የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 40
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ናቡዛራዳን ኤርምያስን በነፃ ለቀቀው (1-6)

      • ጎዶልያስ በምድሪቱ ላይ ተሾመ (7-12)

      • በጎዶልያስ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ (13-16)

ኤርምያስ 40:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:9፤ 52:12, 13
  • +ኢያሱ 18:21, 25

ኤርምያስ 40:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 50:7

ኤርምያስ 40:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:11, 12

ኤርምያስ 40:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:8
  • +2ነገ 22:12, 13፤ ኤር 26:24
  • +2ነገ 25:22፤ ኤር 39:13, 14፤ 41:2

ኤርምያስ 40:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 20:1፤ 1ነገ 15:22

ኤርምያስ 40:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:22፤ ኤር 39:10

ኤርምያስ 40:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:23
  • +2ነገ 25:25
  • +ኤር 41:11, 16፤ 43:2
  • +ኤር 42:1, 2

ኤርምያስ 40:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:24፤ ኤር 27:11

ኤርምያስ 40:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ለመቆም።”

  • *

    የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 39:10

ኤርምያስ 40:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን ለማጥፋት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 41:10
  • +ኤር 41:2

ኤርምያስ 40:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን ለምን ያጥፋት?”

ኤርምያስ 40:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:22

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 40:1ኤር 39:9፤ 52:12, 13
ኤር. 40:1ኢያሱ 18:21, 25
ኤር. 40:3ኤር 50:7
ኤር. 40:4ኤር 39:11, 12
ኤር. 40:52ነገ 22:8
ኤር. 40:52ነገ 22:12, 13፤ ኤር 26:24
ኤር. 40:52ነገ 25:22፤ ኤር 39:13, 14፤ 41:2
ኤር. 40:6መሳ 20:1፤ 1ነገ 15:22
ኤር. 40:72ነገ 25:22፤ ኤር 39:10
ኤር. 40:82ነገ 25:23
ኤር. 40:82ነገ 25:25
ኤር. 40:8ኤር 41:11, 16፤ 43:2
ኤር. 40:8ኤር 42:1, 2
ኤር. 40:92ነገ 25:24፤ ኤር 27:11
ኤር. 40:10ኤር 39:10
ኤር. 40:14ኤር 41:10
ኤር. 40:14ኤር 41:2
ኤር. 40:162ነገ 25:22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 40:1-16

ኤርምያስ

40 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ኤርምያስን ከራማ+ በነፃ ከለቀቀው በኋላ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። ናቡዛራዳን ኤርምያስን ወደዚያ ሲወስደው እጆቹ በሰንሰለት ታስረው ነበር፤ ደግሞም ወደ ባቢሎን በግዞት እየተወሰዱ ከነበሩት የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ መካከል ነበር። 2 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ኤርምያስን ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አምላክህ ይሖዋ በዚህ ስፍራ ላይ ይህ ጥፋት እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል፤ 3 በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁና ቃሉን ስላልታዘዛችሁ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ይህን ጥፋት አመጣ። ይህ ነገር በእናንተ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው።+ 4 እጆችህ የታሰሩበትን ሰንሰለት ዛሬ እፈታልሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ መልካም መስሎ ከታየህ መሄድ ትችላለህ፤ እኔም እንከባከብሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ ካልፈለግክ ግን መቅረት ትችላለህ። እነሆ፣ ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት። ወደመረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”+

5 ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን+ ልጅ፣ ወደ አኪቃም+ ልጅ ወደ ጎዶልያስ+ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።”

ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው። 6 በመሆኑም ኤርምያስ በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ሄዶ በምድሪቱ በቀሩት ሕዝብ መካከል ከእሱ ጋር መኖር ጀመረ።

7 በኋላም ከሰዎቻቸው ጋር በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደሾመው እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት ባልተወሰዱትና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት ድሆች የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።+ 8 ስለሆነም በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣+ የቃሬሃ ልጆች የሆኑት ዮሃናን+ እና ዮናታን፣ የታንሁመት ልጅ ሰራያህ፣ የነጦፋዊው የኤፋይ ልጆችና የማአካታዊው ልጅ የዛንያህ+ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ናቸው። 9 የሳፋን ልጅ፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሎ ማለላቸው፦ “ከለዳውያንን ማገልገል አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።+ 10 እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እናንተን ወክዬ ለመቅረብ* በምጽጳ እቀመጣለሁ። እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬዎችና* ዘይት አከማቹ፤ በማጠራቀሚያ ዕቃዎቻችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸው ከተሞችም ውስጥ ኑሩ።”+

11 በሞዓብ፣ በአሞንና በኤዶም እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩት አይሁዳውያንም በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ የተወሰኑ ቀሪዎች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ እንደፈቀደላቸውና የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በእነሱ ላይ እንደሾመ ሰሙ። 12 በመሆኑም አይሁዳውያኑ በሙሉ ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ይመለሱ ጀመር፤ በይሁዳ ምድር በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም ወይንና የበጋ ፍሬዎችን በብዛት አከማቹ።

13 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። 14 እንዲህም አሉት፦ “የአሞናውያን+ ንጉሥ ባአሊስ አንተን ለመግደል* የነታንያህን ልጅ እስማኤልን እንደላከው አታውቅም?”+ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

15 ከዚያም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ ጎዶልያስን በምጽጳ በሚስጥር እንዲህ አለው፦ “ሄጄ የነታንያህን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ማንም አያውቅም። ለምን ይግደልህ?* ወደ አንተ የተሰበሰቡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ለምን ይበተኑ? የይሁዳ ቀሪዎችስ ለምን ይጥፉ?” 16 የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ+ ግን የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን “ስለ እስማኤል የምትነግረኝ ነገር እውነት ስላልሆነ እንዲህ አታድርግ” አለው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ