የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • ንጹሕና ርኩስ እንስሳት (1-47)

ዘሌዋውያን 11:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከየብስ እንስሳት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:4-6፤ ሕዝ 4:14

ዘሌዋውያን 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:7, 8

ዘሌዋውያን 11:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 30:26

ዘሌዋውያን 11:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ማመራመር፣ ገጽ 61

ዘሌዋውያን 11:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 65:4፤ 66:3, 17

ዘሌዋውያን 11:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 12/2020፣ ገጽ 2

ዘሌዋውያን 11:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:9, 10

ዘሌዋውያን 11:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳት።”

ዘሌዋውያን 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:3

ዘሌዋውያን 11:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 39:27, 30
  • +ዘዳ 14:12-19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 2-3

ዘሌዋውያን 11:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

ዘሌዋውያን 11:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 3:4፤ ማር 1:6

ዘሌዋውያን 11:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 14:46, 47፤ 15:8፤ 17:15፤ 22:4-6

ዘሌዋውያን 11:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 14:2, 8፤ 15:2, 5፤ ዘኁ 19:10

ዘሌዋውያን 11:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:7, 8

ዘሌዋውያን 11:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:15, 16
  • +ዘሌ 5:2

ዘሌዋውያን 11:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 66:17

ዘሌዋውያን 11:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:19
  • +ዘሌ 11:24፤ 22:4, 5

ዘሌዋውያን 11:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 15:12

ዘሌዋውያን 11:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:23, 24፤ ዘኁ 19:11, 16

ዘሌዋውያን 11:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:15፤ 22:3, 8፤ ዘዳ 14:21፤ ሕዝ 4:14፤ 44:31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2005፣ ገጽ 27

ዘሌዋውያን 11:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:21

ዘሌዋውያን 11:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 14:3

ዘሌዋውያን 11:43

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:25

ዘሌዋውያን 11:44

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:2
  • +1ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8
  • +ዘፀ 19:6፤ ዘሌ 19:2፤ ዘዳ 14:2፤ 1ተሰ 4:7

ዘሌዋውያን 11:45

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 6:7፤ 29:46፤ ሆሴዕ 11:1
  • +ዘሌ 20:7, 26፤ ኢያሱ 24:19፤ 1ሳሙ 2:2
  • +ዘፀ 22:31፤ ዘኁ 15:40፤ ዘዳ 7:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2004፣ ገጽ 23

ዘሌዋውያን 11:46

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 2-3

ዘሌዋውያን 11:47

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:25፤ ሕዝ 44:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 1/2021፣ ገጽ 2-3

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 11:2ዘዳ 14:4-6፤ ሕዝ 4:14
ዘሌ. 11:4ዘዳ 14:7, 8
ዘሌ. 11:5ምሳሌ 30:26
ዘሌ. 11:7ኢሳ 65:4፤ 66:3, 17
ዘሌ. 11:8ሥራ 10:14
ዘሌ. 11:9ዘዳ 14:9, 10
ዘሌ. 11:11ዘዳ 14:3
ዘሌ. 11:13ኢዮብ 39:27, 30
ዘሌ. 11:13ዘዳ 14:12-19
ዘሌ. 11:22ማቴ 3:4፤ ማር 1:6
ዘሌ. 11:24ዘሌ 14:46, 47፤ 15:8፤ 17:15፤ 22:4-6
ዘሌ. 11:25ዘሌ 14:2, 8፤ 15:2, 5፤ ዘኁ 19:10
ዘሌ. 11:26ዘዳ 14:7, 8
ዘሌ. 11:28ዘሌ 17:15, 16
ዘሌ. 11:28ዘሌ 5:2
ዘሌ. 11:29ኢሳ 66:17
ዘሌ. 11:31ዘዳ 14:19
ዘሌ. 11:31ዘሌ 11:24፤ 22:4, 5
ዘሌ. 11:33ዘሌ 15:12
ዘሌ. 11:39ዘሌ 11:23, 24፤ ዘኁ 19:11, 16
ዘሌ. 11:40ዘሌ 17:15፤ 22:3, 8፤ ዘዳ 14:21፤ ሕዝ 4:14፤ 44:31
ዘሌ. 11:41ዘሌ 11:21
ዘሌ. 11:42ዘዳ 14:3
ዘሌ. 11:43ዘሌ 20:25
ዘሌ. 11:44ዘፀ 20:2
ዘሌ. 11:441ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8
ዘሌ. 11:44ዘፀ 19:6፤ ዘሌ 19:2፤ ዘዳ 14:2፤ 1ተሰ 4:7
ዘሌ. 11:45ዘፀ 6:7፤ 29:46፤ ሆሴዕ 11:1
ዘሌ. 11:45ዘሌ 20:7, 26፤ ኢያሱ 24:19፤ 1ሳሙ 2:2
ዘሌ. 11:45ዘፀ 22:31፤ ዘኁ 15:40፤ ዘዳ 7:6
ዘሌ. 11:47ዘሌ 20:25፤ ሕዝ 44:23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 11:1-47

ዘሌዋውያን

11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፦ ‘በምድር ላይ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት* መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦+ 3 ሰኮናው የተሰነጠቀውንና ስንጥቁም ሙሉ በሙሉ የተከፈለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ።

4 “‘ሆኖም የሚያመሰኩትን ወይም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እነዚህን እንስሳት መብላት የለባችሁም፦ ግመል የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው።+ 5 ሽኮኮም+ መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 6 ጥንቸልም ብትሆን መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የምታመሰኳ ብትሆንም ሰኮናዋ የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነች። 7 አሳማም+ መብላት የለባችሁም፤ ሰኮናው የተሰነጠቀና ስንጥቁ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ቢሆንም እንኳ አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 8 የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ ወይም በድናቸውን አትንኩ። እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+

9 “‘በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ በባሕርም ሆነ በወንዞች፣ በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ 10 በውኃዎች ውስጥ ካሉ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት* ሁሉ መካከል በባሕርና በወንዞች ውስጥ የሚገኙ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ግን ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 11 አዎ፣ እነዚህን ልትጸየፏቸው ይገባል፤ ሥጋቸውን ፈጽሞ አትብሉ፤+ በድናቸውንም ተጸየፉት። 12 በውኃዎች ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው።

13 “‘ልትጸየፏቸው የሚገቡ በራሪ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፤ አስጸያፊ በመሆናቸው መበላት የለባቸውም፦ ንስር፣+ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ 14 ቀይ ጭልፊት፣ ማንኛውም ዓይነት ጥቁር ጭልፊት፣ 15 ማንኛውም ዓይነት ቁራ፣ 16 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ፣ ማንኛውም ዓይነት ሲላ፣ 17 ትንሿ ጉጉት፣ ለማሚት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ 18 ዝይ፣ ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ 19 ራዛ፣ ማንኛውም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 20 በአራቱም እግሩ የሚሄድ ክንፍ ያለው የሚርመሰመስ ፍጡር* ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ነው።

21 “‘በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ክንፍ ካላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት መካከል መብላት የምትችሉት ከእግሮቻቸው በላይ በመሬት ላይ ለመፈናጠር የሚያገለግል የሚተጣጠፍ ቅልጥም ያላቸውን ብቻ ነው። 22 ከእነዚህም መካከል የሚከተሉትን መብላት ትችላላችሁ፦ የተለያየ ዓይነት የሚፈልስ አንበጣ፣ ሌሎች የሚበሉ አንበጦች፣+ እንጭራሪቶችና ፌንጣዎች። 23 አራት እግር ኖሯቸው ክንፍ ያላቸው ሌሎች የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 24 በእነዚህ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ 25 ከእነዚህ መካከል የማናቸውንም በድን የሚያነሳ ሁሉ ልብሶቹን ይጠብ፤+ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።

26 “‘ሰኮናው የተሰነጠቀ፣ ስንጥቁ ግን ሙሉ በሙሉ ያልተከፈለ እንዲሁም የማያመሰኳ ማንኛውም እንስሳ ለእናንተ ርኩስ ነው። የሚነካቸውም ሁሉ ርኩስ ይሆናል።+ 27 በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ፍጥረታት መካከል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 28 በድናቸውን የሚያነሳ ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤+ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።

29 “‘ለእናንተ ርኩስ የሆኑት በምድር ላይ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፦ ፍልፈል፣ አይጥ፣+ ማንኛውም ዓይነት እንሽላሊት፣ 30 ጌኮ፣ ገበሎ፣ የውኃ እንሽላሊት፣ የአሸዋ እንሽላሊትና እስስት። 31 እነዚህ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+

32 “‘በሚሞቱበት ጊዜ የወደቁበት ማንኛውም ነገር ይኸውም የእንጨት ዕቃም ሆነ ልብስ ወይም ቆዳ አሊያም ደግሞ በርኖስ ርኩስ ይሆናል። አገልግሎት ላይ የሚውል ማንኛውም ዕቃ ውኃ ውስጥ ይነከር፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም ይነጻል። 33 በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከወደቁ ዕቃውን ሰባብሩት፤ በውስጡ ያለውም ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል።+ 34 እንዲህ ባለ ዕቃ ውስጥ የነበረ ውኃ የነካው ማንኛውም ዓይነት ምግብ ርኩስ ይሆናል፤ በእንዲህ ዓይነቱ ዕቃ ውስጥ የነበረ የሚጠጣ ማንኛውም ዓይነት መጠጥም ርኩስ ይሆናል። 35 በድናቸው የወደቀበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። መጋገሪያ ምድጃም ይሁን አነስተኛ ምድጃ ይሰበር። እነዚህ ነገሮች ርኩስ ናቸው፤ ለእናንተም ርኩስ ይሆናሉ። 36 ምንጭና የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ብቻ ንጹሕ ይሆናሉ፤ ይሁንና በድኑን የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል። 37 በድናቸው በሚዘራ ዘር ላይ ቢወድቅ ዘሩ ንጹሕ ነው። 38 ይሁንና በዘሩ ላይ ውኃ ተደርጎበት ሳለ የበድናቸው አንዱ ክፍል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ ለእናንተ ርኩስ ይሆናል።

39 “‘እንድትበሉ ከተፈቀደላችሁ እንስሳ አንዱ ቢሞት የእንስሳውን በድን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ 40 ከበድኑ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ በድኑን ያነሳ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 41 በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት አስጸያፊ ነው።+ መበላት የለበትም። 42 በሆዱ የሚሳብን ማንኛውም ፍጥረት፣ በአራቱም እግሩ የሚሄድን ማንኛውም ፍጥረት ወይም ብዙ እግሮች ያሉትን በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም አስጸያፊ ናቸው።+ 43 በምድር ላይ በሚርመሰመስ በማንኛውም ፍጥረት ራሳችሁን* አስጸያፊ አታድርጉ፤ በእነሱም ራሳችሁን በመበከል አትርከሱ።+ 44 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ራሳችሁን ልትቀድሱና ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የሚርመሰመስ ፍጥረት ራሳችሁን* አታርክሱ። 45 አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ቅዱሳን መሆን አለባችሁ።+

46 “‘እንስሳትን፣ የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ በውኃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስን ማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር* እንዲሁም በምድር ላይ የሚርመሰመስን ፍጡር* ሁሉ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ 47 ርኩስ የሆነውንና ንጹሕ የሆነውን እንዲሁም ለመብል የሚሆነውንና ለመብል የማይሆነውን ሕያው ፍጡር ለመለየት ሕጉ ይህ ነው።’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ