የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 39
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ጥፋት (1-10)

        • ሴዴቅያስ ሲሸሽ ተያዘ (4-7)

      • ኤርምያስ ጥበቃ አገኘ (11-14)

      • ኤቤድሜሌክ ሕይወቱ እንደሚተርፍ ተነገረው (15-18)

ኤርምያስ 39:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾርና።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:1, 2፤ ኤር 52:4, 5፤ ሕዝ 24:1, 2

ኤርምያስ 39:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:3, 4፤ ኤር 52:6, 7፤ ሕዝ 33:21

ኤርምያስ 39:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በዕብራይስጡ ጽሑፍ ላይ ያሉት ቃላት በሚከተለውም መንገድ ሊቀመጡ ይችላሉ፦ “ኔርጋልሻሬጸር፣ ሳምጋርነቦ፣ ሳርሰኪም፣ ራብሳሪስ።”

  • *

    ወይም “የአስማተኞች አለቃ (ኮከብ ቆጣሪ)።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    5/2009፣ ገጽ 11

ኤርምያስ 39:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:25
  • +2ነገ 25:4-7፤ ኤር 52:7-11

ኤርምያስ 39:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 32:4፤ 38:18
  • +2ነገ 17:24
  • +2ነገ 23:31, 33

ኤርምያስ 39:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:7፤ 34:18-20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2017፣ ገጽ 1-2

ኤርምያስ 39:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 12:13

ኤርምያስ 39:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥትና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:9፤ ኤር 38:18
  • +2ነገ 25:9-11፤ 2ዜና 36:17, 19፤ ነህ 1:3፤ ኤር 52:13-15

ኤርምያስ 39:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:20፤ ኤር 40:1፤ 52:12

ኤርምያስ 39:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የግዳጅ አገልግሎት” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:12፤ ኤር 52:16

ኤርምያስ 39:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

ኤርምያስ 39:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 40:2, 4

ኤርምያስ 39:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥት ዋና ባለሥልጣን።”

  • *

    ወይም “የአስማተኞች አለቃ (ኮከብ ቆጣሪ)።”

ኤርምያስ 39:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 38:28
  • +2ነገ 22:8
  • +2ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24
  • +2ነገ 25:22፤ ኤር 40:5፤ 41:2

ኤርምያስ 39:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 32:2፤ 37:21

ኤርምያስ 39:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 38:7

ኤርምያስ 39:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 31

ኤርምያስ 39:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህ።”

  • *

    ወይም “ሕይወትህን ታተርፋለህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:39, 40፤ ኤር 17:7
  • +ኤር 45:2, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 31

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 39:12ነገ 25:1, 2፤ ኤር 52:4, 5፤ ሕዝ 24:1, 2
ኤር. 39:22ነገ 25:3, 4፤ ኤር 52:6, 7፤ ሕዝ 33:21
ኤር. 39:3ኤር 1:15
ኤር. 39:4ዘዳ 28:25
ኤር. 39:42ነገ 25:4-7፤ ኤር 52:7-11
ኤር. 39:5ኤር 32:4፤ 38:18
ኤር. 39:52ነገ 17:24
ኤር. 39:52ነገ 23:31, 33
ኤር. 39:6ኤር 21:7፤ 34:18-20
ኤር. 39:7ሕዝ 12:13
ኤር. 39:8ኢሳ 5:9፤ ኤር 38:18
ኤር. 39:82ነገ 25:9-11፤ 2ዜና 36:17, 19፤ ነህ 1:3፤ ኤር 52:13-15
ኤር. 39:92ነገ 25:20፤ ኤር 40:1፤ 52:12
ኤር. 39:102ነገ 25:12፤ ኤር 52:16
ኤር. 39:12ኤር 40:2, 4
ኤር. 39:14ኤር 38:28
ኤር. 39:142ነገ 22:8
ኤር. 39:142ዜና 34:20, 21፤ ኤር 26:24
ኤር. 39:142ነገ 25:22፤ ኤር 40:5፤ 41:2
ኤር. 39:15ኤር 32:2፤ 37:21
ኤር. 39:16ኤር 38:7
ኤር. 39:18መዝ 37:39, 40፤ ኤር 17:7
ኤር. 39:18ኤር 45:2, 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 39:1-18

ኤርምያስ

39 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾርና* መላው ሠራዊቱ መጥተው ኢየሩሳሌምን ከበቧት።+

2 በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በ11ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዋን ቅጥር ነደሉ።+ 3 የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ይኸውም ሳምጋሩ ኔርጋልሻሬጸር፣ ራብሳሪስ የሆነው ነቦሳርሰኪም፣* ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸርና የቀሩት የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር አጠገብ ተቀመጡ።+

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ፣ በንጉሡ የአትክልት ቦታ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤+ ወደ አረባ የሚወስደውንም መንገድ ተከትለው ሄዱ።+ 5 የከለዳውያን ሠራዊት ግን አሳደዳቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት።+ ከያዙት በኋላ በሃማት+ ምድር በሪብላ+ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነጾር* አመጡት፤ እሱም በዚያ ፈረደበት። 6 የባቢሎን ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አሳረዳቸው፤ በተጨማሪም የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ አሳረደ።+ 7 የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።+

8 ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና* የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤+ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።+ 9 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ በከተማዋ ውስጥ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ከድተው ለእሱ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች እንዲሁም የቀሩትን ሁሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።

10 ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ምንም ነገር ያልነበራቸውን አንዳንድ ያጡ የነጡ ድሆች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ ተዋቸው። ደግሞም በዚያ ቀን የወይን እርሻዎችና የሚያርሱት የእርሻ መሬት* ሰጣቸው።+

11 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ኤርምያስን አስመልክቶ የዘቦች አለቃ ለሆነው ለናቡዛራዳን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ 12 “ወስደህ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ አድርግለት፤ ክፉ ነገር አታድርግበት፤ የሚጠይቅህንም ነገር ሁሉ አድርግለት።”+

13 በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ* የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው 14 ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ+ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን+ ልጅ፣ ለአኪቃም+ ልጅ፣ ለጎዶልያስ+ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ።

15 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተዘግቶበት በነበረ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ 16 “ሂድና ለኢትዮጵያዊው ለኤቤድሜሌክ+ እንዲህ በለው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በዚህች ከተማ ላይ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያም ቀን ይህ ሲፈጸም ታያለህ።”’

17 “‘አንተን ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለምትፈራቸውም ሰዎች አልፈህ አትሰጥም።’

18 “‘የምታመልጥበትን መንገድ አዘጋጅልሃለሁ፤ በሰይፍም አትወድቅም። በእኔ ስለታመንክ+ ሕይወትህ* እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች’*+ ይላል ይሖዋ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ