የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 38
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ (1-6)

      • ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን አዳነው (7-13)

      • ኤርምያስ፣ እጁን እንዲሰጥ ሴዴቅያስን አሳሰበው (14-28)

ኤርምያስ 38:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:3
  • +ኤር 21:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    6/2009፣ ገጽ 29

    11/2007፣ ገጽ 16

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2006፣ ገጽ 14-15

ኤርምያስ 38:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በበሽታ።”

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ከለዳውያን የሚወጣ።”

  • *

    ወይም “ነፍሱ።”

  • *

    ወይም “ሕይወቱን ያተርፋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 27:13፤ 29:18፤ ሕዝ 7:15
  • +ኤር 21:8-10

ኤርምያስ 38:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:1, 2፤ 2ዜና 36:17

ኤርምያስ 38:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:11

ኤርምያስ 38:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 33:1፤ 37:21፤ 38:28

ኤርምያስ 38:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:16
  • +ኤር 37:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 31

ኤርምያስ 38:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

ኤርምያስ 38:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 52:6

ኤርምያስ 38:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 20:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 31

ኤርምያስ 38:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:21

ኤርምያስ 38:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይህችን ነፍስ በፈጠረልን።”

  • *

    ወይም “ነፍስህን ለሚሿት።”

ኤርምያስ 38:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ብትወጣ።”

  • *

    ወይም “ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:9፤ 27:12

ኤርምያስ 38:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት የማትወጣ ከሆነ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:8, 9
  • +2ነገ 25:6፤ ኤር 39:5

ኤርምያስ 38:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች።”

ኤርምያስ 38:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ለመውጣት።”

ኤርምያስ 38:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

  • *

    ቃል በቃል “የሰላምህ ሰዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:3
  • +ሰቆ 1:2

ኤርምያስ 38:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:7
  • +ኤር 52:8, 13

ኤርምያስ 38:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 38:4

ኤርምያስ 38:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:15

ኤርምያስ 38:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:20፤ 32:2፤ 33:1፤ 37:21፤ 39:13, 14
  • +2ነገ 25:8, 9፤ 2ዜና 36:17

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 38:1ኤር 37:3
ኤር. 38:1ኤር 21:1, 2
ኤር. 38:2ኤር 27:13፤ 29:18፤ ሕዝ 7:15
ኤር. 38:2ኤር 21:8-10
ኤር. 38:32ነገ 25:1, 2፤ 2ዜና 36:17
ኤር. 38:4ኤር 26:11
ኤር. 38:6ኤር 33:1፤ 37:21፤ 38:28
ኤር. 38:7ኤር 39:16
ኤር. 38:7ኤር 37:13
ኤር. 38:9ኤር 52:6
ኤር. 38:112ነገ 20:13
ኤር. 38:13ኤር 37:21
ኤር. 38:17ኤር 21:9፤ 27:12
ኤር. 38:182ነገ 25:8, 9
ኤር. 38:182ነገ 25:6፤ ኤር 39:5
ኤር. 38:22ኤር 39:3
ኤር. 38:22ሰቆ 1:2
ኤር. 38:232ነገ 25:7
ኤር. 38:23ኤር 52:8, 13
ኤር. 38:25ኤር 38:4
ኤር. 38:26ኤር 37:15
ኤር. 38:28ኤር 15:20፤ 32:2፤ 33:1፤ 37:21፤ 39:13, 14
ኤር. 38:282ነገ 25:8, 9፤ 2ዜና 36:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 38:1-28

ኤርምያስ

38 የማታን ልጅ ሰፋጥያህ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሸሌምያህ ልጅ ዩካልና+ የማልኪያህ ልጅ ጳስኮር፣+ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን የሚከተለውን ቃል ሰሙ፦ 2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታል።+ ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ* ግን ይተርፋል፤ ሕይወቱ * እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤* በሕይወትም ይኖራል።’+ 3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት መሰጠቷ አይቀርም፤ እሱም ይይዛታል።’”+

4 መኳንንቱ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው እንዲህ ያለ ቃል በመናገር በዚህች ከተማ ውስጥ የቀሩትን ወታደሮችና የሕዝቡን ሁሉ ወኔ* እያዳከመ ስለሆነ እባክህ አስገድለው።+ ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ጥፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝምና።” 5 ንጉሥ ሴዴቅያስም “እነሆ፣ እሱ በእጃችሁ ነው፤ ንጉሡ እናንተን ለማስቆም ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልምና” ሲል መለሰላቸው።

6 እነሱም ኤርምያስን ወስደው በክብር ዘቦቹ ግቢ+ በሚገኘው በንጉሡ ልጅ በማልኪያህ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ኤርምያስን በገመድ ወደ ጉድጓዱ አወረዱት። በጉድጓዱ ውስጥም ጭቃ ብቻ እንጂ ውኃ አልነበረም፤ ኤርምያስም ጭቃው ውስጥ መስመጥ ጀመረ።

7 በንጉሡ ቤት* የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ* ኤቤድሜሌክ+ ኤርምያስን በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ እንደጣሉት ሰማ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በቢንያም በር ተቀምጦ ነበር፤+ 8 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ከንጉሡ ቤት* ወጥቶ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ 9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ ኤርምያስ ላይ ክፉ ነገር ፈጽመዋል! በውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጥለውታል፤ ከረሃቡም የተነሳ እዚያው ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ዳቦ የሚባል ነገር የለምና።”+

10 ከዚያም ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን ኤቤድሜሌክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከዚህ 30 ሰዎች ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ከመሞቱ በፊት ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ጎትተህ አውጣው።” 11 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ሰዎቹን ይዞ በንጉሡ ቤት* ከግምጃ ቤቱ+ ሥር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ ከዚያም የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ከዚያ ወስደው በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ላለው ለኤርምያስ በገመድ አወረዱለት። 12 ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን “ይህን የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ በብብትህና በገመዱ መካከል አድርገው” አለው። ኤርምያስም እንደተባለው አደረገ፤ 13 እነሱም ኤርምያስን በገመዱ ጎትተው ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ አወጡት። ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ።

14 ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰው ልኮ ነቢዩ ኤርምያስን እሱ ወዳለበት፣ በይሖዋ ቤት ወደሚገኘው ወደ ሦስተኛው መግቢያ አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን “አንድ ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ምንም ነገር እንዳትደብቀኝ” አለው። 15 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ሴዴቅያስን “ብነግርህ ትገድለኛለህ። ብመክርህም አትሰማኝም” አለው። 16 ንጉሥ ሴዴቅያስም በሚስጥር ለኤርምያስ እንዲህ ሲል ማለለት፦ “ይህን ሕይወት በሰጠን* ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አልገድልህም፤ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹት* ለእነዚህ ሰዎችም አሳልፌ አልሰጥህም።”

17 ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ* ሕይወትህ ትተርፋለች፤* ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ።+ 18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ* ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+

19 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ኤርምያስን “ወደ ከለዳውያን የኮበለሉትን አይሁዳውያን እፈራለሁ፤ ለእነሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደሆነ ሊያሠቃዩኝ ይችላሉ” አለው። 20 ኤርምያስ ግን እንዲህ አለው፦ “ለእነሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እባክህ የምነግርህን የይሖዋን ቃል ታዘዝ፤ መልካምም ይሆንልሃል፤ በሕይወትም ትኖራለህ።* 21 እጅህን ለመስጠት* ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ይሖዋ የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፦ 22 እነሆ፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤት* የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ይወሰዳሉ፤+ እነሱም እንዲህ ይላሉ፦

‘ተማምነህባቸው የነበሩት ሰዎች* አታለውሃል፤ ደግሞም አሸንፈውሃል።+

እግርህ ጭቃ ውስጥ እንዲሰምጥ አድርገዋል።

አሁን አፈግፍገው ተመልሰዋል።’

23 “ሚስቶችህንና ወንዶች ልጆችህን ሁሉ ለከለዳውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይልቁንም የባቢሎን ንጉሥ ይይዝሃል፤+ በአንተም ምክንያት ይህች ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”+

24 ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “ስለዚህ ጉዳይ ማንም ሰው እንዳይሰማ፤ አለዚያ ትሞታለህ። 25 መኳንንቱ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርኩ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና ‘ለንጉሡ የነገርከውን ነገር እስቲ ንገረን። ምንም ነገር አትደብቀን፤ እኛም አንገድልህም።+ ንጉሡ የነገረህ ምንድን ነው?’ ቢሉህ፣ 26 ‘በዚያ እንዳልሞት ንጉሡ ወደ የሆናታን ቤት መልሶ እንዳይልከኝ ስለምነው ነበር’ በላቸው።”+

27 በኋላም መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት። እሱም ንጉሡ እንዲናገር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። እነሱም ከዚያ በኋላ ምንም አላሉትም፤ ያደረጉትን ውይይት የሰማ ሰው አልነበረምና። 28 ኤርምያስ ኢየሩሳሌም እስከተያዘችበት ጊዜ ድረስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ፤ ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ጊዜም እዚያው ነበር።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ