የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢያቡስቴ ተገደለ (1-8)

      • ዳዊት የኢያቡስቴን ገዳዮች አስገደላቸው (9-12)

2 ሳሙኤል 4:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሳኦል ወንድ ልጅ።”

  • *

    ቃል በቃል “እጆቹ ዛሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:8
  • +2ሳሙ 3:27

2 ሳሙኤል 4:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 9:17፤ 18:21, 25

2 ሳሙኤል 4:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 11:31, 33

2 ሳሙኤል 4:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 20:16
  • +2ሳሙ 9:3
  • +1ሳሙ 29:1, 11
  • +2ሳሙ 9:13፤ 1ዜና 8:34

2 ሳሙኤል 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 4:2

2 ሳሙኤል 4:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:10
  • +1ሳሙ 18:10, 11፤ 20:1, 33፤ 23:15
  • +1ሳሙ 18:28, 29

2 ሳሙኤል 4:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ በተቤዠልኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 24:12፤ 26:25፤ 2ሳሙ 12:7፤ መዝ 34:7

2 ሳሙኤል 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 1:2, 4
  • +2ሳሙ 1:13-15

2 ሳሙኤል 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12፤ ዘኁ 35:16, 30

2 ሳሙኤል 4:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 55:23
  • +ዘዳ 21:22

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 4:12ሳሙ 2:8
2 ሳሙ. 4:12ሳሙ 3:27
2 ሳሙ. 4:2ኢያሱ 9:17፤ 18:21, 25
2 ሳሙ. 4:3ነህ 11:31, 33
2 ሳሙ. 4:41ሳሙ 20:16
2 ሳሙ. 4:42ሳሙ 9:3
2 ሳሙ. 4:41ሳሙ 29:1, 11
2 ሳሙ. 4:42ሳሙ 9:13፤ 1ዜና 8:34
2 ሳሙ. 4:62ሳሙ 4:2
2 ሳሙ. 4:82ሳሙ 2:10
2 ሳሙ. 4:81ሳሙ 18:10, 11፤ 20:1, 33፤ 23:15
2 ሳሙ. 4:81ሳሙ 18:28, 29
2 ሳሙ. 4:91ሳሙ 24:12፤ 26:25፤ 2ሳሙ 12:7፤ መዝ 34:7
2 ሳሙ. 4:102ሳሙ 1:2, 4
2 ሳሙ. 4:102ሳሙ 1:13-15
2 ሳሙ. 4:11ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12፤ ዘኁ 35:16, 30
2 ሳሙ. 4:12መዝ 55:23
2 ሳሙ. 4:12ዘዳ 21:22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 4:1-12

ሁለተኛ ሳሙኤል

4 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ፣*+ አበኔር በኬብሮን መሞቱን+ ሲሰማ ወኔ ከዳው፤* እስራኤላውያንም በሙሉ ተረበሹ። 2 የሳኦል ልጅ የሚመራቸው ወራሪ ቡድኖች አለቃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ የአንደኛው ስም ባአናህ ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሬካብ ነበር። እነሱም ከቢንያም ነገድ የሆነው የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ነበሩ። (ምክንያቱም በኤሮት+ ከቢንያም ወገን እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። 3 በኤሮታውያን ወደ ጊታይም+ ሸሹ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ይኖራሉ።)

4 የሳኦል ልጅ ዮናታን+ እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው።+ እሱም ስለ ሳኦልና ስለ ዮናታን የሚገልጸው ወሬ ከኢይዝራኤል+ በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ ሞግዚቱም አንስታው መሸሽ ጀመረች፤ ሆኖም በድንጋጤ ሸሽታ ስትሮጥ ከእጇ ላይ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜፊቦስቴ+ ነበር።

5 የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ሬካብ እና ባአናህ ሞቃታማ በሆነው የቀኑ ክፍለ ጊዜ ወደ ኢያቡስቴ ቤት ሄዱ፤ እሱም ቀትር ላይ አረፍ ብሎ ነበር። 6 እነሱም ስንዴ የሚወስዱ ሰዎች መስለው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው ገቡ፤ ኢያቡስቴንም ሆዱ ላይ ወጉት፤ ከዚያም ሬካብ እና ወንድሙ ባአናህ+ ሸሽተው አመለጡ። 7 ወደ ቤት ሲገቡ ኢያቡስቴ መኝታ ቤቱ ውስጥ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ ነበር፤ እነሱም መትተው ገደሉት፤ ከዚያም ራሱን ቆርጠው በመውሰድ ወደ አረባ በሚወስደው መንገድ ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዙ አደሩ። 8 የኢያቡስቴንም+ ራስ በኬብሮን ወዳለው ወደ ዳዊት አምጥተው ንጉሡን “ሕይወትህን* ሲፈልጋት+ የነበረው የጠላትህ+ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ። ይሖዋ በዛሬው ዕለት ሳኦልንና ዘሮቹን ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቀለለት” አሉት።

9 ሆኖም ዳዊት ለበኤሮታዊው ለሪሞን ልጆች ለሬካብ እና ለወንድሙ ለባአናህ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሕይወቴን ከመከራ ሁሉ በታደገልኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ 10 አንድ ሰው ምሥራች ያበሰረኝ መስሎት ‘ሳኦል እኮ ሞተ’+ ብሎ በነገረኝ ጊዜ ጺቅላግ ላይ ገደልኩት።+ መልእክተኛው ከእኔ ያገኘው ሽልማት ይህ ነበር! 11 ታዲያ በገዛ ቤቱ አልጋው ላይ ተኝቶ የነበረውን ጻድቅ ሰው የገደሉ ክፉ ሰዎችማ እንዴት ከዚህ የባሰ ነገር አይጠብቃቸው! እና አሁን ደሙን ከእጃችሁ መጠየቅም+ ሆነ እናንተን ከምድር ገጽ ማጥፋት አይገባኝም?” 12 ከዚያም ዳዊት እንዲገድሏቸው ለወጣቶቹ ትእዛዝ ሰጠ።+ እነሱም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቆርጠው በኬብሮን በሚገኘው ኩሬ አጠገብ ሰቀሏቸው።+ የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በኬብሮን ባለው በአበኔር የመቃብር ቦታ ቀበሩት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ