የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 40
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ዮሴፍ የእስረኞቹን ሕልም ፈታላቸው (1-19)

        • “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?” (8)

      • የፈርዖን የልደት በዓል (20-23)

ዘፍጥረት 40:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2015፣ ገጽ 13

ዘፍጥረት 40:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:20-22

ዘፍጥረት 40:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 37:36
  • +ዘፍ 39:20፤ መዝ 105:17, 18

ዘፍጥረት 40:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ለተወሰኑ ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 39:22

ዘፍጥረት 40:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2015፣ ገጽ 12-13

ዘፍጥረት 40:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 41:15, 16፤ ዳን 2:28, 45

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2015፣ ገጽ 13

    12/1/2011፣ ገጽ 12-13

    ራእይ፣ ገጽ 9, 119, 246-247

ዘፍጥረት 40:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራስህን ያነሳል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 41:12, 13
  • +ዘፍ 40:20, 21

ዘፍጥረት 40:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2017፣ ገጽ 20-21

ዘፍጥረት 40:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ፤ ጉድጓድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 37:28
  • +ዘፍ 39:7, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2023፣ ገጽ 16

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2017፣ ገጽ 20-21

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/2014፣ ገጽ 14-15

ዘፍጥረት 40:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራስህን ከላይህ ላይ ያነሳል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:20, 22

ዘፍጥረት 40:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራስ ከፍ አደረገ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 44

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1998፣ ገጽ 31

ዘፍጥረት 40:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:8

ዘፍጥረት 40:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:14

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 40:1ዘፍ 40:11
ዘፍ. 40:2ዘፍ 40:20-22
ዘፍ. 40:3ዘፍ 37:36
ዘፍ. 40:3ዘፍ 39:20፤ መዝ 105:17, 18
ዘፍ. 40:4ዘፍ 39:22
ዘፍ. 40:8ዘፍ 41:15, 16፤ ዳን 2:28, 45
ዘፍ. 40:13ዘፍ 41:12, 13
ዘፍ. 40:13ዘፍ 40:20, 21
ዘፍ. 40:15ዘፍ 37:28
ዘፍ. 40:15ዘፍ 39:7, 8
ዘፍ. 40:19ዘፍ 40:20, 22
ዘፍ. 40:20ማር 6:21
ዘፍ. 40:22ዘፍ 40:8
ዘፍ. 40:23ዘፍ 40:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 40:1-23

ዘፍጥረት

40 ይህ ከሆነ በኋላ የግብፁ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና+ የዳቦ ጋጋሪዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፁን ንጉሥ በደሉ። 2 በመሆኑም ፈርዖን በሁለቱ ሹማምንቱ ማለትም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ ላይ እጅግ ተቆጣ፤+ 3 እሱም በዘቦች አለቃ+ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ይኸውም ዮሴፍ በታሰረበት እስር ቤት+ ውስጥ እንዲታሰሩ አደረገ። 4 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ፣ ዮሴፍ ከእነሱ ጋር እንዲሆንና እንዲረዳቸው መደበው፤+ እነሱም ለተወሰነ ጊዜ* ወህኒ ቤት ውስጥ ቆዩ።

5 እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩት የግብፁ ንጉሥ መጠጥ አሳላፊና ዳቦ ጋጋሪ በአንድ ሌሊት ሕልም አለሙ፤ የእያንዳንዳቸውም ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። 6 በማግስቱ ጠዋት ዮሴፍ ገብቶ ሲያያቸው ተክዘው አገኛቸው። 7 በመሆኑም በጌታው ቤት ከእሱ ጋር የታሰሩትን የፈርዖንን ሹማምንት “ምነው ዛሬ ፊታችሁ በሐዘን ጠቆረ?” ሲል ጠየቃቸው። 8 እነሱም “ሁለታችንም ሕልም አልመን ነበር፤ ሕልማችንን የሚፈታልን ሰው ግን አላገኘንም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?+ እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

9 በመሆኑም የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፦ “በሕልሜ ከፊት ለፊቴ አንድ የወይን ተክል አየሁ። 10 በወይኑም ተክል ላይ ሦስት ቀንበጦች ነበሩ፤ ተክሉም በማቆጥቆጥ ላይ እያለ አበባ አወጣ፤ በዘለላዎቹም ላይ ያሉት ፍሬዎች በሰሉ። 11 እኔም የፈርዖንን ጽዋ በእጄ ይዤ ነበር፤ የወይን ፍሬዎቹንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ውስጥ ጨመቅኳቸው። ከዚያም ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” 12 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እንዲህ አለው፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቀንበጦች ሦስት ቀናት ናቸው። 13 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤* ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል።+ አንተም የመጠጥ አሳላፊው በነበርክበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።+ 14 ይሁንና ሁኔታዎች ሲስተካከሉልህ እኔን እንዳትረሳኝ። እባክህ ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ከዚህ እስር ቤት እንዲያስፈታኝም ስለ እኔ ለፈርዖን ንገረው። 15 በመሠረቱ እኔ ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት ተገድጄ ነው፤+ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት* ውስጥ የጣሉኝ ያለምንም ጥፋት ነው።”+

16 የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃም ዮሴፍ የተናገረው የሕልሙ ፍቺ መልካም መሆኑን ሲያይ እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔም ሕልም አይቼ ነበር፤ በሕልሜም ነጭ ዳቦዎች የያዙ ሦስት ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17 ከላይ ባለው ቅርጫት ውስጥ ለፈርዖን የሚቀርቡ የተለያዩ የተጋገሩ ምግቦች ነበሩ፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከተሸከምኩት ቅርጫት ውስጥ ይበሉ ነበር።” 18 ከዚያም ዮሴፍ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቅርጫቶች ሦስት ቀናት ናቸው። 19 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ራስህን ይቆርጣል፤* በእንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበላሉ።”+

20 ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤+ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው።* 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። 22 የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው።+ 23 ይሁንና የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ጨርሶም ረሳው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ