የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሰቆቃወ ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የኢየሩሳሌም መከበብ ያስከተለው መጥፎ ውጤት

        • የምግብ እጦት (4, 5, 9)

        • ሴቶች ልጆቻቸውን ቀቀሉ (10)

        • “ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል” (11)

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመቅደሱ ድንጋዮች።”

  • *

    ቃል በቃል “በጎዳናዎቹ ሁሉ ራስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:22
  • +1ነገ 5:17፤ 7:9-12
  • +ኤር 52:12, 13

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንደጠራ ወርቅ ውድ የነበሩት።”

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:29፤ ዘዳ 28:53-57፤ ኢዮብ 39:14-16፤ ኤር 19:9፤ ሰቆ 4:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2007፣ ገጽ 10-11

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 1:11፤ 2:11, 12
  • +ኤር 52:6

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ይጠፋሉ።”

  • *

    ቃል በቃል “ደማቅ ቀይ።” ይኸውም ደማቅ ቀይ የሆነ ውድ ልብስ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 6:4, 7
  • +ኤር 6:2, 26

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በደል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:24, 25፤ ሕዝ 16:48፤ ዳን 9:12

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 6:2

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 102:5

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 29:17፤ 38:2

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:29፤ ሰቆ 2:20፤ 4:3
  • +ዘዳ 28:54-57

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 6:11፤ 7:20፤ ሕዝ 22:31
  • +ዘዳ 32:22፤ 2ነገ 25:9, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 25

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 29:24፤ 1ነገ 9:8

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:31፤ 14:14፤ ሚክ 3:11፤ ሶፎ 3:4
  • +ኤር 26:8፤ ማቴ 23:31፤ ሥራ 7:52

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:28፤ ሶፎ 1:17
  • +ኢሳ 1:15፤ ኤር 2:34

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 25

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የባዕድ አገር ሰዎች ሆነው መኖር አይችሉም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:25, 65

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 28:64፤ ኤር 24:9
  • +2ነገ 25:18, 21
  • +ሰቆ 5:12፤ ሕዝ 9:6

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 1:19
  • +ኤር 37:7፤ ሕዝ 29:6

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:5፤ ሰቆ 3:52

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:49, 50፤ ኢሳ 5:26፤ ኤር 4:13፤ ዕን 1:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1996፣ ገጽ 9-10

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:1
  • +2ነገ 25:5, 6፤ ኤር 39:5

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 137:7፤ አብ 12
  • +ኤር 25:17, 20፤ አብ 16
  • +ኤር 49:10, 12

ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:44፤ ኢሳ 52:1፤ 60:18
  • +ኢሳ 34:5፤ ሕዝ 25:13፤ 35:15፤ አሞጽ 1:11፤ አብ 13

ተዛማጅ ሐሳብ

ሰቆ. 4:11ነገ 6:22
ሰቆ. 4:11ነገ 5:17፤ 7:9-12
ሰቆ. 4:1ኤር 52:12, 13
ሰቆ. 4:3ዘሌ 26:29፤ ዘዳ 28:53-57፤ ኢዮብ 39:14-16፤ ኤር 19:9፤ ሰቆ 4:10
ሰቆ. 4:4ሰቆ 1:11፤ 2:11, 12
ሰቆ. 4:4ኤር 52:6
ሰቆ. 4:5አሞጽ 6:4, 7
ሰቆ. 4:5ኤር 6:2, 26
ሰቆ. 4:6ዘፍ 19:24, 25፤ ሕዝ 16:48፤ ዳን 9:12
ሰቆ. 4:7ዘኁ 6:2
ሰቆ. 4:8መዝ 102:5
ሰቆ. 4:9ኤር 29:17፤ 38:2
ሰቆ. 4:10ዘሌ 26:29፤ ሰቆ 2:20፤ 4:3
ሰቆ. 4:10ዘዳ 28:54-57
ሰቆ. 4:11ኤር 6:11፤ 7:20፤ ሕዝ 22:31
ሰቆ. 4:11ዘዳ 32:22፤ 2ነገ 25:9, 10
ሰቆ. 4:12ዘዳ 29:24፤ 1ነገ 9:8
ሰቆ. 4:13ኤር 5:31፤ 14:14፤ ሚክ 3:11፤ ሶፎ 3:4
ሰቆ. 4:13ኤር 26:8፤ ማቴ 23:31፤ ሥራ 7:52
ሰቆ. 4:14ዘዳ 28:28፤ ሶፎ 1:17
ሰቆ. 4:14ኢሳ 1:15፤ ኤር 2:34
ሰቆ. 4:15ዘዳ 28:25, 65
ሰቆ. 4:16ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 28:64፤ ኤር 24:9
ሰቆ. 4:162ነገ 25:18, 21
ሰቆ. 4:16ሰቆ 5:12፤ ሕዝ 9:6
ሰቆ. 4:17ሰቆ 1:19
ሰቆ. 4:17ኤር 37:7፤ ሕዝ 29:6
ሰቆ. 4:182ነገ 25:5፤ ሰቆ 3:52
ሰቆ. 4:19ዘዳ 28:49, 50፤ ኢሳ 5:26፤ ኤር 4:13፤ ዕን 1:8
ሰቆ. 4:20ኤር 37:1
ሰቆ. 4:202ነገ 25:5, 6፤ ኤር 39:5
ሰቆ. 4:21መዝ 137:7፤ አብ 12
ሰቆ. 4:21ኤር 25:17, 20፤ አብ 16
ሰቆ. 4:21ኤር 49:10, 12
ሰቆ. 4:22ዘሌ 26:44፤ ኢሳ 52:1፤ 60:18
ሰቆ. 4:22ኢሳ 34:5፤ ሕዝ 25:13፤ 35:15፤ አሞጽ 1:11፤ አብ 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:1-22

ሰቆቃወ ኤርምያስ

א [አሌፍ]

4 ያንጸባርቅ የነበረው ጥሩው ወርቅ፣+ ምንኛ ደበዘዘ!

የተቀደሱት ድንጋዮች*+ በየመንገዱ ማዕዘኖች* ላይ እንዴት ተበተኑ!+

ב [ቤት]

 2 በጠራ ወርቅ የተመዘኑት* የጽዮን ውድ ልጆች፣

የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራው

የሸክላ ዕቃ እንዴት ተቆጠሩ!

ג [ጊሜል]

 3 ቀበሮዎች እንኳ ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡታቸውን ይሰጣሉ፤

የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች ጨካኝ ሆነች።+

ד [ዳሌት]

 4 ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል።

ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤+ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም።+

ה [ሄ]

 5 ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ ሰዎች በየጎዳናው ላይ ጠኔ ይዟቸው ይተኛሉ።*+

ውድ ልብስ* ለብሰው ያደጉም+ የአመድ ቁልል ያቅፋሉ።

ו [ዋው]

 6 የሕዝቤ ሴት ልጅ የደረሰባት ቅጣት፣*

የማንም እጅ ሳይረዳት በድንገት የተገለበጠችው ሰዶም፣ በሠራችው ኃጢአት የተነሳ ከደረሰባት ቅጣት ይበልጥ ታላቅ ነው።+

ז [ዛየን]

 7 ናዝራውያኗ+ ከበረዶ ይልቅ የጠሩ፣ ከወተትም ይልቅ የነጡ ነበሩ።

ከዛጎል ይበልጥ የቀሉ ነበሩ፤ እንደተወለወለም ሰንፔር ነበሩ።

ח [ኼት]

 8 መልካቸው ከጥላሸት ይልቅ ጠቁሯል፤

በጎዳና ላይ ማንነታቸውን መለየት የቻለ የለም።

ቆዳቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፤+ እንደደረቀ እንጨት ሆኗል።

ט [ቴት]

 9 በሰይፍ የሚወድቁት በረሃብ ከሚያልቁት ይሻላሉ፤+

እነዚህ የምድርን ፍሬ በማጣታቸው መንምነው ያልቃሉ።

י [ዮድ]

10 ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል።+

የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል።+

כ [ካፍ]

11 ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤

የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል።+

በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል።+

ל [ላሜድ]

12 የምድር ነገሥታትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉ

ባላጋራም ሆነ ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል የሚል እምነት አልነበራቸውም።+

מ [ሜም]

13 ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+

እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+

נ [ኑን]

14 ታውረው በየጎዳናው ተቅበዘበዙ።+

በደም ስለተበከሉ+

ማንም ልብሳቸውን ለመንካት አይደፍርም።

ס [ሳሜኽ]

15 “እናንተ ርኩሳን! ሂዱ!” ይሏቸዋል። “ሂዱ! ሂዱ! አትንኩን!” ብለው ይጮኹባቸዋል።

መኖሪያ አጥተው ይቅበዘበዛሉና።

በብሔራት መካከል ያሉ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፦ “ከእንግዲህ ከእኛ ጋር እዚህ መኖር አይችሉም።*+

פ [ፔ]

16 ይሖዋ ራሱ በታትኗቸዋል፤+

ዳግመኛም በሞገስ ዓይን አይመለከታቸውም።

ሰዎች ለካህናቱ አክብሮት አይኖራቸውም፤+ ለሽማግሌዎቹም ሞገስ አያሳዩም።”+

ע [አይን]

17 አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ።+

ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን።+

צ [ጻዴ]

18 እግር በእግር ተከታተሉን፤+ በመሆኑም በአደባባዮቻችን መንቀሳቀስ አልቻልንም።

መጨረሻችን ቀርቧል፤ የሕይወት ዘመናችን አብቅቷል፤ ፍጻሜያችን ደርሷልና።

ק [ኮፍ]

19 አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ።+

በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን።

ר [ረሽ]

20 በይሖዋ የተቀባው፣+ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤+

“በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር።

ש [ሲን]

21 በዑጽ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣+ ሐሴት አድርጊ፤ ደስም ይበልሽ።

ይሁንና ጽዋው ለአንቺም ይደርስሻል፤+ ትሰክሪያለሽ፤ እርቃንሽንም ትገልጫለሽ።+

ת [ታው]

22 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል።

ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም።+

ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል።

ኃጢአትሽን ይገልጣል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ