የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በአሞናውያንና በሶርያውያን ላይ የተገኘ ድል (1-19)

2 ሳሙኤል 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:36, 38፤ መሳ 10:7፤ 11:12, 33፤ 1ሳሙ 11:1
  • +1ዜና 19:1-5

2 ሳሙኤል 10:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:27

2 ሳሙኤል 10:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:21

2 ሳሙኤል 10:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከጦብ ሰዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:21
  • +2ሳሙ 8:5
  • +ኢያሱ 13:13
  • +1ዜና 19:6, 7

2 ሳሙኤል 10:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 23:8፤ 1ዜና 19:8, 9

2 ሳሙኤል 10:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከጦብ ሰዎችና።”

2 ሳሙኤል 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 19:10-13

2 ሳሙኤል 10:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 26:6፤ 2ሳሙ 2:18፤ 23:18፤ 1ዜና 2:15, 16
  • +ዘኁ 21:24

2 ሳሙኤል 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:6
  • +መዝ 37:5፤ 44:5፤ ምሳሌ 29:25

2 ሳሙኤል 10:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 19:14, 15

2 ሳሙኤል 10:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 19:16

2 ሳሙኤል 10:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:3-5
  • +ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 23:31

2 ሳሙኤል 10:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 19:17-19

2 ሳሙኤል 10:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:1፤ መዝ 18:37, 38

2 ሳሙኤል 10:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 20:10, 11

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 10:1ዘፍ 19:36, 38፤ መሳ 10:7፤ 11:12, 33፤ 1ሳሙ 11:1
2 ሳሙ. 10:11ዜና 19:1-5
2 ሳሙ. 10:4ዘሌ 19:27
2 ሳሙ. 10:5ኢያሱ 18:21
2 ሳሙ. 10:6ዘኁ 13:21
2 ሳሙ. 10:62ሳሙ 8:5
2 ሳሙ. 10:6ኢያሱ 13:13
2 ሳሙ. 10:61ዜና 19:6, 7
2 ሳሙ. 10:72ሳሙ 23:8፤ 1ዜና 19:8, 9
2 ሳሙ. 10:91ዜና 19:10-13
2 ሳሙ. 10:101ሳሙ 26:6፤ 2ሳሙ 2:18፤ 23:18፤ 1ዜና 2:15, 16
2 ሳሙ. 10:10ዘኁ 21:24
2 ሳሙ. 10:12ዘዳ 31:6
2 ሳሙ. 10:12መዝ 37:5፤ 44:5፤ ምሳሌ 29:25
2 ሳሙ. 10:131ዜና 19:14, 15
2 ሳሙ. 10:151ዜና 19:16
2 ሳሙ. 10:162ሳሙ 8:3-5
2 ሳሙ. 10:16ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 23:31
2 ሳሙ. 10:171ዜና 19:17-19
2 ሳሙ. 10:18ዘዳ 20:1፤ መዝ 18:37, 38
2 ሳሙ. 10:19ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 20:10, 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 10:1-19

ሁለተኛ ሳሙኤል

10 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን+ ንጉሥ ሞተ፤ ልጁ ሃኑንም በእሱ ፋንታ ነገሠ።+ 2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር እንዳሳየኝ ሁሉ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። ስለሆነም ዳዊት፣ በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት አገልጋዮቹን ወደ ሃኑን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ወደ አሞናውያን ምድር ሲደርሱ 3 የአሞናውያን መኳንንት ጌታቸውን ሃኑንን “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? ዳዊት አገልጋዮቹን ወደ አንተ የላከው ከተማዋን በሚገባ ለማጥናት፣ ለመሰለልና ለመገልበጥ አይደለም?” አሉት። 4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ግማሹን ጢማቸውን ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። 5 ዳዊትም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ ሰዎቹ ላከ፤ ምክንያቱም በኀፍረት ተውጠው ነበር፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

6 ውሎ አድሮ አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ጥንብ እንደተቆጠሩ ተገነዘቡ፤ በመሆኑም አሞናውያን፣ ሰዎችን በመላክ ከቤትሬሆብ+ ሶርያውያንና ከጾባህ+ ሶርያውያን 20,000 እግረኛ ተዋጊዎችን፣ የማአካን+ ንጉሥ ከ1,000 ሰዎች ጋር እንዲሁም ከኢሽጦብ* 12,000 ሰዎችን ቀጠሩ።+ 7 ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን እንዲሁም እጅግ ኃያላን የሆኑትን ተዋጊዎቹን+ ጨምሮ መላውን ሠራዊት ላከ። 8 አሞናውያንም ወጥተው በከተማዋ መግቢያ ላይ ለውጊያ ተሰለፉ፤ የጾባህና የሬሆብ ሶርያውያን ደግሞ ከኢሽጦብና* ከማአካ ጋር ሆነው ለብቻቸው ሜዳ ላይ ተሰለፉ።

9 ኢዮዓብ ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ እሱ እየገሰገሱ መምጣታቸውን ሲያይ በእስራኤል ካሉት ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።+ 10 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ+ አመራር ሥር* ሆነው አሞናውያንን+ እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። 11 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትደርስልኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እደርስልሃለሁ። 12 ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል ብርቱና ደፋር መሆን አለብን፤+ ይሖዋም በፊቱ መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋል።”+

13 ከዚያም ኢዮዓብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሶርያውያንን ለመግጠም ወደ እነሱ ሲገሰግሱ ሶርያውያኑ ከፊታቸው ሸሹ።+ 14 አሞናውያንም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ሲያዩ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዋ ገቡ። ከዚያም ኢዮዓብ አሞናውያንን ከመውጋት ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።

15 ሶርያውያንም በእስራኤላውያን ድል እንደተመቱ ሲያዩ በአዲስ መልክ ተደራጁ።+ 16 በመሆኑም ሃዳድኤዜር+ በወንዙ*+ አካባቢ ወደነበሩት ሶርያውያን መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም የሃዳድኤዜር ሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሄላም መጡ።

17 ዳዊት ወሬው በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ እስራኤላውያንን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን በመሻገር ወደ ሄላም መጣ። ሶርያውያንም ዳዊትን ለመግጠም ተሰለፉ፤ ከእሱም ጋር ተዋጉ።+ 18 ሆኖም ሶርያውያን ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 700 ሠረገለኞችንና 40,000 ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊታቸው አለቃ የሆነውን ሾባክንም መታው፤ እሱም እዚያው ሞተ።+ 19 የሃዳድኤዜር አገልጋዮች የሆኑት ነገሥታት በሙሉ እስራኤላውያን እንዳሸነፏቸው ባዩ ጊዜ ወዲያውኑ ከእስራኤላውያን ጋር እርቅ በመፍጠር ለእነሱ ተገዙ፤+ ሶርያውያንም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ