር. 8:15ኤር 4:10፤ 14:19
ኤር. 8:21ኤር 4:19, 20፤ 14:17
ኤር. 8:22ዘፍ 37:25
ኤር. 8:22ኤር 30:12, 13
ኤር. 8:22ኤር 30:17፤ 33:4, 6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 8:1-22

ኤርምያስ

8 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳ ነገሥታት አጥንቶች፣ የመኳንንቱ አጥንቶች፣ የካህናቱ አጥንቶች፣ የነቢያቱ አጥንቶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አጥንቶች ከየመቃብራቸው ይወሰዳሉ። 2 በወደዷቸው፣ ባገለገሏቸው፣ በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና በሰገዱላቸው በፀሐይ፣ በጨረቃና በሰማያት ሠራዊት ሁሉ ፊት ይሰጣሉ።+ አይሰበሰቡም፤ እንዲሁም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።”+

3 “ደግሞም ከዚህ ክፉ ወገን የሚተርፉት ቀሪዎች በሙሉ እኔ በምበትናቸው ቦታዎች ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

4 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ሰዎች ከወደቁ በኋላ ዳግመኛ አይነሱም?

አንዱ ከተመለሰ ሌላውስ አይመለስም?

 5 ታዲያ ይህ ሕዝብ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪ በክህደት ሥራው የጸናው ለምንድን ነው?

ተንኮልን የሙጥኝ ብለዋል፤

ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል።+

 6 እኔም ትኩረት ሰጥቼ ማዳመጤን ቀጠልኩ፤ የሚናገሩበት መንገድ ግን ትክክል አልነበረም።

ከክፋቱ ንስሐ የገባ ወይም ‘ምን መሥራቴ ነው?’ ብሎ የጠየቀ አንድም ሰው የለም።+

እያንዳንዱ ሰው ወደ ጦርነት እንደሚገሰግስ ፈረስ ብዙኃኑ ወደሚከተለው መንገድ ይመለሳል።

 7 በሰማይ የምትበረው ራዛ* እንኳ ወቅቷን* ታውቃለች፤

ዋኖስ፣ ወንጭፊትና ጭሪ* የሚመለሱበትን* ጊዜ ያከብራሉ።

የገዛ ሕዝቤ ግን የይሖዋን ፍርድ አይገነዘብም።”’+

 8 ‘“ጥበበኞች ነን፤ የይሖዋም ሕግ* አለን” እንዴት ትላላችሁ?

እንዲያውም የጸሐፊዎቹ ሐሰተኛ* ብዕር+ ያገለገለው ውሸት ለመጻፍ ብቻ ነው።

 9 ጥበበኞቹ ለኀፍረት ተዳርገዋል።+

ተሸብረዋል፤ ደግሞም ይያዛሉ።

እነሆ፣ እነሱ የይሖዋን ቃል ንቀዋል፤

ታዲያ ምን ዓይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣

እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+

ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+

ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+

11 ሰላም ሳይኖር፣

“ሰላም ነው! ሰላም ነው!” እያሉ

የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+

12 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?

እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!

ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+

“‘ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።

እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ’+ ይላል ይሖዋ።

13 ‘በምሰበስባቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።

‘በወይን ተክሉ ላይ የቀረ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፉ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሉም ይጠወልጋል።

የሰጠኋቸውም ነገር ይጠፋባቸዋል።’”

14 “እዚህ የምንቀመጠው ለምንድን ነው?

በአንድነት እንሰብሰብ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች ገብተን+ በዚያ እንጥፋ።

አምላካችን ይሖዋ ያጠፋናልና፤

የተመረዘ ውኃ እንድንጠጣ ይሰጠናል፤+

ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል።

15 ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤

የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+

16 የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ።

ድንጉላ ፈረሶቹ ሲያሽካኩ

ምድሪቱ በሙሉ ትንቀጠቀጣለች።

እነሱ መጥተው ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣

ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ይበላሉ።”

17 “እነሆ፣ ድግምት የማይገታቸው እባቦችንና እፉኝቶችን

በመካከላችሁ እልካለሁ፤

እነሱም ይነድፏችኋል” ይላል ይሖዋ።

18 ማጽናኛ የማይገኝለት ሐዘን ደርሶብኛል፤

ልቤ ታሟል።

19 የሕዝቤ ሴት ልጅ “ይሖዋ በጽዮን የለም?

ወይስ ንጉሧ በዚያ የለም?”

የሚል የእርዳታ ጥሪ

ከሩቅ አገር ታሰማለች።

“በተቀረጹት ምስሎቻቸውና

ከንቱ በሆኑት ባዕዳን አማልክታቸው ያስከፉኝ ለምንድን ነው?”

20 “መከሩ አልፏል፤ በጋውም አብቅቷል፤

እኛ ግን አልዳንም!”

21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ውድቀት የተነሳ ደቅቄአለሁ፤+

በጣም አዝኛለሁ፤

በፍርሃት ተውጫለሁ።

22 በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?*+

ወይስ በዚያ ፈዋሽ* የለም?+

ታዲያ የሕዝቤ ሴት ልጅ ያላገገመችው ለምንድን ነው?+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ