የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጥሩ በለሶችና መጥፎ በለሶች (1-10)

ኤርምያስ 24:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

  • *

    ዮአኪን እና ኮንያሁ ተብሎም ይጠራል።

  • *

    “ምሽግ ከሚገነቡት ሰዎች” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:6፤ 1ዜና 3:16
  • +ኤር 22:24
  • +2ነገ 24:15, 16፤ ኤር 29:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 13-14

ኤርምያስ 24:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 13-14

ኤርምያስ 24:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 24:8

ኤርምያስ 24:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 14-15, 17

ኤርምያስ 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 1:3፤ ኤር 12:15፤ 25:11፤ 29:10፤ ሕዝ 36:24
  • +ኤር 1:10፤ 30:18፤ 32:41

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 14-15, 17

ኤርምያስ 24:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:6፤ ኤር 31:33፤ ሕዝ 11:19
  • +ኤር 29:13
  • +ኤር 30:22፤ 32:38፤ ዘካ 8:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2013፣ ገጽ 8-9

    3/1/1994፣ ገጽ 14-15, 17

ኤርምያስ 24:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 29:17
  • +2ነገ 25:6, 7፤ ሕዝ 12:12, 13
  • +ኤር 44:1፤ 46:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 15-16

ኤርምያስ 24:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:4፤ 34:17
  • +ዘዳ 28:64፤ ኤር 29:18
  • +ኤር 26:4, 6፤ 29:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 15

ኤርምያስ 24:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሽታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:33፤ ኤር 9:16
  • +ዘዳ 28:59፤ ኤር 15:2፤ ሕዝ 7:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1994፣ ገጽ 15

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 24:12ነገ 24:6፤ 1ዜና 3:16
ኤር. 24:1ኤር 22:24
ኤር. 24:12ነገ 24:15, 16፤ ኤር 29:1, 2
ኤር. 24:3ኤር 24:8
ኤር. 24:6ዕዝራ 1:3፤ ኤር 12:15፤ 25:11፤ 29:10፤ ሕዝ 36:24
ኤር. 24:6ኤር 1:10፤ 30:18፤ 32:41
ኤር. 24:7ዘዳ 30:6፤ ኤር 31:33፤ ሕዝ 11:19
ኤር. 24:7ኤር 29:13
ኤር. 24:7ኤር 30:22፤ 32:38፤ ዘካ 8:8
ኤር. 24:8ኤር 29:17
ኤር. 24:82ነገ 25:6, 7፤ ሕዝ 12:12, 13
ኤር. 24:8ኤር 44:1፤ 46:13
ኤር. 24:9ኤር 15:4፤ 34:17
ኤር. 24:9ዘዳ 28:64፤ ኤር 29:18
ኤር. 24:9ኤር 26:4, 6፤ 29:22
ኤር. 24:10ዘሌ 26:33፤ ኤር 9:16
ኤር. 24:10ዘዳ 28:59፤ ኤር 15:2፤ ሕዝ 7:15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 24:1-10

ኤርምያስ

24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+ 2 በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም።

3 ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።”+

4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 5 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ። 6 መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+ 7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+

8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+ 9 ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤+ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ+ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ።+ 10 ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣+ ረሃብና ቸነፈር* እሰዳለሁ።”’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ