የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሁዳ ከአምላክ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን አፈረሰች (1-17)

        • “አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋል” (13)

      • ኤርምያስ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ሆነ (18-20)

      • ኤርምያስ ከአገሩ ሰዎች ተቃውሞ ገጠመው (21-23)

ኤርምያስ 11:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለኤርምያስ የተነገረ ሳይሆን አይቀርም።

ኤርምያስ 11:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 27:26፤ 28:15

ኤርምያስ 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:3፤ ዘዳ 4:20
  • +ዘፀ 24:3
  • +ዘሌ 26:3, 12

ኤርምያስ 11:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 3:8፤ ዘሌ 20:24፤ ዘዳ 6:3

ኤርምያስ 11:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:13፤ 25:4፤ 35:15

ኤርምያስ 11:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 65:2፤ ኤር 7:24, 26፤ ሕዝ 20:8፤ ዘካ 7:11, 12

ኤርምያስ 11:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:11, 17፤ 1ሳሙ 8:8፤ 2ነገ 22:17
  • +2ዜና 28:22, 23
  • +ዘዳ 31:16፤ 2ነገ 17:6, 7፤ ሆሴዕ 6:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 9

ኤርምያስ 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:16፤ ኤር 6:19፤ ሕዝ 7:5
  • +ኢሳ 1:15፤ ኤር 14:12፤ ሕዝ 8:18፤ ሚክ 3:4

ኤርምያስ 11:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚጨስ መሥዋዕት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:37, 38፤ ኤር 2:28

ኤርምያስ 11:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለአሳፋሪው አምላክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:9, 10

ኤርምያስ 11:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤርምያስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:16፤ 14:11

ኤርምያስ 11:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በቤተ መቅደሱ የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች ያመለክታል።

ኤርምያስ 11:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:2፤ ኤር 2:21
  • +ኤር 19:5, 15

ኤርምያስ 11:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 18:18

ኤርምያስ 11:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጥልቅ ስሜትንና።” ቃል በቃል “ኩላሊትንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:9፤ ኤር 17:10፤ 20:12

ኤርምያስ 11:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን በሚሿት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:1
  • +ኢሳ 30:10፤ አሞጽ 2:12፤ 7:16

ኤርምያስ 11:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:17፤ ሰቆ 2:21
  • +ኤር 18:21

ኤርምያስ 11:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 21:8, 18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2017፣ ገጽ 1

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 11:3ዘዳ 27:26፤ 28:15
ኤር. 11:4ዘፀ 13:3፤ ዘዳ 4:20
ኤር. 11:4ዘፀ 24:3
ኤር. 11:4ዘሌ 26:3, 12
ኤር. 11:5ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 3:8፤ ዘሌ 20:24፤ ዘዳ 6:3
ኤር. 11:7ኤር 7:13፤ 25:4፤ 35:15
ኤር. 11:8ኢሳ 65:2፤ ኤር 7:24, 26፤ ሕዝ 20:8፤ ዘካ 7:11, 12
ኤር. 11:10መሳ 2:11, 17፤ 1ሳሙ 8:8፤ 2ነገ 22:17
ኤር. 11:102ዜና 28:22, 23
ኤር. 11:10ዘዳ 31:16፤ 2ነገ 17:6, 7፤ ሆሴዕ 6:7
ኤር. 11:112ነገ 22:16፤ ኤር 6:19፤ ሕዝ 7:5
ኤር. 11:11ኢሳ 1:15፤ ኤር 14:12፤ ሕዝ 8:18፤ ሚክ 3:4
ኤር. 11:12ዘዳ 32:37, 38፤ ኤር 2:28
ኤር. 11:13ኤር 7:9, 10
ኤር. 11:14ኤር 7:16፤ 14:11
ኤር. 11:17ኢሳ 5:2፤ ኤር 2:21
ኤር. 11:17ኤር 19:5, 15
ኤር. 11:19ኤር 18:18
ኤር. 11:201ዜና 28:9፤ ኤር 17:10፤ 20:12
ኤር. 11:21ኤር 1:1
ኤር. 11:21ኢሳ 30:10፤ አሞጽ 2:12፤ 7:16
ኤር. 11:222ዜና 36:17፤ ሰቆ 2:21
ኤር. 11:22ኤር 18:21
ኤር. 11:23ኢያሱ 21:8, 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 11:1-23

ኤርምያስ

11 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “እናንተ ሰዎች፣ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ!

“ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ቃሉን ተናገር፤* 3 እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይታዘዝ ሰው የተረገመ ነው፤+ 4 ይህም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫ ምድጃው ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ብዬ ያዘዝኳቸው ቃል ነው፦+ ‘ድምፄን ስሙ፤ ያዘዝኳችሁንም ነገር ሁሉ አድርጉ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤+ 5 ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ለመስጠት ለአባቶቻችሁ የገባሁትን መሐላ ለመፈጸም ነው።’”’”+

እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ አሜን”* ብዬ መለስኩ።

6 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ አውጅ፦ ‘የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ በሥራም ላይ አውሉት። 7 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ “ድምፄን ስሙ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ* አጥብቄ ሳሳስባቸው ነበርና።+ 8 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳቸው ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን ተከተሉ።+ ስለዚህ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያዘዝኳቸውንና እነሱ ሥራ ላይ ያላዋሉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ በእነሱ ላይ አመጣሁባቸው።’”

9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሴራ ጠንስሰዋል። 10 ቃሌን ያልታዘዙት የቀድሞ አባቶቻቸው ይፈጽሙት ወደነበረው በደል ተመልሰዋል።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን ተከትለዋል፤ ደግሞም አገልግለዋል።+ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።+ 11 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ማምለጥ የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ።+ እርዳታ ለማግኘት ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውም።+ 12 ከዚያም የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መሥዋዕት* ወደሚያቀርቡላቸው አማልክት ሄደው እርዳታ ይጠይቃሉ፤+ ሆኖም ጥፋት በሚደርስባቸው ጊዜ ፈጽሞ አያድኗቸውም። 13 ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና፤ ለአሳፋሪው ነገር* ይኸውም ለባአል መሥዋዕት ለማቅረብ የኢየሩሳሌምን ጎዳናዎች ያህል ብዛት ያላቸው መሠዊያዎች ሠርታችኋል።’+

14 “አንተም* ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ፤+ ጥፋት ደርሶባቸው ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና።

15 ብዙዎቹ የሸረቡትን ክፉ ሐሳብ እየፈጸሙ ሳለ፣

ውዴ በቤቴ ለመገኘት ምን መብት አላት?

ጥፋት በአንቺ ላይ ሲመጣ በቅዱስ ሥጋ* ጥፋቱን ሊከላከሉልሽ ይችላሉ?

በዚያን ጊዜ ሐሴት ታደርጊ ይሆን?

16 በአንድ ወቅት ይሖዋ በመልካም ፍሬ የተዋበ፣

የለመለመ የወይራ ዛፍ ብሎ ጠርቶሽ ነበር።

በሚያስገመግም ታላቅ ድምፅ፣ በእሳት አነደዳት፤

እነሱም ቅርንጫፎቿን ሰባበሩ።

17 “የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣+ ለባአል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ያስከፉኝ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በሠሩት ክፉ ነገር የተነሳ በአንቺ ላይ ጥፋት እንደሚመጣ አስታውቋል።”+

18 ይሖዋ ይህን እንዳውቅ ገለጠልኝ፤

አምላክ ሆይ፣ በዚያን ጊዜ የፈጸሙትን ነገር እንዳይ አደረግከኝ።

19 እኔ ለመታረድ እንደሚነዳ የዋህ የበግ ጠቦት ነበርኩ።

“ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋው፤

ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ እንዳይታወስ

ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው

በእኔ ላይ ሴራ እንደጠነሰሱ አላወቅኩም ነበር።+

20 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ግን በጽድቅ ይፈርዳል፤

የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ይመረምራል።+

አምላክ ሆይ፣ በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤

ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።

21 ስለዚህ ይሖዋ ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* በአናቶት+ ሰዎች ላይ ይህን ቃል ተናግሯል፤ እነሱ “በይሖዋ ስም ትንቢት አትናገር፤+ አለዚያ በእጃችን ትጠፋለህ” ይላሉ፤ 22 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እነሱን ተጠያቂ አደርጋለሁ። ወጣት ወንዶቹ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በረሃብ ያልቃሉ።+ 23 እነሱን ተጠያቂ በማደርግበት ዓመት፣ በአናቶት+ ሰዎች ላይ ጥፋት ስለማመጣ ከእነሱ መካከል የሚተርፍ አንድም ሰው አይኖርም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ