የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • ተገቢ ያልሆነ የፆታ ግንኙነት (1-30)

        • እንደ ከነአናውያን አታድርጉ (3)

        • በቅርብ ዘመዳሞች መካከል የሚፈጸም የፆታ ግንኙነት (6-18)

        • በወር አበባ ጊዜ (19)

        • ግብረ ሰዶማዊነት (22)

        • ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸም (23)

        • ምድሪቱ እንዳትተፋችሁ ራሳችሁን አታርክሱ (24-30)

ዘሌዋውያን 18:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 17:7፤ ዘፀ 6:7

ዘሌዋውያን 18:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:24፤ ዘሌ 20:23

ዘሌዋውያን 18:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:22፤ ዘዳ 4:1

ዘሌዋውያን 18:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 10:27, 28፤ ሮም 10:5፤ ገላ 3:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2009፣ ገጽ 6

ዘሌዋውያን 18:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:17

ዘሌዋውያን 18:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ይህ የአባትህ እርቃን ነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:22፤ 49:4፤ ዘሌ 20:11፤ ዘዳ 27:20፤ 2ሳሙ 16:21፤ 1ቆሮ 5:1

ዘሌዋውያን 18:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:17፤ ዘዳ 27:22፤ 2ሳሙ 13:10-12

ዘሌዋውያን 18:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:19

ዘሌዋውያን 18:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአባትህን ወንድም እርቃን አትግለጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:20

ዘሌዋውያን 18:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:12

ዘሌዋውያን 18:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ይህ የወንድምህ እርቃን ነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:21፤ ዘዳ 25:5፤ ማር 6:17, 18

ዘሌዋውያን 18:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሳፋሪ ምግባር፤ ሴሰኝነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:14፤ ዘዳ 27:23

ዘሌዋውያን 18:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:15

ዘሌዋውያን 18:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 15:19, 24፤ 20:18

ዘሌዋውያን 18:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከጎረቤትህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:14፤ ዘሌ 20:10፤ ዘዳ 22:22፤ ምሳሌ 6:29፤ ማቴ 5:27, 28፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ዕብ 13:4

ዘሌዋውያን 18:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መሥዋዕት እንዲሆን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:2፤ ዘዳ 18:10፤ 1ነገ 11:7፤ 2ነገ 23:10
  • +ዘሌ 20:3

ዘሌዋውያን 18:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:5፤ ዘሌ 20:13፤ መሳ 19:22፤ ሮም 1:26, 27፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ይሁዳ 7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    1/2012፣ ገጽ 28

ዘሌዋውያን 18:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:19፤ ዘሌ 20:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2003፣ ገጽ 27

ዘሌዋውያን 18:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:23፤ ዘዳ 18:12

ዘሌዋውያን 18:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    4/8/1993፣ ገጽ 18-19

ዘሌዋውያን 18:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:22፤ ዘዳ 4:1, 40
  • +ዘፀ 12:49

ዘሌዋውያን 18:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:17, 18፤ 2ነገ 16:2, 3፤ 21:1, 2

ዘሌዋውያን 18:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

ዘሌዋውያን 18:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:3፤ 20:23፤ ዘዳ 18:9

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 18:2ዘፍ 17:7፤ ዘፀ 6:7
ዘሌ. 18:3ዘፀ 23:24፤ ዘሌ 20:23
ዘሌ. 18:4ዘሌ 20:22፤ ዘዳ 4:1
ዘሌ. 18:5ሉቃስ 10:27, 28፤ ሮም 10:5፤ ገላ 3:12
ዘሌ. 18:6ዘሌ 20:17
ዘሌ. 18:8ዘፍ 35:22፤ 49:4፤ ዘሌ 20:11፤ ዘዳ 27:20፤ 2ሳሙ 16:21፤ 1ቆሮ 5:1
ዘሌ. 18:9ዘሌ 20:17፤ ዘዳ 27:22፤ 2ሳሙ 13:10-12
ዘሌ. 18:12ዘሌ 20:19
ዘሌ. 18:14ዘሌ 20:20
ዘሌ. 18:15ዘሌ 20:12
ዘሌ. 18:16ዘሌ 20:21፤ ዘዳ 25:5፤ ማር 6:17, 18
ዘሌ. 18:17ዘሌ 20:14፤ ዘዳ 27:23
ዘሌ. 18:18ዘፍ 30:15
ዘሌ. 18:19ዘሌ 15:19, 24፤ 20:18
ዘሌ. 18:20ዘፀ 20:14፤ ዘሌ 20:10፤ ዘዳ 22:22፤ ምሳሌ 6:29፤ ማቴ 5:27, 28፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ዕብ 13:4
ዘሌ. 18:21ዘሌ 20:2፤ ዘዳ 18:10፤ 1ነገ 11:7፤ 2ነገ 23:10
ዘሌ. 18:21ዘሌ 20:3
ዘሌ. 18:22ዘፍ 19:5፤ ዘሌ 20:13፤ መሳ 19:22፤ ሮም 1:26, 27፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ይሁዳ 7
ዘሌ. 18:23ዘፀ 22:19፤ ዘሌ 20:15, 16
ዘሌ. 18:24ዘሌ 20:23፤ ዘዳ 18:12
ዘሌ. 18:25ዘፍ 15:16
ዘሌ. 18:26ዘሌ 20:22፤ ዘዳ 4:1, 40
ዘሌ. 18:26ዘፀ 12:49
ዘሌ. 18:27ዘዳ 20:17, 18፤ 2ነገ 16:2, 3፤ 21:1, 2
ዘሌ. 18:30ዘሌ 18:3፤ 20:23፤ ዘዳ 18:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 18:1-30

ዘሌዋውያን

18 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ 3 ትኖሩበት በነበረው በግብፅ ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነአን ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉትም አታድርጉ።+ እንዲሁም እነሱ የሚከተሏቸውን ደንቦች አትከተሉ። 4 ድንጋጌዎቼን ተግባር ላይ አውሉ፤ ደንቦቼንም በመጠበቅ በእነሱ ሂዱ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 5 ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

6 “‘ከመካከላችሁ ማንም ሰው የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ አይቅረብ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። 7 ከአባትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ከእናትህም ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ እናትህ ናት፤ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።

8 “‘ከአባትህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ ይህ አባትህን ለኀፍረት መዳረግ ነው።*

9 “‘የአባትህ ልጅም ሆነች የእናትህ ልጅ ወይም በቤት የተወለደችም ሆነች በውጭ፣ ከእህትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+

10 “‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተው እርቃን ናቸው።

11 “‘የአባትህ ልጅ ከሆነችው ከአባትህ ሚስት ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ እህትህ ናት።

12 “‘ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።+

13 “‘ከእናትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናት።

14 “‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም እሱን ለኀፍረት አትዳርገው።* እሷ ዘመድህ ናት።+

15 “‘ከልጅህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ እሷ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም የለብህም።

16 “‘ከወንድምህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤+ ምክንያቱም ይህ ወንድምህን ለኀፍረት መዳረግ ነው።*

17 “‘ከአንዲት ሴትና ከሴት ልጇ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅም ሆነ ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም እነሱን አትውሰድ። እነሱ የእሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፤ ይህ ጸያፍ ድርጊት* ነው።

18 “‘እህቷ ጣውንቷ እንዳትሆን+ ሚስትህ በሕይወት እያለች ከእህቷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።

19 “‘አንዲት ሴት በወር አበባዋ ረክሳ እያለች ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ እሷ አትቅረብ።+

20 “‘ከጓደኛህ* ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራስህን አታርክስ።+

21 “‘ከልጆችህ መካከል የትኛውንም ለሞሎክ እንዲሰጥ* አታድርግ።+ በዚህ መንገድ የአምላክህን ስም አታርክስ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።

22 “‘ከሴት ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ።+ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው።

23 “‘አንድ ወንድ ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራሱን አያርክስ፤ ሴትም ብትሆን ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ራሷን ለእንስሳ አታቅርብ።+ ይህ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ነገር ነው።

24 “‘ከእነዚህ ነገሮች በየትኛውም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ምክንያቱም ከእናንተ ፊት አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች አርክሰዋል።+ 25 ስለሆነም ምድሪቱ ረክሳለች፤ እኔም ለሠራችው ስህተት ቅጣት አመጣባታለሁ፤ ምድሪቱም ነዋሪዎቿን ትተፋቸዋለች።+ 26 እናንተ ግን ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤+ ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ማድረግ የለባችሁም፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው እንዲህ ማድረግ የለበትም።+ 27 ምክንያቱም ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ፈጽመዋል፤+ በዚህም የተነሳ አሁን ምድሪቱ ረክሳለች። 28 እናንተ ግን ምድሪቱን ስለማታረክሷት ከእናንተ በፊት የነበሩትን ብሔራት እንደተፋቻቸው እናንተን አትተፋችሁም። 29 ማንኛውም ሰው ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ቢፈጽም ይህን የፈጸመው ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። 30 ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች ይከተሏቸው ከነበሩት አስጸያፊ ልማዶች በመራቅ ለእኔ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤+ አለዚያ በእነሱ ምክንያት ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ