የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤርምያስ እንዳያገባ፣ እንዳያለቅስና ወደ ግብዣ እንዳይሄድ ተነገረው (1-9)

      • ከተቀጡ በኋላ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ (10-21)

ኤርምያስ 16:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:2
  • +መዝ 79:2, 3፤ ኢሳ 5:25፤ ኤር 7:33፤ 9:22፤ 36:30
  • +ሕዝ 5:12

ኤርምያስ 16:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 24:16, 17
  • +ዘዳ 31:17፤ ኢሳ 27:11፤ 63:10

ኤርምያስ 16:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ የአረማውያን የለቅሶ ልማድ ሲሆን ከሃዲዋ እስራኤልም ይህን ልማድ ሳትከተል አትቀርም።

ኤርምያስ 16:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 24:7, 8፤ ኤር 7:34፤ ራእይ 18:23

ኤርምያስ 16:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:19

ኤርምያስ 16:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:12
  • +ኤር 8:1, 2
  • +ዳን 9:11፤ አሞጽ 2:4

ኤርምያስ 16:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:26
  • +ነህ 9:29፤ ኤር 6:28

ኤርምያስ 16:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 7:20፤ ኤር 15:14፤ 17:4
  • +ዘዳ 4:27, 28፤ 28:36

ኤርምያስ 16:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:2፤ ኤር 23:7, 8

ኤርምያስ 16:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:1-3፤ ኤር 3:18፤ 24:6፤ 30:3፤ 32:37፤ አሞጽ 9:14

ኤርምያስ 16:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2020፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 9

ኤርምያስ 16:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በመንገዶቻቸው ሁሉ።”

ኤርምያስ 16:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አስከሬኖች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:2
  • +ዘሌ 26:30፤ መዝ 106:38

ኤርምያስ 16:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:17
  • +ኤር 10:5, 14

ኤርምያስ 16:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 115:4፤ ኤር 2:11፤ 1ቆሮ 8:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 16:4ኤር 15:2
ኤር. 16:4መዝ 79:2, 3፤ ኢሳ 5:25፤ ኤር 7:33፤ 9:22፤ 36:30
ኤር. 16:4ሕዝ 5:12
ኤር. 16:5ሕዝ 24:16, 17
ኤር. 16:5ዘዳ 31:17፤ ኢሳ 27:11፤ 63:10
ኤር. 16:9ኢሳ 24:7, 8፤ ኤር 7:34፤ ራእይ 18:23
ኤር. 16:10ኤር 5:19
ኤር. 16:11መሳ 2:12
ኤር. 16:11ኤር 8:1, 2
ኤር. 16:11ዳን 9:11፤ አሞጽ 2:4
ኤር. 16:12ኤር 7:26
ኤር. 16:12ነህ 9:29፤ ኤር 6:28
ኤር. 16:132ዜና 7:20፤ ኤር 15:14፤ 17:4
ኤር. 16:13ዘዳ 4:27, 28፤ 28:36
ኤር. 16:14ዘፀ 20:2፤ ኤር 23:7, 8
ኤር. 16:15ዘዳ 30:1-3፤ ኤር 3:18፤ 24:6፤ 30:3፤ 32:37፤ አሞጽ 9:14
ኤር. 16:18ኢሳ 40:2
ኤር. 16:18ዘሌ 26:30፤ መዝ 106:38
ኤር. 16:19ኤር 17:17
ኤር. 16:19ኤር 10:5, 14
ኤር. 16:20መዝ 115:4፤ ኤር 2:11፤ 1ቆሮ 8:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 16:1-21

ኤርምያስ

16 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አትውለድ። 3 ይሖዋ በዚህ ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም በዚህች ምድር ስለሚወልዷቸው እናቶችና አባቶች እንዲህ ይላልና፦ 4 ‘በገዳይ በሽታዎች ይሞታሉ፤+ ይሁንና ማንም አያለቅስላቸውም ወይም አይቀብራቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።+ በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ፤+ አስከሬናቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።’

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦

‘ለለቀስተኞች ድግስ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ፤

እዚያም ሄደህ አታልቅስ ወይም አታስተዛዝን።’+

‘ሰላሜን ከዚህ ሕዝብ ወስጄአለሁና’ ይላል ይሖዋ፤

‘ታማኝ ፍቅሬና ምሕረቴ ከእነሱ እንዲርቅ አድርጌአለሁ።+

 6 ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች በዚህች ምድር ላይ ይሞታሉ።

ደግሞም አይቀበሩም፤

ማንም ሰው አያዝንላቸውም፤

ለእነሱ ሲል ሰውነቱን የሚተለትልም ሆነ ራሱን የሚላጭ አይኖርም።*

 7 ሰው የሞተባቸውንም ለማጽናናት

የእዝን እንጀራ የሚወስድላቸው አይኖርም፤

አባት ወይም እናት ለሞተባቸውም

የመጽናኛ ጽዋ እንዲጠጡ የሚሰጣቸው አይኖርም።

 8 ከእነሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣት

ግብዣ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ።’

9 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ስፍራ፣ በእናንተ ዘመን ዓይናችሁ እያየ የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ አስወግዳለሁ።’+

10 “ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁሃል፦ ‘ይሖዋ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ የተናገረው ለምንድን ነው? በአምላካችን በይሖዋ ላይ የፈጸምነው በደልና ኃጢአት ምንድን ነው?’+ 11 አንተም እንዲህ ብለህ ትመልስላቸዋለህ፦ ‘“አባቶቻችሁ እኔን ስለተዉ ነው”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ስላገለገሉ እንዲሁም ስለሰገዱላቸው ነው።+ እኔን ግን ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም።+ 12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’

14 “‘ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” የማይሉበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤+ 15 ‘ከዚህ ይልቅ “እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ሰብስቦ ባመጣቸው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት፣ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።’+

16 ‘እነሆ፣ እኔ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰዳለሁ’ ይላል ይሖዋ፤

‘እነሱንም ያጠምዷቸዋል።

ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤

እነሱም ከየተራራው፣ ከየኮረብታውና

ከየቋጥኙ ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል።

17 ዓይኖቼ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ* ላይ ነውና።

ከፊቴ አልተሸሸጉም፤

በደላቸውም ከዓይኔ አልተሰወረም።

18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+

ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤

ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+

19 ብርታቴና መጠጊያዬ፣

በጭንቀት ጊዜ መሸሸጊያዬ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+

ብሔራት ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ ይመጣሉ፤

እንዲህም ይላሉ፦ “አባቶቻችን ፍጹም ውሸትን፣

ከንቱ የሆኑና ምንም ጥቅም የሌላቸውን የማይረቡ ነገሮች ወርሰዋል።”+

20 ሰው ለራሱ አማልክት ሊሠራ ይችላል?

የሚሠራቸው አማልክት እውነተኛ አማልክት አይደሉም።+

21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤

በዚህ ጊዜ ኃይሌንና ብርታቴን እንዲያውቁ አደርጋለሁ፤

እነሱም ስሜ ይሖዋ መሆኑን ያውቃሉ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ