ኤርምያስ
ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?+
ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው?
2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነሱም ሥር ሰደዋል።
አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል።
ከከንፈራቸው አይለዩህም፤ የውስጥ ሐሳባቸው* ግን ከአንተ የራቀ ነው።+
ለእርድ እንደተዘጋጁ በጎች ለያቸው፤
ለሚገደሉበትም ቀን ለይተህ አቆያቸው።
4 ምድሪቱ ተራቁታ፣
የሜዳውም ተክል ሁሉ ደርቆ የሚቆየው እስከ መቼ ድረስ ነው?+
በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳ
አራዊቱና ወፎቹ ተጠራርገው ጠፉ።
እነሱ፣ “ወደፊት ምን እንደሚገጥመን አያውቅም” ብለዋልና።
በሰላም ምድር ተማምነህ ብትቀመጥ እንኳ
ጥቅጥቅ ባለው የዮርዳኖስ ጥሻ ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?
6 የገዛ ወንድሞችህ፣
የገዛ አባትህ ቤተሰቦች እንኳ አታለውሃልና።+
እነሱ በአንተ ላይ ጮኸዋል።
መልካም ነገር ቢናገሩህ እንኳ
ፈጽሞ አትመናቸው።
እጅግ የምወዳትን* በጠላቶቿ እጅ አሳልፌ ሰጥቻታለሁ።+
8 ርስቴ በጫካ ውስጥ እንዳለ አንበሳ ሆነችብኝ።
በእኔ ላይ ጮኻብኛለች።
በዚህም የተነሳ ጠላኋት።
እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑ፤ በአንድነት ተሰብሰቡ፤
ትቀራመቷት ዘንድ ኑ።+
የተወደደውን ይዞታዬን ጠፍ ምድረ በዳ አድርገውታል።
11 ባድማ ሆኗል።
ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች፤
ይሁንና ይህን ልብ ያለ አንድም ሰው የለም።+
12 በምድረ በዳ ባሉት፣ በተበላሹ መንገዶች ሁሉ አጥፊዎች መጥተዋል፤
የይሖዋ ሰይፍ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ ምድሪቱን ትበላለችና።+
ማንም ሰው* ሰላም የለውም።
13 ስንዴ ዘሩ፤ ሆኖም እሾህን አጨዱ።+
እስኪዝሉ ድረስ ሠሩ፤ ነገር ግን ምንም ጥቅም አላገኙም።
ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ የተነሳ
በሚያገኙት ምርት ያፍራሉ።”
14 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርሰው ያደረግኩትን ርስት የሚነኩ ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ+ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤+ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ። 15 ከነቀልኳቸው በኋላ ግን ዳግመኛ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውን ወደየርስታቸው፣ እያንዳንዳቸውንም ወደየምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።”
16 “ሕዝቤን በባአል እንዲምሉ እንዳስተማሩ ሁሉ እነሱም የሕዝቤን መንገድ በእርግጥ ቢማሩና ‘ሕያው ይሖዋን!’ ብለው በስሜ ቢምሉ በሕዝቤ መካከል ጸንተው ይኖራሉ። 17 ይሁንና ከእነዚህ ብሔራት መካከል የማይታዘዝ ቢኖር ያን ብሔር እነቅለዋለሁ፤ ነቅዬም አጠፋዋለሁ” ይላል ይሖዋ።+