የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • የፍሬ በኩራትን መባ አድርጎ ማቅረብ (1-11)

      • ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጥ አሥራት (12-15)

      • እስራኤል የይሖዋ ልዩ ንብረት ነው (16-19)

ዘዳግም 26:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:19፤ ዘሌ 23:10፤ ዘኁ 18:8, 12፤ 2ዜና 6:6፤ 31:5፤ ምሳሌ 3:9

ዘዳግም 26:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 17:1, 8፤ 26:3

ዘዳግም 26:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ሊጠፋ የሚችል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:5፤ ሆሴዕ 12:12
  • +ዘፍ 46:3፤ ሥራ 7:15
  • +ዘፍ 46:27
  • +ዘፀ 1:7፤ ዘዳ 10:22፤ መዝ 105:24

ዘዳግም 26:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 1:11

ዘዳግም 26:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:9፤ 4:31፤ ሥራ 7:34

ዘዳግም 26:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:6
  • +ዘፀ 7:3፤ ዘዳ 4:33, 34

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2015፣ ገጽ 4-5

ዘዳግም 26:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7, 8፤ ሕዝ 20:6

ዘዳግም 26:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 26:2

ዘዳግም 26:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:7፤ 16:14

ዘዳግም 26:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወላጅ አልባ ለሆነው።”

  • *

    ቃል በቃል “በደጆችህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:5, 6፤ 14:22
  • +ዘዳ 14:28, 29፤ ምሳሌ 14:21፤ 1ዮሐ 3:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 2

ዘዳግም 26:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 1:27

ዘዳግም 26:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18፤ 26:3
  • +ዘፀ 23:25፤ ዘዳ 8:7, 8

ዘዳግም 26:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:6፤ 11:1፤ መዝ 119:34፤ 1ዮሐ 5:3

ዘዳግም 26:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:46
  • +መክ 12:13
  • +ዘሌ 19:37

ዘዳግም 26:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውድ ሀብቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:2፤ 29:10-13

ዘዳግም 26:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:6፤ 28:1, 9
  • +ዘዳ 4:8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 26:2ዘፀ 23:19፤ ዘሌ 23:10፤ ዘኁ 18:8, 12፤ 2ዜና 6:6፤ 31:5፤ ምሳሌ 3:9
ዘዳ. 26:3ዘፍ 17:1, 8፤ 26:3
ዘዳ. 26:5ዘፍ 28:5፤ ሆሴዕ 12:12
ዘዳ. 26:5ዘፍ 46:3፤ ሥራ 7:15
ዘዳ. 26:5ዘፍ 46:27
ዘዳ. 26:5ዘፀ 1:7፤ ዘዳ 10:22፤ መዝ 105:24
ዘዳ. 26:6ዘፀ 1:11
ዘዳ. 26:7ዘፀ 3:9፤ 4:31፤ ሥራ 7:34
ዘዳ. 26:8ዘፀ 6:6
ዘዳ. 26:8ዘፀ 7:3፤ ዘዳ 4:33, 34
ዘዳ. 26:9ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7, 8፤ ሕዝ 20:6
ዘዳ. 26:10ዘዳ 26:2
ዘዳ. 26:11ዘዳ 12:7፤ 16:14
ዘዳ. 26:12ዘዳ 12:5, 6፤ 14:22
ዘዳ. 26:12ዘዳ 14:28, 29፤ ምሳሌ 14:21፤ 1ዮሐ 3:17
ዘዳ. 26:13ያዕ 1:27
ዘዳ. 26:15ዘፍ 15:18፤ 26:3
ዘዳ. 26:15ዘፀ 23:25፤ ዘዳ 8:7, 8
ዘዳ. 26:16ዘዳ 6:6፤ 11:1፤ መዝ 119:34፤ 1ዮሐ 5:3
ዘዳ. 26:17ዘሌ 26:46
ዘዳ. 26:17መክ 12:13
ዘዳ. 26:17ዘሌ 19:37
ዘዳ. 26:18ዘዳ 14:2፤ 29:10-13
ዘዳ. 26:19ዘዳ 7:6፤ 28:1, 9
ዘዳ. 26:19ዘዳ 4:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 26:1-19

ዘዳግም

26 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ስትወርስና በዚያ መኖር ስትጀምር 2 አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ይኸውም ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬ ሁሉ በኩር የሆነውን ወስደህ በቅርጫት ውስጥ በማድረግ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።+ 3 በወቅቱ ወደሚያገለግለው ካህን ሄደህ ‘ይሖዋ ለእኛ ለመስጠት ለአባቶቻችን ወደማለላቸው ምድር መግባቴን ዛሬ ለአምላክህ ለይሖዋ አሳውቃለሁ’ በለው።+

4 “ከዚያም ካህኑ ቅርጫቱን ከእጅህ ላይ ወስዶ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ፊት ያስቀምጠዋል። 5 አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን* አራማዊ+ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ+ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ+ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ።+ 6 ግብፃውያንም ክፉኛ ያንገላቱንና ይጨቁኑን እንዲሁም በላያችን ላይ ከባድ የባርነት ቀንበር ይጭኑብን ነበር።+ 7 እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ ይሖዋም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጉስቁልናችንን፣ መከራችንንና የደረሰብንን ጭቆናም ተመለከተ።+ 8 በመጨረሻም ይሖዋ በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ፣+ አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ እንዲሁም ድንቅ ምልክቶችን በማሳየትና ተአምራትን በመፈጸም ከግብፅ አወጣን።+ 9 ከዚያም ወደዚህ ስፍራ አምጥቶ ይህችን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ሰጠን።+ 10 ይኸው አሁን ይሖዋ የሰጠኝ ምድር ካፈራችው ፍሬ በኩር የሆነውን አምጥቻለሁ።’+

“ይህን በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ስገድ። 11 ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው አምላክህ ይሖዋ ለአንተና ለቤተሰብህ በሰጠው መልካም ነገር ሁሉ ትደሰታላችሁ።+

12 “የአሥራት ዓመት በሆነው በሦስተኛው ዓመት የምርትህን አንድ አሥረኛ አሥራት+ እንዲሆን ለይተህ ካስቀመጥክ በኋላ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለቲቱ ትሰጣለህ፤ እነሱም በከተሞችህ* ውስጥ እስኪጠግቡ ድረስ ይበሉታል።+ 13 ከዚያም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ትላለህ፦ ‘በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ቅዱስ የሆነውን ነገር ከቤት አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ+ ሰጥቻለሁ። ትእዛዛትህን አልጣስኩም ወይም ችላ አላልኩም። 14 ሐዘን ላይ በተቀመጥኩበት ጊዜ ከእሱ አልበላሁም፤ ወይም ረክሼ ባለሁበት ጊዜ ከእሱ ላይ ምንም ነገር አላነሳሁም፤ አሊያም ለሞተ ሰው ከእሱ ላይ ምንም ነገር አልሰጠሁም። የአምላኬን የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ፤ ያዘዝከኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15 እንግዲህ አሁን ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማያት ሆነህ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረት+ የሰጠኸንን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ባርክ።’+

16 “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል። አንተም በሙሉ ልብህና+ በሙሉ ነፍስህ* ፈጽማቸው፤ ጠብቃቸውም። 17 ይሖዋ በመንገዶቹ ከሄድክ እንዲሁም ሥርዓቶቹን፣+ ትእዛዛቱንና+ ድንጋጌዎቹን+ ከጠበቅክና ቃሉን ከሰማህ አምላክህ እንደሚሆን ዛሬ ነግሮሃል። 18 አንተም ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ሕዝቡ ማለትም ልዩ ንብረቱ*+ እንደምትሆንና ትእዛዛቱን በሙሉ እንደምትጠብቅ የተናገርከውን ቃል በዛሬው ዕለት ሰምቷል፤ 19 አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ+ ሆነህ ስትገኝ እሱ ደግሞ በገባው ቃል መሠረት ውዳሴ፣ ዝናና ክብር በማጎናጸፍ፣ ከፈጠራቸው ሌሎች ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ