የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ቆሮንቶስ 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጳውሎስ የጉባኤውን አባላት ለማስደሰት የነበረው ፍላጎት (1-4)

      • ይቅር የተባለና የተመለሰ ኃጢአተኛ (5-11)

      • ጳውሎስ በጥሮአስና በመቄዶንያ (12, 13)

      • አገልግሎት፣ የድል ሰልፍ (14-17)

        • “የአምላክን ቃል አንሸቃቅጥም” (17)

2 ቆሮንቶስ 2:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 7:8, 9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/1996፣ ገጽ 11

2 ቆሮንቶስ 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 5:1

2 ቆሮንቶስ 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 12:12
  • +ሉቃስ 15:23, 24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2010፣ ገጽ 13

    10/1/1998፣ ገጽ 17-18

2 ቆሮንቶስ 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2013፣ ገጽ 20

    10/1/1998፣ ገጽ 17

2 ቆሮንቶስ 2:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 29

2 ቆሮንቶስ 2:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሰይጣን እንዳንታለል።”

  • *

    ወይም “የእሱን ሐሳብ፤ የእሱን ዕቅድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:31፤ 2ጢሞ 2:26
  • +ኤፌ 6:11, 12፤ 1ጴጥ 5:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2006፣ ገጽ 27

    1/15/2006፣ ገጽ 29

    8/15/2002፣ ገጽ 26-28

    10/1/1998፣ ገጽ 18

2 ቆሮንቶስ 2:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 166

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/1998፣ ገጽ 30

2 ቆሮንቶስ 2:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 2:3፤ ቲቶ 1:4
  • +2ቆሮ 7:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 166

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/1998፣ ገጽ 30

2 ቆሮንቶስ 2:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2010፣ ገጽ 23

    9/1/2005፣ ገጽ 31

2 ቆሮንቶስ 2:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2010፣ ገጽ 23

    7/15/2008፣ ገጽ 28

    9/1/2005፣ ገጽ 31

2 ቆሮንቶስ 2:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መዓዛ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:19፤ 2ቆሮ 4:3፤ 1ጴጥ 2:7, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2010፣ ገጽ 23

    7/15/2008፣ ገጽ 28

    9/1/2005፣ ገጽ 31

2 ቆሮንቶስ 2:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንነግድም፤ በአምላክ ቃል አናተርፍም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 4:2

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ቆሮ. 2:42ቆሮ 7:8, 9
2 ቆሮ. 2:51ቆሮ 5:1
2 ቆሮ. 2:7ዕብ 12:12
2 ቆሮ. 2:7ሉቃስ 15:23, 24
2 ቆሮ. 2:8ሮም 12:10
2 ቆሮ. 2:11ሉቃስ 22:31፤ 2ጢሞ 2:26
2 ቆሮ. 2:11ኤፌ 6:11, 12፤ 1ጴጥ 5:8
2 ቆሮ. 2:12ሥራ 16:8
2 ቆሮ. 2:13ገላ 2:3፤ ቲቶ 1:4
2 ቆሮ. 2:132ቆሮ 7:5
2 ቆሮ. 2:16ዮሐ 15:19፤ 2ቆሮ 4:3፤ 1ጴጥ 2:7, 8
2 ቆሮ. 2:172ቆሮ 4:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ቆሮንቶስ 2:1-17

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ

2 እንደገና በምመጣበት ጊዜ ለሐዘን ምክንያት የሚሆን ነገር እንዳይፈጠር ወስኛለሁ። 2 ምክንያቱም የደስታዬ ምንጭ የሆናችሁትን እናንተን ካሳዘንኳችሁ እንግዲህ እኔን ማን ሊያስደስተኝ ነው? 3 ባለፈው ጊዜ የጻፍኩላችሁ በምመጣበት ጊዜ ልደሰትባቸው በሚገባ ሰዎች እንዳላዝን ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የእናንተ የሁላችሁም ደስታ እንደሚሆን እተማመናለሁ። 4 ልቤ በብዙ መከራና ጭንቀት ተውጦ በብዙ እንባ የጻፍኩላችሁ እንድታዝኑ ሳይሆን+ ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።

5 ለሐዘን የሚዳርግ ነገር ያደረገ ማንም ቢኖር+ ያሳዘነው እኔን ሳይሆን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሁላችሁንም ነው፤ እንዲህ ያልኩት ግን ነገሩን ለማክበድ ብዬ አይደለም። 6 እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቻችሁ የሰጣችሁት ተግሣጽ ይበቃዋል፤ 7 አሁን ይህ ሰው ከልክ በላይ በሐዘን እንዳይዋጥ+ በደግነት ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባል።+ 8 ስለዚህ ለእሱ ያላችሁን ፍቅር እንድታረጋግጡለት አሳስባችኋለሁ።+ 9 የጻፍኩላችሁም በሁሉም ነገር ታዛዥ መሆናችሁን ታሳዩ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው። 10 በደሉ ምንም ይሁን ምን እናንተ ይቅር ያላችሁትን ማንኛውንም ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ። እንዲያውም ሁሉንም ነገር በክርስቶስ ፊት ይቅር ያልኩት (ይቅር ያልኩት ነገር ካለ) ለእናንተ ስል ነው፤ 11 ይህም ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ* ነው፤+ እሱ የሚሸርበውን ተንኮል* እናውቃለንና።+

12 ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች ለማወጅ ጥሮአስ+ በደረስኩ ጊዜ የጌታን ሥራ ለማከናወን በር ተከፍቶልኝ ነበር፤ 13 ይሁንና ወንድሜን ቲቶን+ ስላላገኘሁት መንፈሴ ተረብሾ ነበር። በመሆኑም በዚያ ያሉትን ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ+ ሄድኩ።

14 በድል ሰልፍ ከክርስቶስ ጋር አብረን እንድንጓዝ በማድረግ ዘወትር ለሚመራንና የእውቀቱ መዓዛ በእኛ አማካኝነት በሁሉም ቦታ እንዲናኝ ለሚያደርገው አምላክ ምስጋና ይድረሰው! 15 እኛ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ባሉት መካከልና ወደ ጥፋት እያመሩ ባሉት መካከል ለአምላክ የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ 16 ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ለሞት የሚዳርግ የሞት ሽታ፣*+ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላሉት ደግሞ ወደ ሕይወት የሚመራ የሕይወት መዓዛ ነን። እንዲህ ላለው አገልግሎት ብቃት ያለው ማን ነው? 17 እኛ ነን፤ ምክንያቱም እኛ እንደ ብዙዎቹ ሰዎች የአምላክን ቃል አንሸቃቅጥም፤*+ ከዚህ ይልቅ በአምላክ የተላክን እንደመሆናችን መጠን በቅንነት እንናገራለን፤ ይህን የምናደርገው በአምላክ ፊት ሆነን እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ