የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 43
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቡ አሻፈረን ብለው ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7)

      • የይሖዋ ቃል በግብፅ ወደነበረው ወደ ኤርምያስ መጣ (8-13)

ኤርምያስ 43:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 41:16፤ 42:1-3

ኤርምያስ 43:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:4፤ 45:1
  • +ኤር 38:4, 6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 19

ኤርምያስ 43:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 40:11, 12

ኤርምያስ 43:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳት ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:10
  • +2ነገ 22:8
  • +2ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24
  • +2ነገ 25:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 19

ኤርምያስ 43:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:14, 16፤ 44:1፤ ሕዝ 30:4, 18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 19

ኤርምያስ 43:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾርን።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:9፤ 27:6፤ ሕዝ 29:19, 20
  • +ዳን 2:21፤ 5:18

ኤርምያስ 43:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:17, 19፤ 46:13፤ ሕዝ 29:19፤ 30:4, 18
  • +ኤር 44:13፤ ሕዝ 5:12

ኤርምያስ 43:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደሶችም።”

  • *

    ወይም “ጉዳት ሳይደርስበት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 46:25

ኤርምያስ 43:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የፀሐይን ቤት (ቤተ መቅደስ)።” ሂሊዮፖሊስ ማለት ነው።

  • *

    ወይም “ሐውልቶች።”

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደሶችም።”

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 43:2ኤር 41:16፤ 42:1-3
ኤር. 43:3ኤር 36:4፤ 45:1
ኤር. 43:3ኤር 38:4, 6
ኤር. 43:5ኤር 40:11, 12
ኤር. 43:6ኤር 39:10
ኤር. 43:62ነገ 22:8
ኤር. 43:62ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24
ኤር. 43:62ነገ 25:22
ኤር. 43:7ኤር 2:14, 16፤ 44:1፤ ሕዝ 30:4, 18
ኤር. 43:10ኤር 25:9፤ 27:6፤ ሕዝ 29:19, 20
ኤር. 43:10ዳን 2:21፤ 5:18
ኤር. 43:11ኤር 25:17, 19፤ 46:13፤ ሕዝ 29:19፤ 30:4, 18
ኤር. 43:11ኤር 44:13፤ ሕዝ 5:12
ኤር. 43:12ኤር 46:25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 43:1-13

ኤርምያስ

43 ኤርምያስ አምላካቸው ይሖዋ ለእነሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ሁሉ፣ አንድም ሳያስቀር ለሕዝቡ በሙሉ ተናግሮ ሲጨርስ 2 የሆሻያህ ልጅ አዛርያስ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን+ እና እብሪተኛ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “የምትናገረው ነገር ውሸት ነው! አምላካችን ይሖዋ ‘በግብፅ ለመኖር ወደዚያ አትሂዱ’ ብሎ አላከህም። 3 ከዚህ ይልቅ ከለዳውያን እንዲገድሉን ወይም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወስዱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ በእኛ ላይ ያነሳሳህ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ነው።”+

4 በመሆኑም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የሠራዊቱ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን የይሖዋን ቃል አልሰሙም። 5 እንዲያውም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች በሙሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተበተኑባቸው ብሔራት ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳ ቀሪዎች በሙሉ ይዘው ሄዱ።+ 6 ወንዶቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ከሳፋን+ ልጅ፣ ከአኪቃም+ ልጅ ከጎዶልያስ+ ጋር የተዋቸውን ሁሉ* እንዲሁም ነቢዩን ኤርምያስንና የነሪያህን ልጅ ባሮክን ይዘው ሄዱ። 7 የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍነስ+ ድረስም ሄዱ።

8 ከዚያም የይሖዋ ቃል በጣፍነስ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 9 “ትላልቅ ድንጋዮችን ውሰድና አይሁዳውያኑ እያዩ በጣፍነስ በሚገኘው በፈርዖን ቤት መግቢያ፣ ከጡብ ከተሠራው መደብ ሥር ሸሽገህ በቅጥራን ለስናቸው። 10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራዋለሁ፤+ ዙፋኑንም እኔ ከሸሸግኳቸው ከእነዚህ ድንጋዮች በላይ አስቀምጣለሁ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በእነሱ ላይ ይዘረጋል።+ 11 እሱም መጥቶ የግብፅን ምድር ይመታል።+ ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ ለገዳይ መቅሰፍት፣ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ለምርኮ እንዲሁም ሰይፍ የሚገባው ሁሉ ለሰይፍ ይሰጣል።+ 12 የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት አያይዛለሁ፤+ እሱም ያቃጥላቸዋል፤ ማርኮም ይወስዳቸዋል። እረኛ ልብሱን እንደሚጎናጸፍ የግብፅን ምድር ይጎናጸፋል፤ ከዚያም ቦታ በሰላም* ይሄዳል። 13 በግብፅም ምድር የሚገኙትን የቤትሼሜሽን* ዓምዶች* ይሰባብራል፤ የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት ያቃጥላል።”’”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ