የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት

      • የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች (1-11)

      • ኢያሱ ሙሴን እንደሚተካ ተነገረው (12-23)

ዘኁልቁ 27:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 26:33

ዘኁልቁ 27:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:25, 26

ዘኁልቁ 27:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:35፤ 16:1, 2, 19, 35

ዘኁልቁ 27:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:15, 16፤ 33:11፤ ዘሌ 24:11, 12

ዘኁልቁ 27:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 36:2፤ ኢያሱ 17:3, 4

ዘኁልቁ 27:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:47፤ ዘዳ 32:48, 49
  • +ዘፍ 13:14, 15፤ ዘዳ 3:27፤ 32:52፤ 34:1

ዘኁልቁ 27:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:24, 28፤ 33:38፤ ዘዳ 10:6፤ 32:50
  • +ዘኁ 31:2፤ ዘዳ 34:7

ዘኁልቁ 27:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:10, 12፤ ዘዳ 1:37
  • +ኢያሱ 15:1
  • +ዘዳ 1:2
  • +መዝ 106:32, 33

ዘኁልቁ 27:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሥጋ።”

ዘኁልቁ 27:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 34:9፤ ሥራ 6:5, 6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2002፣ ገጽ 12

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 7፣ ገጽ 6

ዘኁልቁ 27:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:7

ዘኁልቁ 27:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከክብርህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 1:17
  • +ዘዳ 1:38፤ 31:3፤ 34:10

ዘኁልቁ 27:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 28:30፤ 1ሳሙ 23:9፤ 28:6፤ ነህ 7:65

ዘኁልቁ 27:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:28፤ 31:14, 23
  • +ዘኁ 27:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘኁ. 27:1ዘኁ 26:33
ዘኁ. 27:2ዘፀ 18:25, 26
ዘኁ. 27:3ዘኁ 14:35፤ 16:1, 2, 19, 35
ዘኁ. 27:5ዘፀ 18:15, 16፤ 33:11፤ ዘሌ 24:11, 12
ዘኁ. 27:7ዘኁ 36:2፤ ኢያሱ 17:3, 4
ዘኁ. 27:12ዘኁ 33:47፤ ዘዳ 32:48, 49
ዘኁ. 27:12ዘፍ 13:14, 15፤ ዘዳ 3:27፤ 32:52፤ 34:1
ዘኁ. 27:13ዘኁ 20:24, 28፤ 33:38፤ ዘዳ 10:6፤ 32:50
ዘኁ. 27:13ዘኁ 31:2፤ ዘዳ 34:7
ዘኁ. 27:14ዘኁ 20:10, 12፤ ዘዳ 1:37
ዘኁ. 27:14ኢያሱ 15:1
ዘኁ. 27:14ዘዳ 1:2
ዘኁ. 27:14መዝ 106:32, 33
ዘኁ. 27:18ዘዳ 34:9፤ ሥራ 6:5, 6
ዘኁ. 27:19ዘዳ 31:7
ዘኁ. 27:20ኢያሱ 1:17
ዘኁ. 27:20ዘዳ 1:38፤ 31:3፤ 34:10
ዘኁ. 27:21ዘፀ 28:30፤ 1ሳሙ 23:9፤ 28:6፤ ነህ 7:65
ዘኁ. 27:23ዘዳ 3:28፤ 31:14, 23
ዘኁ. 27:23ዘኁ 27:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘኁልቁ 27:1-23

ዘኁልቁ

27 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ የሆነው የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች+ ቀረቡ። የሴት ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። 2 እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በአለቆቹ+ እንዲሁም በመላው ማኅበረሰብ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ 3 “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ይሁንና እሱ በይሖዋ ላይ ለማመፅ ከተባበሩት ከቆሬ ግብረ አበሮች+ አንዱ አልነበረም፤ እሱ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነው፤ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። 4 ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ ስሙ ከቤተሰቡ መካከል ለምን ይጥፋ? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስት ስጡን።” 5 ስለዚህ ሙሴ ጉዳያቸውን በይሖዋ ፊት አቀረበ።+

6 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 7 “የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ትክክል ናቸው። በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስታቸውን ውርስ አድርገህ ልትሰጣቸው ይገባል፤ የአባታቸውም ውርስ ለእነሱ እንዲተላለፍ ማድረግ አለብህ።+ 8 እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ውርሱ ለሴት ልጆቹ እንዲተላለፍ ማድረግ አለባችሁ። 9 ሴት ልጅ ከሌለው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ትሰጣላችሁ። 10 ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ትሰጣላችሁ። 11 አባቱ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከቤተሰቡ መካከል ቅርብ ለሆነው የሥጋ ዘመዱ ትሰጣላችሁ፤ እሱም ርስት አድርጎ ይወስደዋል። ይህም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን የተደነገገ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።’”

12 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ አባሪም ተራራ+ ውጣና ለእስራኤላውያን የምሰጠውን ምድር ተመልከት።+ 13 ካየኸውም በኋላ እንደ ወንድምህ እንደ አሮን+ አንተም ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ፤*+ 14 ምክንያቱም ማኅበረሰቡ በጺን ምድረ በዳ ከእኔ ጋር በተጣላ ጊዜ ከውኃዎቹ ጋር በተያያዘ በፊታቸው ሳትቀድሱኝ በመቅረታችሁ ትእዛዜን ተላልፋችኋል።+ እነዚህም በጺን ምድረ በዳ+ በቃዴስ+ የሚገኙት የመሪባ ውኃዎች+ ናቸው።”

15 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ 16 “የሰው* ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነው ይሖዋ በማኅበረሰቡ ላይ አንድ ሰው ይሹም፤ 17 እሱም የይሖዋ ማኅበረሰብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ እንዲሁም እነሱን መርቶ የሚያወጣና የሚያስገባ ይሆናል።” 18 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።+ 19 ከዚያም በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቁመው፤ በፊታቸውም ሹመው።+ 20 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲሰማውም+ ከሥልጣንህ* የተወሰነውን ስጠው።+ 21 እሱም በኡሪም+ አማካኝነት የይሖዋን ፍርድ በሚጠይቅለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር ያሉት እስራኤላውያን እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ በእሱ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእሱ ትእዛዝ ይገባሉ።”

22 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቆመው፤ 23 ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት+ እጆቹን በእሱ ላይ በመጫን ሾመው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ