የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • የኃጢአት መባ (1-35)

ዘሌዋውያን 4:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማንኛውም ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:17፤ ዘኁ 15:27, 28

ዘሌዋውያን 4:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 8:12፤ 21:10
  • +ዘኁ 12:1, 11
  • +ዕብ 5:1-3፤ 7:27

ዘሌዋውያን 4:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 6:25
  • +ዘፀ 29:10, 11

ዘሌዋውያን 4:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:30

ዘሌዋውያን 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 8:15, 16
  • +ዘሌ 16:14, 19

ዘሌዋውያን 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:10
  • +ዘሌ 5:9

ዘሌዋውያን 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 9:8, 10

ዘሌዋውያን 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:3, 4

ዘሌዋውያን 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:14

ዘሌዋውያን 4:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በስብ የራሰው አመድ።” መሥዋዕት ሆነው በሚቀርቡት እንስሳት ስብ የራሰውን አመድ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 8:14, 17፤ ዕብ 13:11

ዘሌዋውያን 4:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 7:11
  • +ዘኁ 15:22-24

ዘሌዋውያን 4:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 26:31፤ 40:21፤ ዕብ 10:19, 20

ዘሌዋውያን 4:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:1, 6
  • +ዘፀ 27:1፤ 40:6

ዘሌዋውያን 4:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:16

ዘሌዋውያን 4:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:30፤ ዘሌ 16:17፤ ዘኁ 15:25፤ ኤፌ 1:7፤ ዕብ 2:17

ዘሌዋውያን 4:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 4:11, 12
  • +ዘሌ 16:15፤ 1ዮሐ 2:1, 2

ዘሌዋውያን 4:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:21

ዘሌዋውያን 4:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:10, 11፤ 6:25፤ 7:2

ዘሌዋውያን 4:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 9:8, 9፤ 16:18፤ ዕብ 9:22
  • +ዘሌ 8:15

ዘሌዋውያን 4:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:3-5

ዘሌዋውያን 4:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 15:27-29

ዘሌዋውያን 4:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:10, 11፤ 6:25

ዘሌዋውያን 4:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 4:25፤ 8:15፤ 9:8, 9፤ ዕብ 9:22

ዘሌዋውያን 4:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:16
  • +ዘሌ 3:3, 4

ዘሌዋውያን 4:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:10, 11

ዘሌዋውያን 4:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 4:25፤ 16:18

ዘሌዋውያን 4:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:13, 14፤ ዘሌ 3:3, 4፤ 6:12፤ 9:8, 10
  • +ዘኁ 15:28፤ 1ዮሐ 1:7፤ 2:1, 2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 4:2ዘሌ 5:17፤ ዘኁ 15:27, 28
ዘሌ. 4:3ዘሌ 8:12፤ 21:10
ዘሌ. 4:3ዘኁ 12:1, 11
ዘሌ. 4:3ዕብ 5:1-3፤ 7:27
ዘሌ. 4:4ዘሌ 6:25
ዘሌ. 4:4ዘፀ 29:10, 11
ዘሌ. 4:5ዘፀ 30:30
ዘሌ. 4:6ዘሌ 8:15, 16
ዘሌ. 4:6ዘሌ 16:14, 19
ዘሌ. 4:7ዘፀ 30:10
ዘሌ. 4:7ዘሌ 5:9
ዘሌ. 4:9ዘሌ 9:8, 10
ዘሌ. 4:10ዘሌ 3:3, 4
ዘሌ. 4:11ዘፀ 29:14
ዘሌ. 4:12ዘሌ 8:14, 17፤ ዕብ 13:11
ዘሌ. 4:13ኢያሱ 7:11
ዘሌ. 4:13ዘኁ 15:22-24
ዘሌ. 4:17ዘፀ 26:31፤ 40:21፤ ዕብ 10:19, 20
ዘሌ. 4:18ዘፀ 30:1, 6
ዘሌ. 4:18ዘፀ 27:1፤ 40:6
ዘሌ. 4:19ዘሌ 3:16
ዘሌ. 4:20ዘፀ 32:30፤ ዘሌ 16:17፤ ዘኁ 15:25፤ ኤፌ 1:7፤ ዕብ 2:17
ዘሌ. 4:21ዘሌ 4:11, 12
ዘሌ. 4:21ዘሌ 16:15፤ 1ዮሐ 2:1, 2
ዘሌ. 4:22ዘፀ 18:21
ዘሌ. 4:24ዘሌ 1:10, 11፤ 6:25፤ 7:2
ዘሌ. 4:25ዘሌ 9:8, 9፤ 16:18፤ ዕብ 9:22
ዘሌ. 4:25ዘሌ 8:15
ዘሌ. 4:26ዘሌ 3:3-5
ዘሌ. 4:27ዘኁ 15:27-29
ዘሌ. 4:29ዘሌ 1:10, 11፤ 6:25
ዘሌ. 4:30ዘሌ 4:25፤ 8:15፤ 9:8, 9፤ ዕብ 9:22
ዘሌ. 4:31ዘሌ 3:16
ዘሌ. 4:31ዘሌ 3:3, 4
ዘሌ. 4:33ዘሌ 1:10, 11
ዘሌ. 4:34ዘሌ 4:25፤ 16:18
ዘሌ. 4:35ዘፀ 29:13, 14፤ ዘሌ 3:3, 4፤ 6:12፤ 9:8, 10
ዘሌ. 4:35ዘኁ 15:28፤ 1ዮሐ 1:7፤ 2:1, 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 4:1-35

ዘሌዋውያን

4 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው* ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ+ ኃጢአት ቢሠራ እንዲህ መደረግ ይኖርበታል፦

3 “‘የተቀባው ካህን+ ኃጢአት+ ቢሠራና ሕዝቡ በደለኛ እንዲሆን ቢያደርግ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለበትን ወይፈን የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያቅርብ።+ 4 ወይፈኑን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ+ ወደ ይሖዋ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፤ ወይፈኑንም በይሖዋ ፊት ያርደዋል።+ 5 ከዚያም የተቀባው ካህን+ ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል፤ 6 ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ+ ደሙን በቅዱሱ ስፍራ መጋረጃ ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ 7 በተጨማሪም ካህኑ ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን የወይፈኑን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።+

8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ 10 ይህም ለኅብረት መሥዋዕት+ ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።

11 “‘ሆኖም የወይፈኑን ቆዳ እንዲሁም ሥጋውን በሙሉ ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹ፣ ከሆድ ዕቃውና ከፈርሱ ጋር+ 12 እንዲሁም ከወይፈኑ የቀረውን በሙሉ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል፤ በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ አድርጎም ያቃጥለዋል።+ አመዱ በሚደፋበት ቦታ ላይ ይቃጠል።

13 “‘መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራቱ በደለኛ ቢሆንና+ ጉባኤው ግን ይሖዋ አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን መፈጸሙን ባይገነዘብ፣+ 14 በኋላም ኃጢአቱ ቢታወቅ ጉባኤው ለኃጢአት መባ የሚሆን ወይፈን ያቅርብ፤ ወደ መገናኛ ድንኳኑም ፊት ያምጣው። 15 የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች በይሖዋ ፊት እጃቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በይሖዋ ፊት ይታረዳል።

16 “‘ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል። 17 ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ የተወሰነውን በመጋረጃው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ 18 የተወሰነውንም ደም ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።+ 19 ስቡንም በሙሉ አንስቶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል።+ 20 በወይፈኑ ላይ ለኃጢአት መባ እንዲሆን በቀረበው በሌላኛው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ ያደርጋል። በዚህኛውም ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ይሆናል፤ ካህኑም ለእነሱ ያስተሰርይላቸዋል፤+ እነሱም ይቅር ይባላሉ። 21 ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ እንዲወሰድ ካደረገ በኋላ ልክ የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለው ሁሉ ይሄኛውንም ያቃጥለዋል።+ ይህ ስለ ጉባኤው የሚቀርብ የኃጢአት መባ ነው።+

22 “‘አንድ አለቃ+ አምላኩ ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ሠርቶ በደለኛ ቢሆን 23 ወይም ትእዛዙን በመተላለፍ ኃጢአት እንደሠራ ቢያውቅ እንከን የሌለበትን ተባዕት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። 24 እጁንም በፍየል ጠቦቱ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም የሚቃጠለው መባ በይሖዋ ፊት ዘወትር በሚታረድበት ስፍራ ያርደዋል።+ ይህ የኃጢአት መባ ነው። 25 ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደሙን የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሳል።+ 26 ስቡንም በሙሉ ልክ እንደ ኅብረት መሥዋዕቱ ስብ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል፤+ ካህኑም የእሱን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

27 “‘በምድሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ማንኛውም ሰው* ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣+ 28 በኋላም የሠራውን ኃጢአት ቢያውቅ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለባትን እንስት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። 29 እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም ለኃጢአት መባ የቀረበችውን እንስሳ የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ ያርዳታል።+ 30 ካህኑም ከደሙ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል።+ 31 ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ ስቡ+ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤+ ካህኑም ስቡ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዲሰጥ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

32 “‘ሆኖም የኃጢአት መባ አድርጎ የሚያቀርበው የበግ ጠቦት ከሆነ እንከን የሌለባትን እንስት የበግ ጠቦት ማምጣት አለበት። 33 እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም እንስሳዋን የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአት መባ አድርጎ ያርዳታል።+ 34 ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበችው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። 35 የኅብረት መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው የበግ ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ እሱም በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።+ ካህኑም ሰውየው የሠራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ