የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • የሚቃጠል መባ (1-17)

ዘሌዋውያን 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:34

ዘሌዋውያን 1:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የእስራኤልን ወንዶች ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:18-20

ዘሌዋውያን 1:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:19, 21፤ ሚል 1:14
  • +2ቆሮ 9:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 6፣ ገጽ 1

ዘሌዋውያን 1:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 10:11
  • +ዕብ 9:13, 14

ዘሌዋውያን 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 7:8

ዘሌዋውያን 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 6:12

ዘሌዋውያን 1:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኩላሊቱን ከሸፈነው ስብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 18:23

ዘሌዋውያን 1:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 8:20, 21፤ ዘኁ 15:2, 3

ዘሌዋውያን 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:4
  • +ዘሌ 12:6፤ 22:18-20

ዘሌዋውያን 1:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:16-18፤ ዘሌ 8:18-21፤ 9:12-14

ዘሌዋውያን 1:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኩላሊቱን የሸፈነውን ስብ።”

ዘሌዋውያን 1:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

ዘሌዋውያን 1:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:7፤ 12:8፤ ሉቃስ 2:24

ዘሌዋውያን 1:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በስብ የራሰው አመድ።” መሥዋዕት ሆነው በሚቀርቡት እንስሳት ስብ የራሰውን አመድ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 27:3፤ ዘሌ 4:11, 12፤ 6:10

ዘሌዋውያን 1:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 1:1ዘፀ 40:34
ዘሌ. 1:2ዘሌ 22:18-20
ዘሌ. 1:3ዘዳ 15:19, 21፤ ሚል 1:14
ዘሌ. 1:32ቆሮ 9:7
ዘሌ. 1:5ዕብ 10:11
ዘሌ. 1:5ዕብ 9:13, 14
ዘሌ. 1:6ዘሌ 7:8
ዘሌ. 1:7ዘሌ 6:12
ዘሌ. 1:81ነገ 18:23
ዘሌ. 1:9ዘፍ 8:20, 21፤ ዘኁ 15:2, 3
ዘሌ. 1:10ዘፍ 4:4
ዘሌ. 1:10ዘሌ 12:6፤ 22:18-20
ዘሌ. 1:11ዘፀ 29:16-18፤ ዘሌ 8:18-21፤ 9:12-14
ዘሌ. 1:14ዘሌ 5:7፤ 12:8፤ ሉቃስ 2:24
ዘሌ. 1:16ዘፀ 27:3፤ ዘሌ 4:11, 12፤ 6:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 1:1-17

ዘሌዋውያን

1 ይሖዋም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛ ድንኳኑ+ እንዲህ ሲል አናገረው፦ 2 “እስራኤላውያንን* አናግራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ከእናንተ መካከል ማንኛችሁም ከቤት እንስሳት ለይሖዋ መባ ማቅረብ ከፈለጋችሁ መባችሁን ከከብቶች ወይም ከመንጎች መካከል ማቅረብ አለባችሁ።+

3 “‘የሰውየው መባ ከከብቶች መካከል ተወስዶ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ማቅረብ ይኖርበታል።+ መባውን በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ+ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። 4 ለሚቃጠል መባ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ መባውም ለሰውየው ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል።

5 “‘ከዚያም ወይፈኑ በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት+ የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን ያቅርቡት፤ እንዲሁም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው መሠዊያ ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+ 6 የሚቃጠለውም መባ መገፈፍና መቆራረጥ ይኖርበታል።+ 7 ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ እሳት ያንድዱ፤+ በእሳቱም ላይ እንጨት ይረብርቡበት። 8 እነሱም ተቆራርጦ የተዘጋጀውን መባ+ ከጭንቅላቱና ከሞራው* ጋር በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደርድሩት። 9 ሆድ ዕቃውና እግሮቹም በውኃ ይታጠቡ፤ ካህኑም የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ሙሉውን በመሠዊያው ላይ ያጭሰው።+

10 “‘ሰውየው የሚቃጠል መባ እንዲሆን የሚያቀርበው መባ ከመንጋው+ ማለትም ከበግ ጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት ያቅርብ።+ 11 በስተ ሰሜን በኩል ባለው የመሠዊያው ጎን በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+ 12 እሱም ጭንቅላቱንና ሞራውን* ጨምሮ እንስሳውን በየብልቱ ይቆራርጠዋል፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደረድራቸዋል። 13 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ያጥባቸዋል፤ ካህኑም ሙሉውን ያቀርበዋል፤ እንዲሁም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።

14 “‘ሆኖም ሰውየው አእዋፋትን ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ መባውን ከዋኖሶች ወይም ከርግብ ጫጩቶች መካከል ያቀርባል።+ 15 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ እንዲሁም አንገቱ ላይ ቦጭቆ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ደሙ ግን በመሠዊያው ጎን ይንጠፍጠፍ። 16 ቋቱንና ላባዎቹንም ከለየ በኋላ ከመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ቦታ ይወርውራቸው።+ 17 ሙሉ በሙሉ ለሁለት ሳይለያየው ክንፎቹን ይዞ ይሰነጥቀዋል። ከዚያም ካህኑ በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ