የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሳባ ዓመፀ፤ ኢዮዓብ አሜሳይን ገደለው (1-13)

      • ሳባን አሳደው ደረሱበት፤ እንዲሁም ተገደለ (14-22)

      • የዳዊት አስተዳደር (23-26)

2 ሳሙኤል 20:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ወደየድንኳንህ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 20:21
  • +መሳ 3:26, 27፤ 2ሳሙ 15:10
  • +2ሳሙ 19:43
  • +1ነገ 12:16

2 ሳሙኤል 20:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 24:21
  • +2ሳሙ 19:15, 41, 42

2 ሳሙኤል 20:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:11
  • +2ሳሙ 15:16
  • +2ሳሙ 16:21, 22

2 ሳሙኤል 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 17:25፤ 19:13፤ 1ዜና 2:17

2 ሳሙኤል 20:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 26:6፤ 2ሳሙ 10:10፤ 23:18፤ 1ዜና 18:12
  • +2ሳሙ 20:1
  • +2ሳሙ 15:12

2 ሳሙኤል 20:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:16
  • +2ሳሙ 8:18፤ 15:18፤ 1ነገ 1:38

2 ሳሙኤል 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:21, 25፤ 21:8, 17
  • +2ሳሙ 17:25፤ 19:13

2 ሳሙኤል 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 3:27፤ 1ነገ 2:5

2 ሳሙኤል 20:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 20:1

2 ሳሙኤል 20:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:20፤ 2ነገ 15:29

2 ሳሙኤል 20:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እነሱም።”

2 ሳሙኤል 20:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የምትውጠው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 32:9

2 ሳሙኤል 20:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጁን አንስቷል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 17:14, 15፤ መሳ 2:8, 9
  • +2ሳሙ 20:1

2 ሳሙኤል 20:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 9:14, 15, 18

2 ሳሙኤል 20:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:16፤ 19:13
  • +1ዜና 12:27
  • +2ሳሙ 23:20፤ 1ዜና 27:5
  • +2ሳሙ 8:18፤ 15:18፤ 1ነገ 1:38, 44

2 ሳሙኤል 20:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 4:6፤ 12:18
  • +1ነገ 4:3

2 ሳሙኤል 20:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:27
  • +2ሳሙ 17:15፤ 19:11፤ 1ነገ 4:4

2 ሳሙኤል 20:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ካህን።”

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 20:12ሳሙ 20:21
2 ሳሙ. 20:1መሳ 3:26, 27፤ 2ሳሙ 15:10
2 ሳሙ. 20:12ሳሙ 19:43
2 ሳሙ. 20:11ነገ 12:16
2 ሳሙ. 20:2ምሳሌ 24:21
2 ሳሙ. 20:22ሳሙ 19:15, 41, 42
2 ሳሙ. 20:32ሳሙ 5:11
2 ሳሙ. 20:32ሳሙ 15:16
2 ሳሙ. 20:32ሳሙ 16:21, 22
2 ሳሙ. 20:42ሳሙ 17:25፤ 19:13፤ 1ዜና 2:17
2 ሳሙ. 20:61ሳሙ 26:6፤ 2ሳሙ 10:10፤ 23:18፤ 1ዜና 18:12
2 ሳሙ. 20:62ሳሙ 20:1
2 ሳሙ. 20:62ሳሙ 15:12
2 ሳሙ. 20:72ሳሙ 8:16
2 ሳሙ. 20:72ሳሙ 8:18፤ 15:18፤ 1ነገ 1:38
2 ሳሙ. 20:8ኢያሱ 18:21, 25፤ 21:8, 17
2 ሳሙ. 20:82ሳሙ 17:25፤ 19:13
2 ሳሙ. 20:102ሳሙ 3:27፤ 1ነገ 2:5
2 ሳሙ. 20:132ሳሙ 20:1
2 ሳሙ. 20:141ነገ 15:20፤ 2ነገ 15:29
2 ሳሙ. 20:19ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 32:9
2 ሳሙ. 20:21ኢያሱ 17:14, 15፤ መሳ 2:8, 9
2 ሳሙ. 20:212ሳሙ 20:1
2 ሳሙ. 20:22መክ 9:14, 15, 18
2 ሳሙ. 20:232ሳሙ 8:16፤ 19:13
2 ሳሙ. 20:231ዜና 12:27
2 ሳሙ. 20:232ሳሙ 23:20፤ 1ዜና 27:5
2 ሳሙ. 20:232ሳሙ 8:18፤ 15:18፤ 1ነገ 1:38, 44
2 ሳሙ. 20:241ነገ 4:6፤ 12:18
2 ሳሙ. 20:241ነገ 4:3
2 ሳሙ. 20:252ሳሙ 15:27
2 ሳሙ. 20:252ሳሙ 17:15፤ 19:11፤ 1ነገ 4:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 20:1-26

ሁለተኛ ሳሙኤል

20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+ 2 ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ዳዊትን መከተል ትተው የቢክሪን ልጅ ሳባን መከተል ጀመሩ፤+ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው አልተለዩም።+

3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤቱ*+ ሲመጣ ንጉሡ ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው ሄዶ የነበሩትን አሥሩን ቁባቶቹን+ ወስዶ በዘብ በሚጠበቅ አንድ ቤት ውስጥ አስገባቸው። በየጊዜው ቀለብ ይሰጣቸው የነበረ ቢሆንም ከእነሱ ጋር ምንም ግንኙነት አልፈጸመም።+ እነሱም ባላቸው በሕይወት ያለ ቢሆንም እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ እንደ መበለት ሆነው ኖሩ።

4 ንጉሡም አሜሳይን+ “የይሁዳን ሰዎች በሦስት ቀን ውስጥ ጠርተህ ወደ እኔ ሰብስብልኝ፤ አንተም እዚህ መገኘት ይኖርብሃል” አለው። 5 ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳን ሕዝብ ለመሰብሰብ ሄደ፤ ሆኖም ንጉሡ ከቀጠረለት ጊዜ ዘገየ። 6 ከዚያም ዳዊት አቢሳን+ “ከአቢሴሎም ይልቅ የቢክሪ ልጅ ሳባ+ የከፋ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል።+ ስለሆነም የተመሸጉ ከተሞች አግኝቶ እንዳያመልጠን የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው” አለው። 7 በመሆኑም የኢዮዓብ+ ሰዎች፣ ከሪታውያን፣ ጴሌታውያን+ እና ኃያላን የሆኑት ሰዎች በሙሉ ተከትለውት ሄዱ፤ የቢክሪን ልጅ ሳባን ለማሳደድም ከኢየሩሳሌም ወጡ። 8 እነሱም በገባኦን+ በሚገኘው ትልቅ ድንጋይ አጠገብ ሲደርሱ አሜሳይ+ ሊገናኛቸው መጣ። ኢዮዓብ የጦር ልብሱን ለብሶ፣ ወገቡም ላይ ሰይፉን ከነሰገባው ታጥቆ ነበር። ወደ ፊት ራመድ ሲልም ሰይፉ ከሰገባው ወደቀ።

9 ኢዮዓብም አሜሳይን “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህ?” አለው። ከዚያም ኢዮዓብ የሚስመው አስመስሎ በቀኝ እጁ የአሜሳይን ጢም ያዘ። 10 አሜሳይ፣ በኢዮዓብ እጅ ከነበረው ሰይፍ ራሱን አልጠበቀም፤ ኢዮዓብም በሰይፉ ሆዱ ላይ ወጋው፤+ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ። ዳግመኛ መውጋት እንኳ ሳያስፈልገው አንዴ ብቻ ወግቶ ገደለው። ከዚያም ኢዮዓብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሳባን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ።

11 ከኢዮዓብ ወጣቶች መካከል አንዱ አሜሳይ አጠገብ ቆሞ “ከኢዮዓብ ጎን የሚቆምና የዳዊት የሆነ ማንኛውም ሰው ኢዮዓብን ይከተል!” ይል ነበር። 12 በዚህ ጊዜ አሜሳይ መንገዱ መሃል ላይ በደም ተጨማልቆ ይንፈራገጥ ነበር። ሰውየውም ሰዉ ሁሉ እዚያ ሲደርስ እንደሚቆም ሲያይ አሜሳይን ከመንገዱ ላይ ወደ ሜዳው ገለል አደረገው። ይሁንና ሰዉ ሁሉ አሁንም እሱ ጋ ሲደርስ እንደሚቆም ሲያይ ልብስ ጣል አደረገበት። 13 አሜሳይን ከመንገዱ ላይ ካነሳው በኋላ ሰዉ ሁሉ የቢክሪን ልጅ ሳባን+ ለማሳደድ ኢዮዓብን ተከትሎ ሄደ።

14 ሳባም የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አልፎ ወደ ቤትማዓካዋ አቤል+ ሄደ። ቢክሪያውያንም ተሰብስበው ተከተሉት።

15 ኢዮዓብና ሰዎቹም* መጥተው ሳባን በቤትማዓካዋ አቤል እንዳለ ከበቡት፤ በከተማዋም ዙሪያ የአፈር ቁልል ደለደሉ፤ ከተማዋም በአፈር ቁልሉ መሃል ነበረች። ከኢዮዓብም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ የከተማዋን ቅጥር ለመጣል ከሥሩ ይሰረስሩ ነበር። 16 ከከተማዋም ውስጥ አንዲት ብልህ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ስሙ፣ እናንተ ሰዎች ስሙ! እባካችሁ ኢዮዓብን ‘ወደዚህ ቅረብና ላነጋግርህ’ በሉት” አለች። 17 እሱም ወደ እሷ ቀረበ፤ ከዚያም ሴትየዋ “ኢዮዓብ አንተ ነህ?” አለችው፤ እሱም “አዎ፣ እኔ ነኝ” አላት። በዚህ ጊዜ “አገልጋይህ የምትልህን ስማ” አለችው። እሱም መልሶ “እሺ እየሰማሁ ነው” አላት። 18 እሷም እንዲህ አለች፦ “ቀደም ባሉት ጊዜያት ሰዎች ‘በአቤል ከተማ ይጠይቁ’ ይሉ ነበር፤ ጉዳያቸውም እልባት ያገኛል። 19 እኔ የእስራኤልን ሰላማዊና ታማኝ ሰዎች እወክላለሁ። አንተ በእስራኤል ውስጥ እንደ እናት የሆነችን ከተማ ልትደመስስ ትፈልጋለህ። የይሖዋን ውርሻ የምታጠፋው* ለምንድን ነው?”+ 20 ኢዮዓብም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከተማዋን ማጥፋትም ሆነ መደምሰስ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው። 21 ነገሩ እንደዚያ አይደለም። ሆኖም ከኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ የመጣውና የቢክሪ ልጅ የሆነው ሳባ+ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዓምፆአል።* ይህን ሰው አሳልፋችሁ ከሰጣችሁኝ ከተማዋን ትቼ እሄዳለሁ።” ከዚያም ሴትየዋ ኢዮዓብን “እንግዲህ የሰውየው ራስ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል!” አለችው።

22 ብልህ የሆነችው ሴትም ወዲያውኑ ወደ ሕዝቡ ሄደች፤ እነሱም የቢክሪን ልጅ የሳባን ራስ ቆርጠው ለኢዮዓብ ወረወሩለት። በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ ቀንደ መለከት ነፋ፤ እነሱም ከተማዋን ትተው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደቤቱ ሄደ፤+ ኢዮዓብም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሡ ተመለሰ።

23 ኢዮዓብ የመላው የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ነበር፤+ የዮዳሄ+ ልጅ በናያህ+ ደግሞ በከሪታውያንና በጴሌታውያን+ ላይ የበላይ ነበር። 24 አዶራም+ የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ በተመለመሉት ላይ የበላይ ነበር፤ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ነበር። 25 ሻዌ ጸሐፊ ነበር፤ ሳዶቅና+ አብያታር+ ደግሞ ካህናት ነበሩ። 26 በተጨማሪም ያኢራዊው ኢራ ዋና ኃላፊ* ሆኖ ዳዊትን ያገለግል ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ